ፈልግ

ተጽዕኖ ፈጣሪ ካቶሊኮች በፖርቱጋል በሊዝቦን ተጽዕኖ ፈጣሪ ካቶሊኮች በፖርቱጋል በሊዝቦን  

ወደ ዲጂታል ሚስዮናውነት እና የካቶሊክ ተፅእኖ ፈጣሪዎች በኢዮቤልዩ መንገድ ላይ!

ለዲጂታል ሚስዮናውያን እና ለካቶሊክ ተጽእኖ ፈጣሪዎች በሮም የሚካሄደው የኢዮቤልዩ ዝግጅት በማህበራዊ ሚዲያዎች ወንጌልን በማስፋፋት ላይ ያተኩራል እና በቤተክርስቲያን ውስጥ የማህበረሰብ እና የተልእኮ ስሜትን ለማሳደግ ይፈልጋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢኢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ከአንድ አመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሮም ከአለም ዙሪያ ዲጂታል ሚስዮናውያን እና የካቶሊክ ተጽእኖ ፈጣሪዎችን የሚሰበስብ የኢዮቤልዩ ዝግጅት ታስተናግዳለች።

እ.ኤ.አ. በሐምሌ 28 እና 29/2024 ዓ.ም የወጣቶች ኢዮቤልዩ ከመከበሩ ጥቂት ቀደም ብሎ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ለወንጌል አገልግሎት የተሰጡ ሐዋርያዊ አገልጋዮች ለራሳቸው ኢዮቤልዩ ይሰበሰባሉ። ይህ እ.ኤ.አ. በ2023 በሊዝበን የአለም ወጣቶች ቀን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለተገናኙት ወጣቶች በድጋሚ የሚገናኙበትን መድረክ ይፈጥራል።

በዚያ ዝግጅት ላይ በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረውና የባህልና ትምህርት ጉዳዮችን በበላይነት የሚቆጣጠረው ጽሕፈት ቤት ዋና ጸኃፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ሆሴ ቶለንቲኖ ደ ሜንዶንካ ለወጣቶች ተጽእኖ ፈጣሪዎች በስብከታቸው ንግግር ያደረጉ ሲሆን “ዛሬ ቤተ ክርስቲያኒቱ እናንተን የተወደዳችሁ የዲጂታል ተጽእኖ ፈጣሪዎች ወደ እነዚህ አዳዲስ ማኅበራዊ ቦታዎች ለመምጣት ተስፋ እንድታደርጉ ትፈልጋላች።  ማህበራዊ ሚዲያ እና ማህበራዊ አውታረ መረቦች ተደራሽነታቸው እጅግ ከፍተኛ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

የቤተክርስቲያኗ ሚስዮናዊ ሕይወት አካል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዲጂታል ሚስዮናውያን እራሳቸውን እንደ ማህበረሰብ እንዲመለከቱ አበረታቷቸዋል "የቤተክርስቲያኗ ሚስዮናዊ ህይወት አካል፣ ወደ አዲስ አድማስ እና ድንበሮች ለመግባት ፈጽሞ አይፈራም። በፈጠራ እና በድፍረት" የእግዚአብሔርን ምህረት አውጁ” ማለታቸውን አስታውሰዋል።

ይህ ኢዮቤልዩ በዲጂታል ሚስዮናውያን መካከል የማህበረሰቡን እና የመግባቢያ ስሜትን ለማዳበር ያለመ ነው። በጋራ ተልእኮ ለተባበሩት የሚሲዮናውያን ማኅበረሰብ በኢዮቤልዩ ዓመት በቅዱስ በር ስር እንዲሰበሰብና በእዚህ የቅዱስ በር ሥር እንዲያልፍ ዕድል ይፈጥራል ሲሉ ተናግረዋል።

የዲጂታል ሚሲዮኖች የመጀመሪያ ስብሰባ

በሐምሌ 13/2016 ዓ.ም በአፓሬሲዳ በብራዚል የመጀመሪያውን የዲጂታል ሚሲዮናውያን ብሔራዊ ስብሰባ ይስተናገዳል።

ይህ ክስተት በብራዚል ጳጳሳት ጉባኤ፣ በጳጳሳት ጉባኤ የማህበራዊ ግንኙነት ኮሚሽን (ሴፓክ)፣ ከወጣቶች ኤጲስ ቆጶስ ኮሚሽን፣ ሳንታ ካሮና፣ ኢግሬጄሮስ፣ ሶል ሻይን ብራንዲንግ፣ ፓስኮም ብራዚል እና ጆቨንስ ኮንክታዶስ ጋር በመተባበር ያስተዋውቃል።

በሉቃስ ወንጌል አነሳሽነት "መረቡን ጣሉ" በሚል መሪ ቃል ስብሰባው ከጠዋቱ 9 ሰዓት እስከ ምሽቱ 6 ሰዓት ድረስ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በዲጂታል ግዛት ውስጥ ሲኖዶሳዊነትን መቀበል

 “በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ልዩ ጊዜ እየኖርን ነው፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሲኖዶሳዊነትን እንድንኖር እያሳሰቡን ነው። በመካከላችን ኅብረት በመፍጠር አንድነትን በክርስቶስ ኢየሱስ እንፈልግ” ማለታቸውን ያስታወሱት በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረውና የባህልና ትምህርት ጉዳዮችን በበላይነት የሚቆጣጠረው ጽሕፈት ቤት ዋና ጸኃፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ሆሴ ቶለንቲኖ ደ ሜንዶንካ የዛሬው የዲጂታል መልክዓ ምድር የእግዚአብሔርን ቃል ለማሰራጨት እና መንግሥቱን ለመገንባት ልዩ እድል እንደሚሰጥ በመጥቀስ ሰዎች ከግዴለሽነት እና ግድየለሽነት ወጥተው የኢየሱስ ክርስቶስን እና የወንጌልን ድንቅ ነገር እንደገና እንዲያውቁ አሳስቧል።

የካቶሊክ ተጽእኖ ፈጣሪዎች እና በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ የሚያደርጉት ውይይት

በስብሰባው ላይ አባ ሉሲዮ አድሪያን ሩዪዝ የቅድስት መንበር ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጸሐፊ ከሌሎች የሴፓክ ጳጳሳት እና ከወጣቶች ኮሚሽን ጋር ይሳተፋሉ። በዲጂታል የወንጌል ስርጭት ላይ ያለውን ቁርጠኝነት ለማጠናከር ውይይት ያደርጋሉ።

የ CNBB የማህበራዊ ግንኙነት ኮሚሽን አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ዲጂታል ሚሲዮናውያንን ወደዚህ የመጀመሪያ ስብሰባ ጋብዟል፣ ነገር ግን በዲጂታል ቦታ ላይ የተሳትፎ እና የተልዕኮ ጥረቶች ለመጨመር የወደፊት ስብሰባዎችን ለማስፋት አቅዷል።

ዝግጅቱ ማስተዋልን እና ሲኖዶሳዊነትን የሚያጎላ በመንፈስ ቅዱስ የንግግር ዘዴ በመጠቀም ውይይት፣ መደማመጥ፣ ተሳትፎ እና ክብ ጠረጴዛዎችን ያካትታል።

በተሳታፊዎች መካከል እምነትን እና መግባባትን ለማጠናከር እድል የሚሰጥ የመንፈሳዊነት፣ የጸሎት እና የመስዋዕተ ቅዳሴ ጊዜዎችም ይኖራሉ ተብሏል።

 

12 July 2024, 16:45