ፈልግ

ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን በዩክሬን ሐዋርያዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን በዩክሬን ሐዋርያዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ  

ብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን በዩክሬን ሐዋርያዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ተገለጸ

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በዩክሬን ከሐምሌ 12-17/2016 ዓ. ም. ድረስ የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት ጀምረዋል። ብጹዕነታቸው በሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ማጠቃለያ ላይ በዩክሬን የላቲን ሥርዓተ አምልኮን ከሚከተሉት ካቶሊክ ምዕመናን ጋር በበርዲቺቭ የእመቤታችን ማርያም ቤተ መቅደስ ውስጥ መስዋዕተ ቅዳሴን እንደሚያሳርጉ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ከሐምሌ 12/2016 ዓ. ም. ጀምሮ በዩክሬን ሐዋርያዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ወደ ዩክሬን የተጓዙት በዩክሬን የላቲን ሥርዓት የሚከተሉ ካቶሊክ ምዕመናን ወደ በርዲቺቭ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ መቅደስ የሚያደርጉት መንፈሳዊ ጉዙ ማጠቃለያ መስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ለመመራት እንደሆነ ታውቋል።

ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረችበት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ምሥራቅ አውሮፓ አገር የተጓዙት የብጹዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ሐዋርያዊ ጉብኝት ሐምሌ 17/2016 ዓ. ም. እንደሚጠናቀቅ የጉብኝታቸው መርሃ ግብር አመልክቷል። ብጹዕነታቸው በእነዚህ ቀናት ውስጥ የሚያከናውኗቸው ተግባራት እና የሚሳተፉባቸው ዝግጅቶች እንዳሏቸው አክሎ አስታውቋል።

በበርዲቺቭ ቤተ መቅደስ የሚቀርብ ጸሎት
ዓርብ ሐምሌ 12/2016 ዓ. ም. በዩክሬን ሊቪቭ ከተማ የሚገኘውን የብጹዓን ጳጳሳት ጽሕፈት ቤት
የጎበኙት ብጹ ዕ ካርዲናል ፓሮሊን ቀጥለውም ኦዴሳን ጎብኝተዋል።

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ዩክሬን ውስጥ የሚገኙ የላቲን ሥርዓት ተከታይ ካቶሊክ ምዕመናን ወደ በርዲቺቭ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ መቅደስ የሚያደርጉት መንፈሳዊ ጉዙ ማጠቃለያን በማስመልከት እሑድ ሐምሌ 14/2016 ዓ. ም. የሚቀርበውን መስዋዕተ ቅዳሴ እንደሚመሩ ታውቋል።

ቤተ መቅደሱ ከኪየቭ በስተ ምዕራብ በኩል በሚገኝ በዛይቶሚር አውራጃ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፥ ከመላው ዩክሬን እና ከሌሎች አገራት ለሚመጡት ካቶሊክ ምዕመናን የመንፈሳዊ ጉዞአቸው መዳረሻ እንደሆነ ይታወቃል። የአገሪቱ ምዕመናን በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሰላም አማላጅነትን በጸሎት ጠይቀዋል።

ብጹዕነታቸው ከባለሥልጣናት ጋርም ይገናኛሉ
ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በመጪዎቹ ቀናት በኪየቭ የሚገኘውን የግሪክ-ካቶሊክ ካቴድራል እንደሚጎበኙ እና በተጨማሪም ከዩክሬን የግሪክ-ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ከሆኑት ከብጹዕ አቡነ ስቪያቶላቭ ሼቭቹክ ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ መያዛቸው ታውቋል።

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ሐዋርያዊ ጉብኝት መርሃ ግብር ከዩክሬን ሲቪል እና የሃይማኖት መሪዎች ጋር የሚያደርጉትን ስብሰባን የሚያካትት ሲሆን፥ ብፁዕነታቸው ቀደም ሲል በሰኔ 2008 እና በነሐሴ 2013 ዓ. ም. ዩክሬንን መጎብኘታቸው ይታወሳል።

 

 

20 July 2024, 16:01