ፈልግ

የአዲስ ቤተ ክርስቲያን አኃዛዊ መረጃዎች የካቶሊኮች ቁጥ መጨመር እና መንፈሳዊ ጥሪ መቀነሱን ያሳያል! የአዲስ ቤተ ክርስቲያን አኃዛዊ መረጃዎች የካቶሊኮች ቁጥ መጨመር እና መንፈሳዊ ጥሪ መቀነሱን ያሳያል!   (ANSA)

የአዲስ ቤተ ክርስቲያን አኃዛዊ መረጃዎች የካቶሊኮች ቁጥ መጨመር እና መንፈሳዊ ጥሪ መቀነሱን ያሳያል!

የቅድስት መንበር እ.አ.አ የ2024 ጳጳሳዊ ዓመታዊ መጽሐፍ እና እ.አ.አ የ2022 የቤተ ክርስቲያን እስታቲስቲካዊ በመረጃ የተደገፈ ዓመዊ መጽሐፍ በማሳተም በመላው ዓለም የሚገኙ የኤጲስ ቆጶሳትን፣ የካህናትን፣ የወንዶችንና የሴቶችን ገዳማዊያን እና ገዳማዊያትን፣ ዲያቆናትን በዝርዝር አስቀምጧል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በቫቲካን ማተሚያ ቤት የታተመው እ.አ.አ የ2024 ጳጳሳዊው በእየአመቱ የሚታተመው መጽሐፍ እና የ2022 የቤተ ክርስቲያን የስታቲስቲክስ በእየዓመቱ ይፋ የሚሆነው መጽሐፍ በቤተ ክርስቲያን ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ጽ/ቤት ተዘጋጅቶ በአሁኑ ጊዜ በመጽሃፍት መሸጫ መደብሮች እየተከፋፈለ ይገኛል።

ጳጳሳዊ በእየዓመቱ የሚታተመው መጽሐፍ እ.አ.አ ከታኅሣሥ 1/2022 እስከ ታኅሣሥ 31/2023 ዓ.ም ድረስ ያለውን ጊዜ ባካተተ መልኩ በዓለም ዙሪያ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን ሕይወት በተመለከተ መረጃ ይሰጣል።

በዚህ ጊዜ ውስጥ 9 አዲስ የጳጳሳት መንበር እና 1 ሐዋርያዊ አስተዳደር ተቋቁመዋል፣ 2 ኤጲስ ቆጶስ መንበር ወደ የመጀመሪያ ሀገረ ስብከት መንበር እና 1 ሐዋሪያዊ አስተዳደር ወደ ኤጲስ ቆጶስ መንበር ከፍ ተደርገዋል።

የቤተክርስቲያኗ የስታቲስቲክስ ዓመታዊ መጽሐፍ በዓለም ዙሪያ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንን ዝግመተ ለውጥ የሚመለከቱ ዋና ዋና አዝማሚያዎችን ለመገምገም በስታቲስቲካዊ መረጃ ተሞልቷል። እ.አ.አ በ2021 እና 2022 መካከል ባለው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አንዳንድ መሠረታዊ ገጽታዎች ላይ ጥቂቶቹ ጉልህ ዝርዝሮች እዚህ ይገኛሉ።

የቤተ ክርስቲያን ስታቲስቲክስ፡ ካቶሊካዊያን እና ጳጳሳት

እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም በዓለም አቀፍ ደረጃ የተጠመቁ ካቶሊካዊያን ቁጥር 1.376 ቢሊዮን የነበረ ሲሆን እ.አ.አ በ2022 ደግሞ ይህ አሃዝ ወደ 1.390 ቢሊዮን ከፍ ብሏል፣ በአንፃራዊነት 1.0 በመቶ ጨምሯል።

የለውጡ ፍጥነት ከአህጉር ወደ አህጉር ይለያያል። አፍሪካ የ3 በመቶ እድገት ያስመዘገበች ሲሆን በተመሳሳይ ጊዜ የካቶሊካዊያን ቁጥር ከ265 ወደ 273 ሚሊዮን ከፍ ብሏል። አውሮፓ የመረጋጋት ሁኔታን ያሳያል (እ.አ.አ በ 2021 እና 2022 የካቶሊካዊያን ምዕመናን  ቁጥር 286 ሚሊዮን ነበር)። አሜሪካ እና እስያ የካቶሊካዊያን ቁጥር (+ 0.9% እና + 0.6% በቅደም ተከተል) ከፍተኛ እድገት አስመዝግበዋል፣ ይህ አዝማሚያ ሙሉ በሙሉ ከእነዚህ ሁለት አህጉራት የስነ-ሕዝብ እድገት ጋር የሚስማማ ነው። ኦሺያኒያ የአህጉሩን እሴቶች በጠበቀ መልኩ  የቁጥር መረጋጋትን  እንዳለ ተዘግቧል።

እ.አ.አ በ2021-2022 በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ቁጥር በ0.25% ጨምሯል፣ ከ5,340 ወደ 5,353 የጳጳሳት ቁጥር ከፍ ብሏል። አብዛኛው ይህ እድገት በአፍሪካ እና በእስያ የተገኘ ሲሆን አንጻራዊ ልዩነት 2.1 እና 1.4 በመቶ ነው። በአሜሪካ አህጉር ከሚገኙ (ከ 2,000 ጳጳሳት ጋር) እና በኦሺንያ አህጉር ከሚገኙ (ከ 130 ጳጳስት ጋር) ሲነጻጸር የመረጋጋት ሁኔታ ታይቷል፣ በአውሮፓ ውስጥ ትንሽ መቀነስ (-0.6%) (በማሳየት ከ 1,676 እስከ 1,666) ዝቅ ማለቱ ተመዝግቧል።

ጥቂት ካህናት እና ተጨማሪ ቋሚ ዲያቆናት

እ.ኤ.አ. 2022 የካህናት ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የበለጠ ቀንሷል ፣ ይህም ከ 2012 ጀምሮ ያለውን የቁልቁለት አዝማሚያ ማሳየቱን ቀጥሏል። እ.ኤ.አ. በ 2022 በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የካህናት ብዛት እ.አ.አ ከ 2021 ጋር ሲነፃፀር ፣ በ 142 ካህናት ቀንሷል ፣ ከ 407,872 ወደ 407,730 መቀነሱ ተዘግቧል።

አፍሪካ እና እስያ ቀጣይነት ያለው ተለዋዋጭነት (+3.2% እና 1.6% በቅደም ተከተል) አሳይተዋል እና አሜሪካ ከሞላ ጎደል በተረጋጋ ሁኔታ ላይ እንዳለ አሃዙ ያሳያል። በጠቅላላው ትልቁ ክብደት ያለው አውሮፓ እና ኦሺኒያ እንደቅደም ተከተላቸው 1.7 እና 1.5 በመቶ አሉታዊ ልዩነት ተመዝግቧል።

የቋሚ ዲያቆናት ቁጥር ጉልህ የሆነ የዝግመተ ለውጥ ተለዋዋጭነትን ማሳየቱን ቀጥሏል።

እ.ኤ.አ. በ 2022 የዲያቆናት ቁጥር ከአንድ አመት በፊት ከነበረው የቁጥር አሃዝ በ 2% ጨምሯል ፣ ይህም ከ 49,176 ወደ 50,150 ዲያቆናት ደርሷል ። ቁጥሩ በሁሉም አህጉራት በከፍተኛ ፍጥነት ተሻሽሏል። በአፍሪካ፣ በእስያ እና በኦሺንያ ከጠቅላላው 3% መድረስ በመቻላቸው፣ የዲያቆናት ቁጥር በ1.1% ጨምሯል፣ በ2022 1,380 እድገት በማሳየት የቋሚ ዲያቆናት ቁጥር አሻቅቧል።

የቋሚ ዲያቆናት መኖር በቁጥር ጉልህ በሆነባቸው አካባቢዎችም መረጃው ተሻሽሏል። ከጠቅላላው ህዝብ 97.3% በሚኖሩባቸው አሜሪካ እና አውሮፓ፣ ዲያቆናት በ2.1 እና በ1.7 በመቶ ቁጥራቸው ጨምረዋል።

ቃለ ማሃላ የፈጸሙ ሴት ገዳማዊያን ከፍተኛ መጠን ያለው ቁጥር ነበራቸው።

እ.ኤ.አ. በ2022፣ በዓለም ዙሪያ ካሉት የካህናት ብዛት በ47 በመቶ በልጠዋል፣ ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ እያሽቆለቆለ ነው። በአለም አቀፍ ደረጃ እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም ከ608,958 በላይ የሚሆኑ ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሴት ገዳማዊያን ቁጥር እ.አ.አ በ2022 ወደ 599,228 በቁጥር በመቀነስ በአንጻራዊ ሁኔታ በ1.6 በመቶ ቅናሽ አሳይተዋል።

እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም ከ 81,832 ወደ 83,190 በ2022 ዓ.ም በማደግ በ1.7 በመቶ ጭማሪ ያሳየችው አፍሪካ ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሴት ገዳማዊያን ከፍተኛ እድገት ያስመዘገበች አህጉር ነበረች። እነሱም ደቡብ ምስራቅ እስያ በተከታይነት፣ ቃለ መሃላ የፈጸሙ ሴት ገደማዊያን እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም ከ171,756 እ.አ.አ በ2022 ዓ.ም ወደ 171,930 በ2022 ከፍ ብሏል፣ ይህም በ0.1% ብቻ ጭማሪ አሳይቷል። ደቡብ እና መካከለኛው አሜሪካ እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም ከ98,081 ቃለ መሃላ ከፈጸሙ ሴት ገድማዊያት እ.አ.አ በ2022 ወደ 95,590 በመሸጋገር፣ በአለም አቀፍ ደረጃ በ2.5% ቅናሽ አሳይተዋል። በመጨረሻም፣ ሶስት አህጉራዊ አካባቢዎች ጉልህ በሆነ ስበት   ተለይተው ይታወቃሉ፡ ኦሺኒያ (-3.6%)፣ አውሮፓ (-3.5%) እና ሰሜን አሜሪካ (-3.0%)።

የሴሚናሮች ቁጥር ቀንሷል

እ.አ.አ ከ2012 ጀምሮ የክህነት ጥሪዎች አዝማሚያ ያሳየው ማሽቆልቆል በየጊዜው ቀጥሏል።

እ.ኤ.አ. በ 2022 ለምስጢረ ክህነት ማዕረግ በዝግጅት ላይ የነበሩ የዐብይ ዘረዐ ክህነት ተማሪዎች በቁጥር 108,481 ነበሩ ፣ ይህም ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው ሁኔታ ጋር ሲነፃፀር በ -1.3% ልዩነት አሳይቷል። በክፍለ አህጉር ደረጃ የተደረገው ማጠቃለያ ትንታኔ እንደሚያሳየው የአካባቢ ባህሪያት እርስ በርስ ይለያሉ።

በአፍሪካ ውስጥ የዐብይ ዘረዐ ክህነት ተማሪዎች (የድህረ-ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የሚማሩ) ቁጥር በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ በ 2.1% ጨምሯል። በሁሉም የአሜሪካ አህጉራት፣ ለመንፈሳው ጥሪ የሚዘጋጁ የዐብይ ዘረዐ ክህነት ተማሪዎች ቁትር ቀንሷል፣ በዚህም ምክንያት የ -3.2% ልዩነት ያሳያል። በእስያ በ2022 ዓ.ም የዐብይ ዘረዐ ክህነት ተማሪዎች ቁጥር እ.አ.አ ከ2021 ዓ.ም በ1.2% ያነሰ የደረሰ ቅናሽ ተመዝግቧል።

እ.አ.አ ከ2008 ጀምሮ የአውሮፓ ለመንፈሳዊ ጥሪ የሚዘጋጁ ሰዎች ቁጥር እጅግ በጣም በቁጥር መቀነሱን ያለማቋረጥ ቀጥሏል፣ እ.ኤ.አ. በ 2021-2022 ውስጥ የዐብይ ዘረዐ ክህነት ተማሪዎች ቁጥር በ 6% ቀንሷል። በኦሺንያ እ.አ.አ በ2022 ዓ.ም የክህነት ጥሪዎች እ.አ.አ በ2021 ዓ.ም ከነበረው ቁጥር በ1.3 በመቶ በልጠዋል።

በዓለም ዙሪያ ካሉት 108,481 የዐብይ የዘረዐ ክህነት ተማሪዎች መካከል እ.አ.አ በ2022፣ አፍሪካ በ34,541 ወንድ ተማሪዎች ከፍተኛውን የዐብይ የዘረዐ ክህነት ተማሪዎች ቁጥር ያሳየች አህጉር ነበረች። በመቀጠልም እስያ በ31,767፣ አሜሪካ በ27,738፣ አውሮፓ በ14,461፣ እና ኦሺኒያ በ974 የዐብይ ዘረዐ ክህነት ተማሪዎች ቁጥር በቀደ ተከተል ተቀምጧል።

05 April 2024, 18:30