በቫቲካን ሙዚየም ውስጥ የዐብይ ጾም ወቅት እንደ የተስፋ ምልክት ይቆጠራል!
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
"ክርስቶስ ተነስቷል! በእውነት ተነሥቷል!" በኢየሱስ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በሞት ላይ የተገኘው ድል እርግጠኝነት ከመጀመሪያዎቹ መቶ ዘመናት ጀምሮ ክርስቲያኖች ፋሲካን በሚያከብሩበት ወቅት በተለዋወጡት የትንሳኤ ሰላምታ ውስጥ ያስተጋባል። የአዚዚው ቅዱስ ፍራንችስኮስ ለልዑል እግዚአብሔር የጠየቀው “የተወሰነ ተስፋ” በጥንቶቹ ክርስቲያኖች እምነት ላይ ሥር የሰደደ ነበር። የደረሱን ምስክርነቶችም ይህንኑ ያጠናክራሉ። በቫቲካን ሙዚየም ውስጥ በሚገኘው የክርስቲያን ሙዚየም እምብርት ውስጥ የሚገኘው ከድንጋይ ተቀርጾ የተሰራው የመቀበሪያ ሳጥን ለዚህ ማረጋገጫ ነው። ለስድስት ተከታታይ ቅዳሜዎች ለዐቢይ ጾም የቀረበው የሥርዓተ-ጉብኝት መርሐ ግብር የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ስብስብ ጎብኝዎች ከዚህ ይጀምራል።
ከግምት ወደ ማሰላሰል
የጳጳሳዊ ስብስቦች የትምህርት ተግባራት ኃላፊ የሆኑት ሲስተር ኢማኑኤላ ኤድዋርድስ “ሥነ ጥበብ የኢየሱስን ሕይወት ማዕከላዊ ገጽታዎች በተለይም የፋሲካን ምስጢራት እንድናስታውስ የሚረዳን ኃይለኛ ዘዴ ሊሆን ይችላል” በማለት ገልጸዋል። የጌታ ህማማት እና ትንሳኤ ክስተቶች በተወሰነ ደረጃ ይጠናከራሉ ምክንያቱም የስራው ውበት በዓይኖቻችን ፊት ለተቀመጠው የእግዚአብሔር ፍቅር እውነታ ከግላዊ ግምት ወደ ተጨባጭ ማሰላሰል ስለሚወስደን ነው።
ጥበብ እና ጸሎት
በቀደምት የክርስቲያን ከድንጋይ ተቀርጾ የተሰራ የመቀበሪያ ሳጥን እብነ በረድ ላይ የተቀረጹትን እፎይታዎች ስንመለከት፣ ኪነጥበብ ለጸሎት ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር እንዴት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ወዲያውኑ እንገነዘባለን። የስቅለት ትእይንት አለመኖሩ አስገራሚ ነው። እህት ኢማኑኤላ ኤድዋርድስ ለዚህ ክስተት ያላቸውን ምክንያት ወዲያውኑ ገልጸዋል፡- “የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች የጌታን ሞትና ትንሣኤ ለማመልከት ከብሉይ ኪዳን የተወሰዱ ምሳሌዎችን ይጠቀሙ ነበር፣ ለምሳሌ ዳንኤል በአንበሳ ጉድጓድ ውስጥ እንዳለ ወይም የዮናስ ታሪክ ስንመለከት የስቅለትን ታሪክ ስንመለከት ይህንን ታሪክ ወክሎ ለመናገር በጣም አስፈሪ እንደ ሆነ እንድረዳለን" ብለዋል።
የትንሳኤ ተስፋ
"በአናስታሲስ በድንጋይ የተሰራ የቀብር ሣጥን ውስጥ፣ ትንሳኤ በምሳሌያዊ ሁኔታ በክርስቶስ የስቅለት ምስል ላይ ከተሰቀለው መስቀል ጋር በሞት ላይ ድል እንዳደረገ ያሳያል።" በዚህ ምሥጢር ታላቅነት ውስጥ የሰው ልጅ ረዳት አልባነት የሚገለጠው እና የተኙት ወታደሮች ተምሳሌት ነው። "የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ጌታ እንደተነሳ እርግጠኛ ነበሩ፣ እናም ይህ ምስል አንድ ቀን እነሱም ከክርስቶስ ጋር እንደሚነሱ ያላቸውን እምነት ይገልፃል፣ ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ እንደተናገረው። ይህ ታላቅ በድንጋይ የተሰራ የመቀበሪያ ሳጥን አሁን የምናንጸባርቅበት መንገድ ነው። በትንሳኤው ተስፋ” በማለት መነኮሳቱ አክለዋል።
አዲስ ሕይወት
ከምልክቱ ኃይል ወደ ቃሉ እውነተኛነት ነብስ ዘራ። ጉብኝቱ በቫቲካን ሙዚዬም ውስጥ የቀጠለ ሲሆን ከካራቫጂዮ ማከማቻ ፊት ለፊት የኒቆዲሞስ እይታ እና የመቃብር ድንጋይ እይታ ሕይወት አልባ በሆነው የክርስቶስ አካል በማይክል አንጄሎ ሜሪሲ በተወከለው ድራማ ላይ እንድንሳተፍ ያደርገናል። እህት ኢማኑዌላ ኤድዋርድስ ከሰዎች እይታ የሚያመልጡ ዝርዝሮችን እንድንረዳ ይጋብዙናል። "በታችኛው ጥግ ላይ አዲስ ህይወት እና የክርስቶስን ሞት በሞት ላይ ያለውን ድል የሚያመለክት ተክል ወደ ህይወት ሲመጣ የተስፋ ምልክቶች ይታያሉ"።
ከእኛ ጋር እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ
በላይኛው ማዕከለ-ስዕላት ውስጥ ከ 16 ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የአዲሱ ትምህርት ምልክቶችን እናገኛለን።"ክርስቶስ የድልን አርማ ይዞ ከመቃብር ጨለማ በኃይል የሚወጣበት" የትንሳኤ ፊት ለፊት ቆም ብለን እንመለከታለን። እኛን የሚገርመን በትንሣኤ የሚቻለውን ቃሉን ለመቀስቀስ ያህል፣ “እነሆ እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” በማለት የሚከተለን እይታው ነው። ጉብኝቱ በሲስቲን ቻፕል ይጠናቀቃል። የቫቲካን ሙዚየሞች የትምህርት ተግባራት ቢሮ ኃላፊ ምንም ጥርጥር የለውም፡- "የመጨረሻው ፍርድ የተስፋ እና የላቀ የላቀ ጥበብ ነው። በፍሎሬንቲን አርቲስት የተከበሩ ዝርዝሮችን በመጥቀስ አስረድተዋል።
የጥበብ ኃይል
ለዐብይ ጾም የተዘጋጀው ጉብኝት በኢንተርኔት በቀጥታ የግቡኝት መርሃ ግብሩን ለመቀላቀል ጥያቄ ማቅርበ ይቻላል። ለሁሉም ሰው ክፍት ነው፣ ልጆች ካሏቸው ቤተሰቦች እስከ የስሜት ህዋሳት እና የአእምሮ እክል ላለባቸው ሰዎች ጭምር ማለት ነው።
ከተሳታፊዎች መካከል "የእምነት ጉጉት" እና "የሥራዎቹ ጥበባዊ እና ሃይማኖታዊ ተምሳሌትነት ፍላጎት ያላቸው ጎብኚዎች" ናቸው፤ "እያንዳንዱ ጉብኝት - እህት ኢማኑኤላ ኤድዋርድስ ትዝብት - በኃይለኛው የጥበብ ዘዴ ለወንጌል አገልግሎት ልዩ እድል ነው"።
ጸሎት እና ተስፋ
በዚህ ዓመት ትኩረቱ እ.አ.አ በ2025 ታላቁ ኢዮቤልዩ ላይ በክርስቲያናዊ ተስፋ መሪ ሃሳብ ላይ መሆኑ የማይቀር ነው፡ የነዚ ልዩ የአብይ ዓብይ ጾም አዘጋጆች በቫቲካን ሙዚየም ጉብኝት አስተባባሪዎች ያላቸው ተስፋ “የጸሎትን ፍቅርና የእነዚያን ዘሮች ለማስተላለፍ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ነው። እምነታችን እየሞላ እንደሆነ ተስፋ እናደርጋለን።