ፈልግ

“ውዳሴ ለእግዚአብሔር”  ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ይፋ በሆነበት ዕለት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ “ውዳሴ ለእግዚአብሔር” ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ይፋ በሆነበት ዕለት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ   (VATICAN MEDIA Divisione Foto)

ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲዎች በሥነ-ምሕዳር የመስመር ላይ ትምህርት ለመስጠት መዘጋጀታቸው ተገለጸ

በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሚተዳደሩ በሮም የሚገኙ ጳጳሳዊ ዩኒቨርስቲዎች ምድራችን ለገጠማት እና ከዚህ በፊት ታይቶ ለማያውቅ ተግዳሮት ምላሽ ለመስጠት የሚያግዝ በጠቅላላ ሥነ-ምህዳር ላይ ያተኮረ የመስመር ላይ የዲፕሎማ ትምህርት ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ገለጹ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ሮም ውስጥ የሚገኙ እና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሚተዳደሩ ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲዎች በመቀናጀት በሥነ-ምህዳር ላይ ያተኮረ አዲስ የዲፕሎማ ትምርት በጋር ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስታውቀዋል። ይህም ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቁልፍ ጽንሰ-ሀሳብ ማለትም ለአካባቢያዊ፣ ኤኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ሥነ-ምግባራዊ ጉዳዮች እርስ በርስ የተሳሰሩ ለመሆናቸው አጽንዖትን የሚሰጥ እንደሆነ ተነግሯል። ትምህርቱ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከጥር ወር እስከ ሰኔ ወር 2024 ዓ. ም. የሚቆይ ሲሆን፥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በታወቁ ምሁራን፣ የአገር መሪዎች እና የማኅበርሰሰብ አንቂዎች የሚሰጥ እንደሆነ ታውቋል።

“የጋራ መኖሪያ ምድራችን ወደ መሰባበር ቀርርባለች"

ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲዎቹ በጋራ ባወጡት ጋዜጣዊ መግለጫቸው እንዳስታወቁት፥ ትምህርቱ ምድራችንን ለገጠማት እና ከዚህ በፊት ታይቶ ለማያውቅ ተግዳሮት ምላሽ ለመስጠት ያለመ እንደሆነ ገልጸው፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2015 ዓ. ም. “ውዳሴ ላንተ ይሁን” በሚል ርዕሥ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ማበርከታቸውን በማስታወስ፥ ይህ ታሪካዊ ቃለ ምዕዳንም በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች በሙሉ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ያቀረቡበት እንደሆነ አስረድተዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በቅርቡ “ውዳሴ ለእግዚአብሔር” በማለት ይፋ ባደረጉት ሁለተኛው እና ተከታታይ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳናቸው የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እስካሁን የተደረጉ ጥረቶች በቂ እንዳልነበሩ በመገንዘብ ባስተላለፉት መልዕክት፥ “በጋራ የምንኖርባት ዓለማችን የፈራረሰች እና ወደ መሰባበር እየተቃረበች ነው” ማለታቸውን ዩኒቨርሲቲዎቹ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።

የትምህርት ዓይነቶች ዝርዝሮች

ጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ የሚስጡትን የዲፕሎማ ትምህርት ለመጀመሪያ ያዘጋጁት እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2016 ዓ. ም. ሲሆን፥ አሁን ግን ለመጀመሪያ ጊዜ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ጭምር ማዘጋጀታው ታውቋል።

ትምህርቱ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ከጥር እስከ ሰኔ 2024 ዓ. ም. ድረስ የሚሰጥ ሲሆን፥ ስድስት ምዕራፍች ያሉት እያንዳንዱ ምዕራፍ 90 ደቂቃ የሚወስድና በወሩ ሦስተኛ ሐሙስ በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ ከሰባት ሰዓት ተኩል እስከ ዘጠኝ ሰዓት የሚቆይ እንደሆነ ተገልጿል። እንዲሁም በመጋቢት ወር ወርክሾፕ እንደተዘጋጀ እና በግንቦት ወርም “ውዳሴ ለእግዚአብሔር” በሚለው ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ላይ ዓለም አቀፍ የመስመር ላይ ኮንፈረንስ እንደሚኖር ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ መግለጫቸው አስታውቀዋል።

ትምህርቱ በይፋ የሚከፈተው እንደ ጎርጎሮሳውያኑ ጥር 25/2024 ዓ. ም. ሲሆን የምዝገባ ሂደቱ ግን እስከ መጋቢት 31/2024 ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ዩኒቨርሲቲዎቹ አክለው አስታውቀዋል። ለተማሪዎች ምዝገባ እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት፥  https://www.unigre.it/en/events-and-communication/communication/news-and-press-releases/registration-open-online-course-on-integral-ecology/   የሚለውን ሊንክ መጠቀም እንደሚቻል ተጠቅሷል።

18 January 2024, 15:39