ብጹዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ከፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ተገናኝተዋል ብጹዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ከፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ተገናኝተዋል  

ካርዲናል ፓሮሊን ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ጋር ተገናኝተው ለሰላም ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋገጡ

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልዕክተኛ ሆነው በዩክሬን ሐዋርያዊ ጉብኝት ሲያካሂዱ የቆዩት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ማክሰኞ ከአገሪቱ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ተገናኝተው ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። ብፁዕነታቸው ባለፉት ቀናት ውስጥ ከዩክሬን ባለስልጣናት ጋር የተካሄዱት ተቋማዊ ስብሰባዎች ማክሰኞ ከፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ባደረጉት ስብሰባ ተጠናቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ብጹዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ከፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጋር ከተገናኙ በኋላ በኤክስ ገጹ ላይ የወጣው የቅድስት መንበር የውጭ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት ዜና እንዳመለከተው፥ ብጹዕነታቸው ከፕሬዝዳንት ጋር ባደረጉት ውይይት፥ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን አጋርነት እና በጦርነት ለተጎዳችው ዩክሬን ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላም ለማግኘት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

አቶ ዘለንስኪ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ የርዕሠ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በልዕክተኞችን በኪዬቭ መቀበላቸው የሚታወስ ሲሆን፥ በወቅቱ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጣሊያን ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት እና የቦሎኛ ከተማ ጳጳስ ብጹዕ ካርዲናል ማቴዮ ዙፒ በጦርነት የተመሰቃቀለችው ዩክሬንን እንዲጎብኟት እና ከዩክሬን ፕሬዝዳንት ጋር እንዲገናኙ ጠይቀው ነበር ይታወሳል።


ባለፉት ዓመታት አቶ ዘለንስኪ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳት ፍራንችስኮስ ጋር ለመነጋገር ብዙ ዕድሎችን ያገኙ ሲሆን የመጨረሻው አጋጣሚ ሰኔ 7/2016 ዓ. ም. በደቡብ ጣሊያን በተካሄደው የ G7 ስብሰባ ላይ እንደ ነበር ይታወሳል። ከዚያ በፊትም በታኅሳስ 18/2016 ዓ. ም. የብርሃነ ልደቱን በዓል ምክንያት በማድረግ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በስልክ መልካም ምኞት መለዋወጣቸውን እና ውይይት ማድረጋቸውን አቶ ዘለንስኪ በኤክስ ገጻቸው በኩል መናገራቸው እና በዚህ አጋጣሚም ፍትሓዊ ሰላም ለሁላችን እንዲመጣ እና ቫቲካን ለፕሬዝዳንታዊው የሰላም ዕቅድ ባላት አድናቆት ላይ አጽንዖት ሰጥተዋል።

ቀደም ሲል ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር የተደረጉ ውይይቶች
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከዚህ ቀደም የዩክሬይኑን ፕሬዝዳንትን አቶ ዘለንስኪን በቫቲካን ተቀብለው ማነጋገራቸው የሚታወስ ሲሆን፥ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ2020 እና እና በተመሳሳይ ዓመት ግንቦት 13/ 2020 ለሁለተኛ ጊዜ እንደተገንኙ እና ይህም ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች በኋላ የመጀመሪያው እንደ ነበር ይታወሳል።

አቶ ዘለንስኪ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንደጻፉት፥ በሩስያ እና በዩክሬን መካከል ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት ከሁለት ቀናት በኋላ ማለትም እንደ ጎርጎሮሳውያኑ የካቲት 26/2022 ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እየሆነ ባለው ነገር በጥልቅ ማዘናቸውን ገልጸው፥ ፕሬዝዳንቱም በበኩላቸው የዩክሬን ሕዝብ የቅዱስነታቸው መንፈሳዊ ድጋፍ የተሰማው መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ መጋቢት 22/2022 በተደረገ ሌላ የስልክ መልዕክት ልውውጥ በዩክሬይን ስለተከሰተው አስቸጋሪ ሰብዓዊ ሁኔታ እና የሰብዓዊ ዕርዳታ መንገዶች በሩሲያ ኃይሎች መዘጋታቸውን በማስመልከት ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ገለጻ ማድረጋቸውን እና የሕዝቡን ስቃይ ለማስቆም ቅድስት መንበር የምትጫወተውን የሽምግልና ሚናን በደስታ መቀበላቸውን አቶ ዘለንስኪ ገልጸዋል።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በነሐሴ 12/2022 የተደረገውን ሌላ የስልክ መልዕከት ልውውጥ በማስመከት ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ በኤክስ ገጻቸው ላይ በለጠፉት ጽሑፍ፥ ከቅዱስነታቸው ጋር የተደረገው ውይይት በሩሲያ ወረራ ምክንያት በሕዝቡ እየደረሰ ባለው መከራ ላይ ያተኮረ እንደ ነበር ተናግረዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዩክሬንን ሕዝብ በጸሎታቸው በማስታወሳቸው ምስጋናቸውን እንዳቀረቡላቸው እና ቅዱስነታቸው በዩክሬይን ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተስፋ እንዳላቸው አቶ ዘለንስኪ በመልዕክታቸው ገልጸዋል።

የክብር ሽልማት መስጠት
በብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን እና በፕሬዝዳንት ዘለንስኪ መካከል ማክሰኞ ሐምሌ 16/2016 ዓ. ም. በተካሄደው ስብሰባ ላይ ፕሬዝዳንቱ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የልኡካን ቡድን የክብር ሽልማት የሰጡ ሲሆን፥ ፕሬዝዳንት ከስብሰባው በኋላ በ X ገጻቸው ላይ በለጠፉት ጽሑፍ፥ “ሽልማቱ ብጹዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን በሁለትዮሽ ግንኙነት ዕድገት መካከል ለተጫወቱት ልዩ ሚና እና በአስፈሪው የጥቃት ጊዜ ላደረጉት ድጋፍ እውቅናን ለመስጠት ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

ለብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን የተሰጠ የክብር ሽልማት
ለብጹዕ ካርዲናል ፓሮሊን የተሰጠ የክብር ሽልማት
24 July 2024, 16:09