ፈልግ

ከአገር ጉብኚነት ወደ መንፈሳዊ ተጓዥነት የተሰኘው የኢንትርኔት የመተግበሪያ ገጽ ይፋ ሆነ ከአገር ጉብኚነት ወደ መንፈሳዊ ተጓዥነት የተሰኘው የኢንትርኔት የመተግበሪያ ገጽ ይፋ ሆነ 

ዐራቱን ባዚሊካዎች ከቱሪስት ወደ መንፈሳዊ ተጓዥነት ለመቀየር የሚረዳ የኢዮቤልዩ መመሪያ አስጀመረ!

አራቱ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ባሲሊካዎች እና የቫቲካን የቅድስት መንበር ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ቡድን ለባሲሊካ መንፈሳዊ እና ጥበባዊ መመሪያ ሆኖ እንዲያገለግል እና ምእመናን “ከቱሪስት ወደ መንፈሳዊ ተጓዥነት” እንዲዞሩ ለመርዳት አዲስ ልዩ የኢንትርኔት መተግበሪያ ገጽ ለማስጀመር ማቀዱ ተገለጸ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

እ.አ.አ በ2025 ኢዮቤልዩ የጸሎት አመት ቤተክርስቲያን ስትቀጥል፣ የቫቲካን የቅድስት መንበር ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት በሮም ለሚገኙት አራቱ የጳጳሳዊ ባሲሊካዎች የተዘጋጀ የኢንትርኔት መተግበሪያ ገጽ አስጀምሯል።

“ከቱሪስት ወደ መንፈሳዊ ተጓዢነት” በሚል የኢንትርኔት መተግበሪያ ገጽ ላይ የቅዱስ ጴጥሮስን ቤተ መቅደስን፣ የቅዱስ ዮሐንስ ላተራንን፣ ከአጥር ውጪ የሚገኘውን የቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካን እና ቅድስት ማርያም ሜጀርን ባዚሊካ ጨምሮ ለወጣት ታዳሚዎች ለፍላጎታቸው በተዘጋጀ ይዘት ለማስተዋወቅ ይፈልጋል።

ሐሙስ የካቲት 14/2016 ዓ.ም ላይ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መሠረት ድረ-ገጹ የእነዚህን ቅዱሳት ቦታዎች ውበት እና ታሪክ ለማስተላለፍ እና በውስጣቸው የተሞሉ ጥበባዊ ድንቅ ስራዎችን ለማስተላለፍ በ "ድምፅ" ሚዲያ ላይ በጥንቃቄ የተሰሩ ታሪኮችን ያቀርባል።

"የድምፅ ሙቀት እና ቅንዓት"

በየእለቱ መንፈሳዊ ተጓዦችን ከሚያገለግሉ የሀይማኖት ወንዶች እና ሴቶች ጋር በኪነ ጥበብ ጥናት፣ ቁፋሮ እና እድሳት ላይ የተሰማሩ ባለሙያዎች የጳጳሱን ባሲሊካ ታሪክ በራሳቸው አንደበት ይናገራሉ።

"በድምፃቸው ሙቀት እና ጉጉት እንደ 'ምሥክሮች' ሆነው ይሠራሉ እና አራቱ ጳጳሳዊ ባሲሊካዎች ለሚወክሉት ሁሉ ያላቸውን ፍቅር ያጋራሉ" ሲል መግለጫው ገልጿል።

የኢንትርኔት የመተግበሪያው ገጽ በጠረጴዛው ምልክት ይመሰላል፣ በቅዱሳን እና በሰዓሊዎች ተሞልተው ህይወታቸው እና ጥበባቸው ቤተክርስቲያንን ቀርፀዋል።

መግለጫው “ጠረጴዛው ምግብ ብቻ ሳይሆን እይታዎች፣ ታሪኮች እና ልምዶች የሚካፈሉበት ቦታ ይሰጣል፣ ስለዚህም ጎብኚው ለአፍታ ቆም ብሎ እንዲያስብበት እና የተወሰነ ጊዜ እንዲወስድ ይጋብዛል።

የመንፈሳዊ ጉዞ ላይ እርምጃዎች

“ከቱሪስት ወደ መንፈሳዊ ተጓዥነት” ተነሳሽነቱ በመንፈሳዊ ጉዟቸው ወቅት - በአካልም ሆነ በመስመር ላይ - በባሲሊካ ታሪክ ውስጥ የሚያጅብ ፖድካስት መልክ ይይዛል፣ ይህም እጅግ በጣም አስፈላጊ ለሆኑ ገፅታዎቻቸው ልዩ ግንዛቤዎችን ይሰጣል።

የፖድካስት (MP3…etc) ተከታታይ ዝግጅቱ እ.አ.አ. በየካቲት 27 ይጀምራል፣ በእያንዳንዱ ማክሰኞ በሚለቀቀው አዲስ ክፍል እራሱን እያዘመነ እንዲሄድ ተደርጎ ተቀርጿል።

“ለቱሪስት የከተማ አደባባይ ብቻ የሚመስለው ነገር በመንፈሳዊ ተጓዥ ዐይን ከታየ ደረጃ፣ ጉዞ፣ መለኮታዊ ምልክት ይሆናል” ይላል መግለጫው። "እነዚህ አጫጭር ጉብኝቶች በመንፈሳዊ ጉዞ መነፅር የተገለጠውን የሮምን ድብቅ ውበት ለማጉላት የተነደፉ ናቸው" ሲል መግለጫው አክሎ አትቷል።

የር.ሊ.ጳ ባሲሊካ በዲጂታል ዓለም ውስጥ

"ከቱሪስት ወደ መንፈሳዊ ጉዞ" የተሰኘው የኢንትርኔት መተግበሪያ በቫቲካን የቅድስት መንበር የኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት የተዘጋጀ ሲሆን "የእምነት ግንኙነት በዲጂታል ዓለም" በሚል ርዕስ ወጣት የካቶሊክ ኮሚዩኒኬተሮችን ለማሰልጠን ታስቦ የተወለደ በፕሮጀክት ነው።

ከአስር ሀገራት የተውጣጡ 16 ወጣት ባለሙያዎች አራቱን የጳጳሳት ቤተክርስትያን ከባለሙያዎች ጋር ጎብኝተዋል፣ ለጉብኝት ምእመናን የሚያገለግሉት በወጣቶች ይን አዲስ እይታ እንዲኖራቸው ለመርዳት ታስቦ የተደርገ ነው።

የኢንትርኔት መተግበሪያው ልዩ ገጽ ከፖድካስት የልምዳቸውን ፍሬዎች በዲጂታል መልክ ይወክላሉ።

“አንዳንዶቻችን በሕይወታቸው ውስጥ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር እንኳ ተረድተናል። ጎብኚዎች ተመሳሳይ ልምድ እንዲኖራቸው እንፈልጋለን ነገር ግን በዲጂታል ዓለም ውስጥ። እምነታችን ከየት እንደመጣ መረዳት በቻልን መጠን የሰዎችን ልብ ለመንካት መልእክቱን በደንብ ማስተላለፍ እንችላለን።

 

23 February 2024, 13:22