ፈልግ

የቫቲካን የአትሌቲክስ ቡድን የቫቲካን የአትሌቲክስ ቡድን  

የቫቲካን የአትሌቲክስ ቡድን የኦሎምፒክ ተወዳዳሪ አትሌቶች ያላቸውን ታላቅ ኃላፊነት ያስታውሳል!

የቫቲካን የአትሌቲክስ ቡድን እ.አ.አ በፓሪስ ከሚካሄደው የ2024 ዓ.ም የበጋ ኦሊምፒክ የመክፈቻ ስነ ስርዓት በፊት አትሌቶች በወንድማማችነት ወዳጅነት ላይ እንዲያተኩሩ ያበረታታል፣ እናም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለኦሎምፒክ ውድድር ተሳታፊዎች ያቀረቡትን ጥሪ በድጋሚ አስተጋብቷል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"ኦሎምፒክ እና ፓራሊምፒክስ ለሰላም ስልቶች እና እንደ ጨዋታ ለተቆጠረው ጦርነት መከላከያ ሊሆኑ ይችላሉ" በማለት የአትሌቲክስ ቡድኑ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን የቅድስት መንበር የስፖርት ማኅበር አትሌቲካ ቫቲካና በፓሪስ እ.አ.አ በ2024 ዓ.ም የበጋ ኦሊምፒክ ለሚሳተፉ አትሌቶች በላከው ግልጽ ደብዳቤ ያስተላለፈው መልእክት ነው።

ማህበሩ በኦሎምፒክ የመክፈቻ ስነ ስርዓት ላይ ባሳተመው ፅሁፍ አትሌቶቹ በወንድማማችነት እና በመቀራረብ በፍትሃዊ ጨዋታቸው እና በስኬታቸው እንዲራመዱ ያበረታታል።

አትሌቲካ ቫቲካን “በእያንዳንዱ ሰው የስፖርት እንቅስቃሴ ውበት፣ ፍትሃዊነት እና አቋራጭ መንገዶችን ሳይጠቀሙ ጨዋታው የተስፋ እድሎች ሊሆኑ ይችላሉ” ብለዋል ።

የኦሎምፒክ የበጋ ውድድር

አትሌቲካ ቫቲካና የዚህ አመት ኦሊምፒክ በጦርነት፣ ውጥረት እና ኢፍትሃዊነት በሰፈነበት መልኩ በአለም አቀፍ ደረጃ እንደሚካሄድ በመግለጽ ይህ "ለሰብአዊነት የጨለማ ጊዜ ነው" ሲል ነቅፏል። ማህበሩ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን በኦሎምፒክ ውድድር ወቅት የሚካሄዱት ጦርነቶች ሁሉ እንዲቆሙ የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደረግ ያቀረቡትን አቤቱታ በድጋሚ ገልጿል።

ሰላምን ለማስፈን የሚደረጉ ጥረቶችን ለመቀበል ለኦሎፒክ ስፖርት ተካፋዮች ጥሪ ያቀረበው ማኅበሩ፣ አትሌቶቹ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “የሦስተኛው የዓለም ጦርነት የተፋፋመበት” በማለት የገለጹትን ጦርነት ማቆም ባይችሉም ወንድማማችነት ያለው የሰው ልጅ ማፍራት እንደሚችሉ ጠቁሟል።

ታዋቂው እና ለመረዳት የሚቻል የስፖርት ቋንቋ እና እሴቶቹ አትሌቲካ ቫቲካና ሁሉም ለዚህ አላማ አስተዋፅኦ አድርገዋል።

"የህይወት ማራቶን"

"እያንዳንዱ የስልጠና ክፍለ ጊዜ፣ እያንዳንዱ የተሸነፈ ፈተና፣ እያንዳንዱ የችግር ጊዜ ድፍረት ያጋጠመን እኛ ወደ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ያመጣችሁ ድል ወይም ሽንፈት ብቻ ሳይሆን ብቻውን የማይደረግ የህይወት ጉዞ ነው" ሲል መልእክቱ አክሎ ይገልጻል።

አትሌቲካ ቫቲካና ያቀረበው መልእክት ሁሉንም የኦሎምፒክ አትሌቶች በአንድነት "የወንድማማችነት ሜዳሊያ" እንዲያሸንፉ በመጋበዝ ስፖርታዊ ወዳጅነትን እና ምስጋናን በማቃበል ተጠናቋል።

26 July 2024, 11:05