ፈልግ

ቫቲካን ከሌሎች ሀገራት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በዋናነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ጋላገር ቫቲካን ከሌሎች ሀገራት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በዋናነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ጋላገር  

ሊቀ ጳጳስ ጋልገር ክሮኤሺያን ጎበኙ

ቫቲካን ከሌሎች አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ በክሮኤሺያ የእመቤታችን የድንጋይ በር በዓልን ለማክበር ወደ እዚያው ማቅናታቸው የገለጸ ሲሆን በእዚያውም ከአገሪቷ ባለስልጣናት ጋር ለመገናኘት እና በክሮኤሺያ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ንግግር ለማድረግ ቀጠሮ ተይዞላቸዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ቫቲካን ከሌሎች አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ ​​ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር ሐሙስ ግንቦት 22/2016 ዓ.ም በክሮኤሺያ የሶስት ቀናት ጉብኝት ማድረግ መጀመራቸው ተገልጿል።

በዛግሬብ ሊቀ ጳጳስ ድራዤን ኩትላሻ የክሮኤሺያ ዋና ከተማ ደጋፊ ለሆነችው ለድንጋይ በር የእመቤታችን በዓል ተጋብዘዋል።

የጉዞ መስመር

በቀጠሮው መሰረት ሊቀ ጳጳስ ጋላገር ከጠቅላይ ሚኒስትር አንድሬጅ ፕሌንኮቪች እና የውጭ ጉዳይ እና የአውሮፓ ጉዳዮች ሚኒስትር ጎርዳን ግሪች-ራድማን ጋር ይገናኛሉ።

በክሮኤሺያ ካቶሊካዊ ዩኒቨርሲቲ ቤተመጻሕፍት ታላቅ መክፈቻ በዓል ላይም ይሳተፋሉ፣ በዚያም ንግግር ያደርጋሉ።

በመጨረሻም የክሮሺያ ጳጳሳት በተገኙበት በዛግሬብ ካቴድራል የእመቤታችን የድንጋዩ በር በዓል ላይ መስዋዕተ ቅዳሴ እንደሚያደርጉ የሚጠበቅ ሲሆን መስዋዕተ ቅዳሴውን ቫቲካን ከሌሎች አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና ፀሐፊ ​​ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር  እንደ ሚመሩትም ይጠበቃል።

በበዓሉ ላይ በሀገሪቱ እና በቅድስት መንበር መካከል ያለው ግንኙነት “በታሪክ ብዙ ግጭቶች ቢኖሩትም ጨርሶ አልቀዘቀዘም” ብለዋል።

በስብከተ ወንጌል ምእመናን በጦርነትና በግጭት ለሚሰቃዩ አገሮች ሁሉ እንዲጸልዩ የጋበዙ ሲሆን በክሮኤሺያ ስላለው “የነጻነትና የሰላም ስጦታ” አምላክን አመስግነዋል።

31 May 2024, 13:17