ፈልግ

በኒው ዮርክ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ዋና መሥሪያ ቤት በኒው ዮርክ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ዋና መሥሪያ ቤት  (ANSA)

ቅድስት መንበር፡- ባለጸጋ አገሮች የደሴት አገሮችን በእዳ እፎይታ መርዳት ይችላሉ ማለቷ ተገለጸ።

በተባበሩት መንግስታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ ጋብሪኤሌ ካቺያ የአለም ማህበረሰብ የእዳ ስረዛ እና የእዳ እፎይታ ሊያካትት በሚችል ተጨባጭ ጥረት ትንንሽ የደሴት ላይ አገሮች እና በማደግ ላይ ያሉ ሀገራትን እንዲያግዙ አሳስበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"የእኔ ልዑካን ሁሉም አባል ሀገራት በልዩ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሀገራትን በተጨባጭ እርምጃ እና በተሻሻለ ትብብር ዘላቂ ልማት ለማምጣት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያረጋግጡ ጥሪውን ያቀርባል" ሲሉ ሊቀ ጳጳስ ገብርኤሌ ካቺያ ተናግረዋል።

በተባበሩት መንግስታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ ገብርኤሌ ካቺያ ረቡዕ ዕለት በኒውዮርክ በተካሄደው “ትንንሽ በማደግ ላይ ያሉ የደሴት ሀገራት፡ የአራተኛው የSIDS (በትናንሽ ደሴት ታዳጊ ሀገራት ላይ የሚደርገው አለምአቀፍ ኮንፈረንስ) “የኮንፈረንስ ውጤቶችን ተግባራዊ ማድረግ” በሚል ርዕስ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር ላይ ያቀረቡት አቤቱታ ይህ ነበር። የበለጸጉ አገራት ዕዳን ለማስወገድ ወይም የተጎዳውን SIDS አገራት ዕዳ እንዲሰረዙ አሳስቧል።

ስብሰባው በኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ምክር ቤት (እ.አ.አ ከሐምሌ 8-17/2024 ዓ.ም) አስተባባሪነት በተጠራው የ2024 ዓ.ም ከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ መድረክ (HLPF) እየተካሄደ ነው። የመድረኩ መሪ ቃል "የ2030 አጀንዳን ማጠናከር እና በተለያዩ ቀውሶች ውስጥ የሚገኙትን ድህነትን ማጥፋት፡ ዘላቂ፣ ተቋቋሚ እና አዳዲስ መፍትሄዎችን ውጤታማ ማድረግ" የተሰኘው ነው።

አለም አቀፉ ማህበረሰብ ሃላፊነት አለበት።

ሊቀ ጳጳስ ካቺያ በዚህ ግንባር ላይ የታደሰ ቁርጠኝነት እንዲኖረን በማሳሰብ ነበር ንግግራቸውን የጀመሩት።

"የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደ 'የሀገሮች ቤተሰብ' በተለየ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ሀገራት (በትናንሽ ደሴት ታዳጊ ሀገራት ላይ የሚደርገው አለምአቀፍ ኮንፈረንስ) ጨምሮ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የሚያደርጉትን ጥረት የመርዳት ሃላፊነት እንዳለበት ግልፅ ነው" ብለዋል።

ቀጣይነት ያለው የልማት ግቦችን ለማሳካት የሚፈለገው እድገት የሚደናቀፈው በልዩ ሁኔታ ውስጥ ባሉ ሀገራት የሚገጥሟቸው ፈተናዎች ማለትም በዕዳ መሽመድመድ፣ የእድገት ዝግመት፣ የማያቋርጥ የምግብ ዋስትና እና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ተጋላጭነት የሚያመጣ በመሆኑ የቅድስት መንበር “ትልቅ ስጋት” እንደ ሆነባት ገልጸዋል፣ የተፈጥሮ አደጋዎችን ጨምሮ ሲሉ አክለው ተናግረዋል።  

ይህንን አዝማሚያ ለመዋጋት እ.አ.አ የ2030 ዓ.ም አጀንዳው “ወደ ኋላ ለቀሩት አገራት ቅድሚያ የመስጠት ቁርጠኝነትን እንደሚያካትት” የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ምልከታ “እኛ በምንጥርበት ጊዜ ለሌሎች ደካማነት ተጠያቂው እኛው ነን፣ የጋራ የወደፊት ጊዜን የመገንባት ኃላፊነት አለብን” ሲሉ መናገራቸውን አስታውሰዋል።

የልማት ፍላጎቶችን እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለመፍታት አስፈላጊ ነው

"ስለዚህም" ሊቀ ጳጳስ ካቺያ ተማጽነዋል፣ "በተለየ ሁኔታ ውስጥ ያሉ አገሮች ልዩ የልማት ፍላጎቶች እና ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች በትክክል መስተካከል አለባቸው፣ ይህ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሞራል ግዴታ ነው" ብለዋል።

"ይህ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሞራል ግዴታ ስለሆነ በልዩ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሀገራት ልዩ የልማት ፍላጎቶች እና ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች በትክክል መስተካከል አለባቸው" ብለዋል።

በዚህ አውድ ውስጥ፣ አገሮች የህዝቦቻቸውን ፍላጎት በሚፈታ የለውጥ ፕሮግራሞች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ የሚያስፈልገውን የገንዘብ አያያዝ ሁኔታ ለSIDS (በትናንሽ ደሴት ታዳጊ ሀገራት ላይ የሚደርገው አለምአቀፍ ኮንፈረንስ)እንዲያቀርቡ የሚጠይቀውን አንቲጓ እና ባርቡዳ አጀንዳ ለ SIDS (ABAS) መቀበሉን አድንቀዋል። በSIDS ያጋጠሟቸው ልዩ ተጋላጭነቶች እና እንደገና የሚቋቋም ብልጽግናን ለማሳደድ እነርሱን ለመደገፍ ቃል መግባት ይኖርበታል ብለዋል።

የዕዳ ሸክም መጫን ዘላቂ መፍትኤ አያመጣም

ሆኖም፣ “በብዙ SIDS (በትናንሽ ደሴት ታዳጊ ሀገራት ላይ የሚደርገው አለምአቀፍ ኮንፈረንስ) እየጨመረ ያለው የእዳ ሸክም ዘላቂነት የሌለው እየሆነ መጥቷል፣ እናም ትግበራው ገና ከመጀመሩ በፊት አደጋ ላይ ይጥላል” ሲሉ አስጠንቅቋል።

አሁን ያሉት የዕዳ ግዴታዎች ሊቀ ጳጳስ ካቺያ እንዳሉት ከሆነ "ድህነትን ማስወገድ እና የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ በጣም አሳሳቢ ጉዳዮችን ለመፍታት አቅማቸውን በሚያደናቅፍ በጥገኝነት ዑደት ውስጥ SIDSን (በትናንሽ ደሴት ታዳጊ ሀገራት ላይ የሚደርገው አለምአቀፍ ኮንፈረንስ) ያጠምዳሉ" ሲሉ የተናገሩ ሲሆን አላማው የSIDSን የማይበገር ብልጽግና ማመቻቸት ከሆነ "በጤና አጠባበቅ፣ በትምህርት እና በማህበራዊ ጥበቃ ስርዓቶች ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ለበጀት ቦታን መስጠት አስፈላጊ ነው" ሲሉ አሳስበዋል።

የእዳ እፎይታ ወይም መሰረዝን ግምት ውስጥ ማስገባት

ሊቀ ጳጳስ ካቺያ ቅድስት መንበር “የበለጸጉት መንግሥታት የዕዳ ስረዛን ወይም የዕዳ እፎይታ እንዲያጤኑ በድጋሚ ጥሪዋን ታቀርባለች” ያሉ ሲሆን “የእኔ ልዑካን ቡድን የበለፀጉ አገሮች ዕዳን ለማስወገድ ወይም በእርግጥ ዕዳ መሰረዝን እንዲያስቡ በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል። እንዲህ ዓይነቱ ሥር ነቀል፥ ነገር ግን አስፈላጊው እርምጃ SIDSን (በትናንሽ ደሴት ታዳጊ ሀገራት ላይ የሚደርገው አለምአቀፍ ኮንፈረንስ) የወለድ ክፍያዎችን በአገልግሎት መስክ ወይም በጤና፣ በትምህርት፣ በማህበራዊ ጥበቃ ሥርዓቶች እና በመሠረተ ልማት ላይ ለመዋዕለ ንዋይ ለማፍሰስ ግብዓቶችን በመመደብ መካከል ካለው የማይጸና ምርጫ ነፃ ያደርገዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

ሊቀ ጳጳስ ካቺያ ሁሉም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት ቁርጠኝነታቸውን እንዲያረጋግጡ ጥሪ በማድረግ አጠቃለዋል።

ቋሚ ታዛቢው "ለSIDS (በትናንሽ ደሴት ታዳጊ ሀገራት ላይ የሚደርገው አለምአቀፍ ኮንፈረንስ) እና በእዳ ስረዛ ወይም እፎይታ ለመላው የሀገራት ቤተሰብ ዘላቂ እና የበለፀገ የወደፊት ግንባታ ሊሳካ የሚችለው በጋራ ጥረቶች እና በጋራ ሃላፊነት ብቻ ነው" ሲል አረጋግጧል።

 

12 July 2024, 16:42