ፈልግ

በፓሪስ የተካሄዱ የኦሎምፒክ ውድድሮች ዝግጅቶች በፓሪስ የተካሄዱ የኦሎምፒክ ውድድሮች ዝግጅቶች   (ANSA)

ቅድስት መንበር በኦሎምፒክ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት፥ በክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመውን ወንጀል አወገዘች

ቅድስት መንበር በዘንድሮው የፓሪስ የኦሎምፒክ ውድድሮች መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ በቀረቡ አንዳንድ ትዕይንቶች ላይ የተሰማትን ሐዘን ገልጻለች። ቅድስት መንበር ይህን ትዕይንት በማስመልከት መግለጫ የሰጠች ሲሆን፥ “መላው ዓለም የጋራ እሴቶቻቸውን ለመጋራት በተሰበሰበበት ታላቅ ዝግጅት ላይ በሕዝቦች ሃይማኖታዊ እምነት ላይ የሚያፌዙ ንግግሮች ሊኖሩ አይገባም” ስትል ገልጻለች።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ቅድስት መንበር ሐምሌ 19/2016 ዓ. ም. በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ውስጥ በተካሄደው የኦሊምፒክ ውድድሮች የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ በአንዳንድ ትዕይንቶች ላይ የተሰማትን ሐዘን እና ጸጸት በመግለጫው ላይ ገልጻለች።

በክርስቲያኖች እና ሌሎች አማኞች ላይ የተፈጸመ ወንጀል
“በፓሪሱ የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ በቀረቡት አንዳንድ ትዕይንቶች ላይ ቅድስት አዝናለች” ያለው መግለጫው፥ “በቅርብ ቀናት የተነሱትን የተቃውሞ ድምፆች መቀላቀል የምትችለው በክርስቲያኖች እና በሌሎች ሃይማኖቶች ተከታዮች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥፋት ለማቃለል ብቻ” እንደሆነ መግለጫው ገልጿል።


ሌሎችን ለማክበር ሲባል ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት ተገድቧል
የቅድስት መንበር መግለጫ በመቀጠልም፥ “መላው ዓለም እሴቶቹን ለመጋራት በተሰበሰበበት ታላቅ ዝግጅት ላይ በበርካታ ሕዝቦች ሃይማኖታዊ እምነት ላይ የሚያፌዙ ንግግሮች ሊኖሩ አይገባም” ሲል ገልጿል።

ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ጥያቄ ውስጥ እንደማይገባ የገለጸው መግለጫው፥ “ነገር ግን ሌሎችን በማክበር ረገድ ተገድቧል” ሲል ገልጿል።

 

05 August 2024, 15:53