ፈልግ

የኒካራጓ መንግሥት ከእስር የፈቷቸው ብጹዕ አቡነ ሮላንዶ አልቫሬዝ የኒካራጓ መንግሥት ከእስር የፈቷቸው ብጹዕ አቡነ ሮላንዶ አልቫሬዝ   (AFP or licensors)

የኒካራጓ መንግሥት ነፃ የለቀቋቸውን ጳጳስ ጨምሮ 15 ካኅናትን ቅድስት መንበር መቀበሏን አስታወቀች

የኒካራጓ መንግሥት እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከ2022 ዓ. ም. ጀምሮ ያሰሯቸውን የማታጋልፓ ጳጳስ እና ሁለት የዘርዓ ክህነት ተማሪዎችን ጨምሮ 15 ካህናትን ከእስር መፍታቱን አረጋገጠ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የኒካራጓ መንግሥት ከእስር ነጻ የለቀቃቸው ከአንድ ዓመት በላይ ታስረው የቆዩት ብጹዕ አቡነ ሮላንዶ አልቫሬዝ፣ ብጹዕ አቡነ ኢሲዶሮ ዴል ካርመን ሞራ ኦርቴጋ፣ ሁለት የዘርዓ ክህነት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና 15 ካኅናት እንደሆኑ ታውቋል። የኒካራጓ መንግሥት ከእስር የፈታቸው 19 የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች እንደ ሆኑ ታውቋል።

በዋና ከተማዋ ማናጉዋ የሚገኙ የመንግሥት ባለስልጣናት በሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በመጀመሪያ የተሰራጨውን ዘገባ አረጋግጠዋል። በቬንዙዌላ ውስጥ ከቀሩት ከአንዱ በስተቀር ሁሉም እሑድ ጥር 5/2016 ዓ. ም. ከሰዓት በኋላ ወደ ሮም ደርሰው ቅድስት መንበር በእንግድነት መቀበሏ ታውቋል።

የ26 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸው የነበረ የማታጋልፓ ጳጳስ እና የእስቴሊ ሀገረ ስብከት ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ ብጹዕ አቡነ አልቫሬዝ ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ከተያዙ በኋላ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከነሐሴ ወር 2022 ዓ. ም. በእስር መቆየታቸው ይታወሳል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሑድ ጥር 5/2016 ዓ. ም. ባቀረቡት የመልዓከ እግዚአብሔር ጸሎት መጀመሪያ ላይ ባሰሙት ንግግር፥ በመካከለኛው አሜሪካ አገር ኒካራጓ ውስጥ ነጻነታቸውን የተነጠቁ ብጹዓን  ጳጳሳት እና ካኅናት የሚገኙበትን ሁኔታ ተናግረው፥ በጸሎት እንደሚያስታውሷቸው በማረጋገጥ፥ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ለኒካራጓ እንዲጸልዩ በማሳሰብ፥ ውይይት ዘወትር ችግሮች የሚፈታበት መንገድ እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

ባለፈው ጥቅምት ወር 12 የኒካራጓ ካኅናት ከእስር ተፈትተው እንደ ነበር ሲታወስ፥ ከዚያም በኋላ ቅድስት መንበር ከእስር የተፈቱትን እንድትቀበላቸው የቀረበላትን ጥያቄ ተቀብላው ወደ ሮም ጠርታቸው ማስተናገዷ ይታወሳል።

 

15 January 2024, 15:34