ፈልግ

Cookie Policy
The portal Vatican News uses technical or similar cookies to make navigation easier and guarantee the use of the services. Furthermore, technical and analysis cookies from third parties may be used. If you want to know more click here. By closing this banner you consent to the use of cookies.
I AGREE
የቅዱስ ጴጥሮስ የዕርዳታ ማሰባሰብ መርሃ ግብር የቅዱስ ጴጥሮስ የዕርዳታ ማሰባሰብ መርሃ ግብር  

ለር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የዕርዳታ ተልዕኮ የሚደረግ የልገሳ መጠን መጨመሩ ተገለጸ

የቅዱስ ጴጥሮስ የዕርዳታ ማሰባሰብ መርሃ ግብር የጎርጎሮሳውያኑ 2023 የፋይናንስ ሪፖርት ይፋ አደረገ። ዓመታዊ ሪፖርቱ ለር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የዕርዳታ ተልዕኮ የተሰበሰበው የገንዘብ መጠን ከ2022 ዓ. ም. ጋር ሲነጻጸር በአምስት ሚሊዮን ዩሮ ከፍ ማለቱን አስታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2023 ዓ. ም. የተሰበሰበው የቅዱስ ጴጥሮስ የዕርዳታ ገንዘብ የካቶሊካዊ ቤተ ክርስቲያን ፍላጎቶች ለማሟላት እና የተቸገሩትን ለመርዳት የሚደረጉ በርካታ ተነሳሽነቶችን ለመደገፍ የታሰበው የገቢ መጠን 52 ሚሊዮን ዩሮ ሲሆን ጠቅላላው የወጪ መጠንም በድምሩ 109.4 ሚሊዮን ዩሮ መድረሱን ሪፖርቱ አመላክቷልል።

አሜሪካ ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ አድርጋለች
ለቅዱስ ጴጥሮስ የዕርዳታ መርሃ ግብር የተሰበሰበው የገንዘብ ልገሳ በሦስት ዋና ዋና መንገዶች ሲሆን፥የመጀመሪያው በቅዱሳን ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ዕለት በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ካቶሊካዊ ሰበካዎች፣ በጣሊያን ሀገረ ስብከቶች እና ጳጳሳዊ ውክልና ባላቸው አህጉረ ስብከቶች አማካይነት ለቅድስት መንበር የደረሱ የገንዘብ ልገሳዎች እንደሆኑ ታውቋል።

ሁለተኛው የዕርዳታ ማሰባሰቢያ መንገድ በባንክ፣ በፖስታ ቤቶች እና በሌሎች የገንዘብ መክፈያ መስመሮች በኩል በቀጥታ የሚላኩ የገንዘብ ልገሳዎች ሲሆኑ፥ ሦስተኛው ምዕመናን እና በጎ ፈቃድ ያላቸው ግለሰቦች በገቡት ቃል በኩል የተገኙ ልገሳዎች እንደሆነ ታውቋል።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2023 ዓ. ም. ካቶሊካዊ ሀገረ ስብከቶች 31.2 ሚሊዮን ዩሮ ያዋጡ ሲሆን፥ ይህም ከ64.4 በመቶ ውስጥ 4.4% ወይም 2.1 ሚሊዮን ዩሮ ከግል ለጋሾች የተገኘ ሲሆን፥ በተጨማሪም ከተለያዩ ፋውንዴሽን ከተገኘው የ13.9 ሚሊዮን ዩሮ ጋር 1.2 ሚሊዮን ዩሮ ከልዩ ልዩ ገዳማውያን እና ገዳማውያት የተላከ እንደሆነ ታውቋል።

ከጠቅላላው ገቢው መካከል አሜሪካ 13.6 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 28.1 ከመቶ ያዋጣች ሲሆን፥ ጣሊያን 3.1 ሚሊዮን ዩሮ፣ ብራዚል € 3.1 ሚሊዮን ዩሮን በማዋጣት ትልቁን ደረጃ መያዛቸው ተገልጿል።

በ 76 አገሮች ውስጥ የሚገኙ 236 ፕሮጀክቶችን በገንዘብ መደገፍ
እንደ ጎሮጎሮሳውያኑ በ2023 ዓ. ም. ለፕሮጀክቶች ማስከጃ ከተከፋፈለው 103 ሚሊዮን ዩሮ የቅዱስ ጴጥሮስ የዕርዳታ ፈንድ መካከል 90 ሚሊዮን ዩሮ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ ተልዕኮ ለማስፈጸም ቅድስት መንበር ለምታከናውናቸው ተግባራት የዋለ ሲሆን፥ 13 ሚሊዮን ዩሮ በዓለም ዙሪያ ዕርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች፣ ሀገረ ስብከቶ፣ ቁምስናዎች እና የሃይማኖት ተቋማት፣ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች፣ በጦርነት እና በረሃብ የተጎዱ ሕዝቦች፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለተጎዱ ማኅበረሰቦች መከፋፈሉ ታውቋል።

የቅዱስ ጴጥሮስ የዕርዳታ ፈንድ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ 2023 በ 76 አገሮች ውስጥ 236 ፕሮጀክቶችን በመደገፍ በአጠቃላይ 13 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። ፈንዱ በአፍሪካ ለሚካሄዱ 68 ፕሮጀክቶች የ5.4 ሚሊዮን ዩሮ፣ በአውሮፓ ለሚካሄዱ 100 ፕሮጀክቶች የ2.4 ሚሊዮን ዩሮ፣ በደቡብ እና ሰሜን አሜሪካ ውስጥ ለሚካሄዱ 34 ፕሮጀክቶች 2.3 ሚሊዮን ዩሮ፣ በእስያ ውስጥ ለሚካሄዱ 33 ፕሮጀክቶች 2.8 ሚሊዮን ዩሮ እና በኦሽንያ በመካሄድ ላይ ለሚገኝ 1 ፕሮጀክት 0.1 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል።

ሪፖርቱ በአውሮፓ ውስጥ የተከናወኑ ፕሮጀክቶችን በመጥቀስ እንዳስታወቀው፥ ግማሽ ሚሊዮን ዩሮ ለካህናቱ፣ ለዘርዓ ክኅነት ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በጳጳሳዊ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርቶችን ለመከታተል የትምህርት ዕድል ላገኙት ከአፍሪካ፣ ከላቲን አሜሪካ እና ከእስያ የሚመጡ ተማሪዎች ለመርዳት መዋሉን አመልክቶ፥ በጦርነት ውስጥ በምትገኝ ዩክሬን ውስጥ በመካሄድ ላይ የሚገኙ ልዩ ልዩ ሐዋርያዊ አገልግሎቶች እና ማህበራዊ ውጥኖች ለመደገፍ ከአንድ ሚሊዮን ዩሮ በታች ድጋፍ መደረጉን ሪፖርቱ አስታውቋል።

የገንዘብ ልገሳ መጠን መጨመር
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2023 የተሰበሰበው የቅዱስ ጴጥሮስ የዕርዳታ ፈንድ መጠን አምና ከተሰበሰበው በእጥፍ መጨመሩን የገለጸው ሪፖርቱ ይህም 107 ሚሊዮን እንደሆነ አስታውቆ፥ የወጪው መጠንም 95.5 ሚሊዮን እንደ ነበር አክሎ አስታውቋል። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2022 ዓ. ም. ከሪል እስቴት ንብረቶች ሽያጭ የተገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ የዕርዳታ ትርፍ ከፍተኛ እንደነበር ሪፖርቱ አመላክቷል።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2023 ዓ. ም. የተገኘው የልገሳ መጠን በ2022 ከተገኘው 43.5 ሚሊዮን ዩሮ ጋር ሲነፃፀር ወደ አምስት ሚሊዮን ዩሮ ገደማ መጨመሩን ሪፖርቱ አስታውቋል። የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን ሐዋርያዊ ተልዕኮ ለመደገፍ የወጣው ወጪ 370.4 ሚሊዮን ዩሮ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 90 ሚሊዮን ዩሮ የተገኘው ከቅዱስ ጴጥሮስ የዕርዳታ ፈንድ እንደ ነበር እና ገንዘቡም ለ68 የቅድስት መንበር ከፍተኛ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤቶች እና መምሪያዎች እንደነበር ሪፖርቱ አክሎ አስታውቋል።

 

01 July 2024, 16:54
Prev
January 2025
SuMoTuWeThFrSa
   1234
567891011
12131415161718
19202122232425
262728293031 
Next
February 2025
SuMoTuWeThFrSa
      1
2345678
9101112131415
16171819202122
232425262728