ሊቀ ጳጳስ ጋላገር የእስራኤልን 76ኛ የነጻነት አመትን ያስታውሳሉ
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ቫቲካን ከሌሎች አገራት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና ጸኃፊ ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር ሐሙስ ግንቦት 28/2016 ዓ.ም በቅድስት መንበር የእስራኤል ኤምባሲ የእስራኤልን 76ኛ የነጻነት በዓል በማክበር ንግግር አድርገዋል።
የእስራኤል መንግሥት መመሥረትና በዓለም አቀፍ ሕግ ማዕቀፍ ውስጥ ያለው ዕውቅና በቅድስት መንበር የተከበረ መሆኑን ደጋግመው ገልጸው ነበር - ይህ ደግሞ ሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በመመሥረታቸው ነው።
ከ30 ዓመታት በፊት እ.አ.አ ሰኔ 15/1994 ዓ.ም በእስራኤል የሚገኙ ሁለቱ የሐዋርያት ዲፕሎማሲያዊ ልዑካን እና የእስራኤል የቅድስት መንበር ኤምባሲ መመረቃቸውን አስታውሰዋል።
“የቅድስት መንበር ከእስራኤል ጋር ግንኙነት ለመመሥረት የጀመረችው የፖለቲካ ምርጫ በጥልቅ የጸና ነው” ያሉት ቫቲካን ከሌሎች አገራት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና ጸኃፊ ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር “ይህ ምርጫ የተነሣሣው የእስራኤል ህልውና ጥያቄ ውስጥ መግባት እስካልቻለ ድረስ የቅድስት መንበር የረዥም ጊዜ አቋም ለዘለቄታው ይቆያል በሚለው እምነት ነው። የሁለት ሀገር መፍትሄ" በተሰኘው መሰረት ነው ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
እ.አ.አ ጥቅምት 7 ቀን 2023
ሊቀ ጳጳስ ጋላገር እንዳሉት “ይህ እ.አ.አ በጥቅምት 7 ቀን ሃማስ እና ሌሎች ታጣቂዎች በእስራኤል ህዝብ ላይ ከደረሰው ዘግናኝ የሽብር ጥቃት በኋላ በመቶዎች የሚቆጠሩ አይሁዶች በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉበት፣ የተደፈሩበት እና በአረመኔያዊ መንገድ ታግተው ከተገደሉ በኋላ የበለጠ ግልጽ ሆኗል ያሉ ሲሆን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባለፈው ጥር ለዲፕሎማቲክ ልዑካን አባላት የተናገሩትን ቃል በማስተጋባት ድርጊቱን በማውገዝ እና በሁሉም የሽብርተኝነት እና የአክራሪነት ጉዳዮች ላይ የተናገሩት ቫቲካን ከሌሎች አገራት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና ጸኃፊ ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር "ሽብርተኝነት ለማንኛውም ግጭት መፍትሄ አይደለም" ሲሉ አረጋግጠዋል። "ለሰብአዊ ሕይወት ፍጹም የሆነ የንቀት ተግባር እና ምንም ዓይነት ተነሳሽነት ቢያንስ ከፖለቲካዊም ሆነ ከሃይማኖታዊ አካላት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም" ብለዋል።
ሊቀ ጳጳሱ በሙኒክ የጸጥታ ጉባኤ ላይ በጀርመን ከሚገኙ ታጋቾች ቤተሰቦች ጋር መገናኘታቸውን አስታውሰው፣ ሊቀ ጳጳስ ጋላገር፣ “ለተፈጠረው ነገር ያለኝን ርኅራኄና ሀዘን አድሳለሁ” ብለዋል።
“ስቃያቸው ብዙ ነው” በማለት በቁጭት ተናግሯል፣ “በየቀኑ ቁጥር እየጨመረ ነው፣ በተለይም ፈጣን መፍትሄዎች በሌሉበት ሁኔታ” ብለዋል።
የሊቀ ጳጳሱ ታጋቾች እንዲፈቱ ያቀረቡት ጥሪ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ታጋቾቹ በአስቸኳይ እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ጥሪ ማቅረባቸውን ብቻ ሳይሆን ዘመዶቻቸውን በቡድን እና በተናጠል በማግኘታቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ያላቸውን የማያቋርጥ ቅርበት አስታውሰዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተመሳሳይ በእስራኤል ውስጥ ላሉ የአይሁድ ማህበረሰቦች በፃፉት ደብዳቤ፣ ሐዘናቸውን እና ስቃያቸውን በመግለጽ እና ሁሉንም አይነት ፀረ ሴማዊነት በማውገዝ ያላቸውን ቅርበት ገልጿል።
የጥቅምት 7ቱ ጥቃት ሊቀ ጳጳስ ጋላገር እንዳሉት ከሆነ በጋዛ ከባድ የእስራኤል ወታደራዊ ምላሽ እንደቀሰቀሰ፣ ይህም ተከትሎም ከሊባኖስ፣ ከየመን እና ከሌሎችም በመጡ ብዙ የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት በእስራኤል ላይ ተጨማሪ ወታደራዊ ጥቃት አድርሷል።
"በተለያዩ አጋጣሚዎች" አንዳንድ ድርጊቶች ሁኔታውን በክልል ደረጃ በጣም አደገኛ ወደሆነ ግጭት አመራርተዋል" ብለዋል።
ሶስት ፍላጎቶች፡ የተኩስ አቁም፣ ታጋቾችን መልቀቅ፣ ሰብአዊ እርዳታ
“በእነዚህ አስቸጋሪ እና ውስብስብ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ቅዱስ አባታችን ፍራንችስኮስ ሦስት ግልጽ ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡ በሁሉም አቅጣጫ የተኩስ አቁም፣ ሁሉም የእስራኤል ታጋቾች በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ እና ለተጎዱት ሰብዓዊ ርዳታዎች ያለ ምንም እንቅፋት እንዲደርስ ጥሪ አድርገዋል። የፍልስጤም ህዝብ አስፈላጊው ርዳታ እንዲደርሰውም ጥሪ አቅርበዋል።
"የሰብአዊነት መሰረታዊ መርህ በወታደራዊ ስልቶች ፈጽሞ መተው ወይም መሸፈን የለበትም" ምክንያቱም "አለበለዚያ የአስፈላጊነት እና ተመጣጣኝነት መርሆዎች መበላሸታቸው የማይቀር ነው" ያሉት ቫቲካን ከሌሎች አገራት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና ጸኃፊ ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር በግጭቶች ውስጥ "ቅድስት መንበር የገለልተኝነት መርሆዎችን ማክበር አለባት" ብለዋል። ይህ “በሥነ ምግባር ግድየለሽ መሆን ማለት አይደለም” ሲሉ ገልጿል፣ “ቅድስት መንበር ለማንም በሯን አትዘጋም እና የሁሉንም ሰው ተነሳሽነት እና አመለካከቶች ለመረዳት ትጥራለች ብለዋል።
የ 30 ዓመታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት
በመቀጠልም በቅድስት መንበር እና በእስራኤል መካከል ላለፉት ሰላሳ ዓመታት የዘለቀው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መሻሻል እና ተግዳሮቶች መታየታቸውንና በተቻላቸው መጠን ለመተባበር ፍቃደኛ መሆናቸውን በተለይም በቅድስት መንበር እና በእስራኤል መካከል ባሉ በርካታ የትብብር ዘርፎች ታይቷል ብለዋል።
ለአብነት ያህል፣ ከአሥር ዓመታት በፊት በቫቲካን የአትክልት ሥፍራ የተካሄደውን እና የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጳጳሳትን በእስራኤል ያደረጉትን ጉብኝት “ቅርብ እና ጥልቅ የሆነ መተዋወቅን ማፋጠን” በማለት ነው ሲሉ ጠቅሰዋል። በመቀጠልም የእስራኤል ፕሬዝዳንት ሺሞን ፔሬዝ፣ የፍልስጤም ፕሬዝዳንት መሀሙድ አባስ እና የኢኩሜኒካል ፓትርያርክ ቁስጥንጥንያ በርተሎሜዎስ ቀዳማዊ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በመሆን ያደረጉትን ግንኙነት አስታውሰዋል።
ታላቅ የሰላም ፍላጎት
ይህም ሊቀ ጳጳስ ጋልገር “ተስፋ ይሰጠናል እና ውይይት እና መግባባት እንደሚቻል ያስታውሰናል” ብለዋል። ለሰላም ትልቅ ፍላጎት አለ፣ እሱም "በእስራኤል ውስጥ በተቻለ ፍጥነት ቶሎ ቶሎ መድረስ ይቻላል!" ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ ለ2025 ዓ.ም ኢዮቤልዩ ‘ኢንዲክሽን’ በሚል ርዕስ ባሰፈሩት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰላም አስፈላጊነት ሁላችንም ተጨባጭ እርምጃዎችን እንድንወስድ ይሞግተናል በማለት ለእስራኤል መንግሥት ያላቸውን ምኞትና ተስፋ ተመሳሳይ ነው ሲሉ የቫቲካን ዲፕሎማት አጠቃለዋል። "ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ያለመ ድርድር ለማካሄድ ያለውን እድል ሁሉ ለመፈለግ አትታክቱ” "ሰላም፣ ሰላም፣ ሰላም!" ካሉ በኋላ ቫቲካን ከሌሎች አገራት እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚቆጣጠረው የቅድስት መንበር ጽሕፈት ቤት ዋና ጸኃፊ ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር ንግግራቸውን አጠናቀዋል።