ቅድስት መንበር፡- ቴክኖሎጂ የሰውን ሕይወት ማሻሻል እንጂ መንጠቅ የለበትም ማለቷ ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
ሊቀ ጳጳስ ኤቶሬ ባሌስትሬሮ በቅርቡ በጄኔቫ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መድረክ ላይ “ገዳይ ሮቦቶች” እየተባሉ የሚጠሩትን ገዳይ ራስ ገዝ የጦር መሣሪያ ሥርዓቶችን (LAWS) ልማትን በቅርበት መከታተል እንደሚያስፈልግ ተናሯል።
በጄኔቫ የቅድስት መንበር የተባበሩት መንግስታት እና ሌሎች አለም አቀፍ ድርጅቶች ቋሚ ታዛቢ እ.አ.አ በ2024 ዓ.ም የመንግስት በዘርፉ በቂ ሙያ ያላቸው ሰዎች ቡድን በገዳይ ራስ ገዝ የጦር መሣሪያ ሥርዓቶች ላይ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በተመለከተ የምያደርጉትን ስብሰባ ሁለተኛውን ክፍለ ጊዜ እ.አ.አ በነሐሴ 26/2024 ዓ.ም ጀምሮ ማከናወን ጀምረዋል።
ሊቀ ጳጳስ ባሌስትሬሮ ንግግራቸውን ሲከፍቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለቡድን ሰባት አገራት አባላት "ለG7" መሪዎች እ.አ.አ በሰኔ 2024 ዓ.ም ባደረጉት ንግግር እነዚህን ራስ ገዝ የሆኑ ገዳይ የጦር መሣሪያ ሥርዓቶችን ለመከላከል ህጎችን የማውጣት አስፈላጊነትን አጽኖት ሰጥተው እንደተናገሩም አስታውሰዋል።
በዚያ አጋጣሚ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ የሰው ልጅ ሁል ጊዜ የማንኛውም የጦር መሣሪያ በቁጥጥር ሥር መሆኑን መረጋገጥ እንዳለበት ገልጸው፣ “ምንም ዓይነት ማሽን ወይም የብልሃት መሣሪያ የሰውን ሕይወት ለማጥፋት መመረት የለበትም” ብለዋል።
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የጦር መሳሪያ አጠቃቀምን፣ እድገታቸውን እና አጠቃቀማቸውን ለማቆም ቅድስት መንበር ህጋዊ የሆነ ስምምነት እንደምትፈልግ ሊቀ ጳጳሱ ተናግረዋል። ሀገራት መሣሪያዎችን ለመፈተሽ የጦር ትያትሮችን እየተጠቀሙ ነው ሲሉ በቁጭት ተናግሯል።
“በጣም አሳዛኝ ነው” ሲሉ አክለው የተናገሩት ሊቀ ጳጳስ ባሌስትሬሮ “በመሳሪያ ግጭቶች ምክንያት የሚደርሰውን ስቃይ በተጨማሪ የጦር ሜዳዎቹ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተራቀቁ የጦር መሣሪያዎችን ለማግኘት መሞከሪያ ሆነዋል ብለዋል።
ሊቀ ጳጳስ ባሌስትሬሮ የቅድስት መንበር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተወካይ “የአውቶማቲክ የጦር መሣሪያ ሥርዓቶችን አቅም ያላቸው ተግባራት እና የቴክኖሎጂ ገጽታዎች” ለመተንተን የሚደረገውን ጥረት ትደግፋለች ያሉት ሲሆን አሁን ያሉትን ደንቦች እና ዓለም አቀፍ ደንቦችን ያሟሉ መሆናቸውን በትክክል ለመገምገም አስፈላጊ በመሆኑ የተነሳ ነው ብለዋል።
ሊቀ ጳጳሱ አክለውም ቅድስት መንበር ገዳይ ራስ ገዝ የጦር መሣሪያ ሥርዓቶችን (LAWS) በፍፁም “ሥነ ምግባራዊ ኃላፊነት የሚሰማቸው አካላት” ተደርገው ሊወሰዱ እንደማይችሉ ትናገራለች ብለዋል።
"የሰው ልጅ የማመዛዘን ችሎታ ያለው፣ ምንም ያህል ውስብስብ ቢሆንም በማንኛውም የስልተ ቀመሮች ሊደገም የማይችል የሞራል ፍርድ እና የስነ-ምግባር ውሳኔ የመስጠት ልዩ ችሎታ አለው" ብሏል።
ሊቀ ጳጳስ ባሌስትሬሮ “በምርጫ” እና “በውሳኔ” መካከል ያለውን የሥነ ምግባር ልዩነት ጠቁመዋል።
ውሳኔ ከቀላል ምርጫ የዘለለ እና እሴቶችን እና ተግባሮችን ግምት ውስጥ በማስገባት ተግባራዊ ግምገማን ይጠይቃል ብለዋል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ "ማሽኖች የቴክኒክ ስልተ ቀመር ወይም አልጎሪዝም አማራጮችን እንደሚመርጡ ሲጠቁሙ "የሰው ልጆች ግን መምረጥ ብቻ ሳይሆን በልባቸው ውስጥ የመወሰን ችሎታ አላቸው" ብለዋል።
ስለዚህ የቅድስት መንበር ተወካይ ሊቀ ጳጳስ ባሌስትሬሮ እንዳሉ ከሆነ ሰብዓዊ ክብርን እና ሥነ ምግባራዊ ግምትን የሚያመለክት ሆን ተብሎ የሚነገር ቋንቋን ትጠቀማለች ብለዋል።
ዓለም አቀፍ ስምምነቶች በሰው ሰራሽ ኢንተለጀንስ መርሃ ግብሮች በሚደረጉ ምርጫዎች ላይ ትክክለኛ የሰው ልጅ ቁጥጥር ቦታን ለማረጋገጥ እና ለመጠበቅ ፣የሰብአዊ ክብር እራሱ በእሱ ላይ የተመሰረተ ነው ብለዋል ።
በማጠቃለያው የቅድስት መንበር ተወካይ በጄኔቫ እንደተናገሩት ይበልጥ የተራቀቁ የጦር መሣሪያዎችን ማዘጋጀት ለዓለም ችግሮች መፍትሄ አይሆንም ያሉ ሲሆን "የሰው ልጅ አሁን ካለው የቴክኖሎጂ ግስጋሴ ሊያገኘው የሚችላቸው የማያጠራጥር ጥቅማጥቅሞች የሚወሰኑት እንዲህ ያለው እድገት በበቂ የኃላፊነት እና የእሴቶች እድገት ደረጃ ላይ ሲሆን የቴክኖሎጂ እድገቶችን ለውህደት አገልግሎት የሚሰጥ ነው፣ የሰው ልጅ ልማት እና የጋራ ጥቅምን ከግምት ያስገባ ሊሆን ይገባዋል ብለዋል።