ፈልግ

ቅዱስ ሲኖዶስ፥ ስለ ሰላም መስከረም 27 ስለሚደረገው የፆም ጸሎት ቀን አስመልክቶ መግለጫ ሰጠ

በአዲስ መልክ የተዋቀረው የቅድስት መንበር ጋዜጣዊ መግለጫ ጽ/ቤት የሲኖዶስ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሲኖዶሳዊ ጉባኤ መክፈቻን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የብጹአን ጳጳሳት ሲኖዶስ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ 2ኛ ምዕራፍ መክፈቻን አስመልክቶ ሐሙስ ጥቅምት 23 ቀን 2017 ዓ. ም. ከቅድስት መንበር የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በቀጥታ ስርጭት የተላለፈ ሲሆን፥ መግለጫው ቁልፍ ጭብጦች ስለሆኑት የሰላም፣ የይቅር ባይነት፣ የሴቶች ሚና እንዲሁም የጥናት ቡድኖቹ የአሰራር ዘዴዎች ላይ በማተኮር ነበር።

መግለጫውን ከሰጡት ውስጥ የብጹአን የጳጳሳት ሲኖዶስ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ልዩ ጸሐፊ አባ ጃኮሞ ኮስታ፣ 2ኛው የሲኖዶስ ልዩ ጸሐፊ የሆኑት ሞንሲኞር ሪካርዶ ባቶቺዮ፣ የሲኖዶሱ ጉባኤ ልዑካን ፕሬዚዳንት የሆኑት የቅዱስ ዮሴፍ እህቶች ጉባኤ አባል ሲስተር ማርያ ዴ ሎስ ፓሌንሺያ ጎሜዝ እና የቴክሳስ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብጹእ አቡነ ዳንኤል ኤርነስት ይገኙበታል። ከእነዚህም በተጨማሪ የቅድስት መንበር መገናኛዎች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ እና የሲኖዶሱ የመረጃ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ዶክተር ፓውሎ ሩፊኒ ለጋዜጠኞች ንግግር አድርገዋል።

ፓውሎ ሩፊኒ፥ "መንፈሳዊነት እና ጸሎት ዋነኛ ናቸው"
ሃሙስ ጠዋት በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ከ365 የሲኖዶስ አባላት 356ቱ መገኘታቸውን ዶክተር ሩፊኒ አስታውቀዋል። በጉባኤው ወቅት የእያንዳንዱን ቡድን ዕለታዊ የውይይት ጭብጥ የሚዘግቡ ሰዎች የተመረጡ ሲሆን፥ በዕለቱም በኢንስትሩሜንተም ላቦሪስ “መሠረቶች” ምእራፍ ላይ በማተኮር ከአምስት የሥራ ሞጁሎች ውስጥ የመጀመሪያው ምዕራፍ ተጀምሯል።

የቫቲካን መገናኛ ጉዳዮች ሃላፊው በክፍለ-ጊዜዎቹ ውስጥ የ “መንፈሳዊነት እና የጸሎት” አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት የሰጡ ሲሆን፥ ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ በሁሉም ተሳታፊዎች ልብ እና አእምሮ ላይ በተለይም በጦርነት ወይም በስቃይ ውስጥ ከሚገኙ ክልሎች ለሚመጡት ልዩ ትኩረት እንደሚሰጣቸው ጠቁመዋል። በዚህ አግባብ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ሁከትን ለማስቆም የሚቻለውን ሁሉ እናድርግ” እንዲሁም “የሰላም መንገዶችን እንፈልግ” በማለት ደጋግመው የተናገሩትን አስታውሰዋል። ከዚህም በላይ ዶክተር ፓኦሎ ሩፊኒ በሲኖዶሱ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉት አሥር የጥናት ቡድኖች በሂደቱ ውስጥ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ጎላ አድርገው ገልጸዋል።

የሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ
የሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ

አባ ኮስታ፥ "የሥራ ቡድኖች እንደ ሲኖዶሳዊ ሕይወት ‘ቤተ ሙከራ’ ናቸው”
አባ ኮስታ በበኩላቸው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ሲኖዶሱ “ፓርላማ አይደለም፣ ነገር ግን የመደማመጥና የመግባቢያ ቦታ ነው” በማለት ያሳሰቡትን በድጋሚ የተናገሩ ሲሆን፥ በጉባኤው አዳራሽ ውስጥ ያለውን አስደሳችና ጥልቅ መንፈስ በመጥቀስ፥ ይህ የተጋነነ አነጋገር ዘይቤ ብቻ ሳይሆን የሕይወት ተሞክሮ መሆኑንም ጭምር አሳስበዋል።

ሁሉም ምእመናን ለሚያረጉት አስተዋጾ ክፍት የሆነው እና የሚሰጡት ግብአቶች እስከ ሰኔ 2017 ዓ.ም. ተቀባይነት የሚያገኙበትን “የሲኖዶሳዊ ሕይወት ቤተ ሙከራ” የሆኑትን የጥናት ቡድኖችን ሁሉም ሰው እንዲከታተል መክረዋል። ከዚህም በተጨማሪ እነዚህ ቡድኖች፣ ዝግ የሆኑ ኮሚቴዎች ሳይሆኑ ቤተ ክርስቲያን በጋራ ለመስራት የምትማርባቸው የትብብር ቦታዎች መሆናቸውንም ጠቁመዋው፥ ተልእኳቸውም በሲኖዶሱ የሥራ ሰነድ ውስጥ ካሉት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ “አነስተኛ” ሲኖዶሳዊ ሂደቶችን ማካሄድ እንደሆነ ገልጸዋል።

ዕቅዱ ከ2023 ወደ 2024 መሸጋገሩ
አባ ኮስታ በአንደኛውና በሁለተኛው የሲኖዶስ ምዕራፍ መካከል ያለውን ልዩነት ሲያንራሩ፥ በ 2015 ዓ.ም. ግቡ መታየት የሚገባቸውን የተለያዩ አመለካከት ያላቸውን “የቤተ ክርስቲያኑ ታሪኮች” ማዳመጥ እንደነበር በማስታወስ፥ በ 2016 ዓ.ም. ግን የጉባዔው ሚና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን አቅጣጫዎች ለሲኖዶሱ ጉዞ አቅጣጫ መስጠት እንደሆነ፥ ይህም ተመሳሳይነትን ሳይፈጥር ስምምነትን ለማጎልበት እንደሆነ ገልጸዋል።

“አሁን ያለው የአሰራር ዘዴ በመንፈሳዊ ውይይት ለጥልቅ ትንተና እና ቁልፍ ነጥቦችን ለመለየት እንደሚረዳ በማንሳት፥ ግትር ድምዳሜዎችን ለማስወገድ ለተጨማሪ ጥናቶች ክፍት ቦታዎችን እንደሚተው ጠቁመዋል።

የይቅርታ እና የሃይማኖት ሊቃውንት አስፈላጊነት
የሥነ-መለኮት ምሁሩ ሞንሲኞር ባቶቺዮ በበኩላቸው በተለይ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ መሪነት በቅዱስ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ማክሰኞ ዕለት ይቅርታን አስመልክቶ የተካሄደውን የውይይት ወቅትን አስታውሰው፥ በዚያን ወቅት ኃጢአተኛው ሌላ ሰው ሳይሆን ሸክሙን መሸከም ያለብኝ ሰው በመሆኑ “ቤተ ክርስቲያን መሆን ምን ማለት እንደሆነ ለማስተዋል ምሳሌ የሚሆን” እንደሆነ በመግለጽ፣ “እኛ የእግዚአብሔርን ምሕረት የምንቀበል ቤተክርስቲያን ነን” በማለት አጽንዖት ሰጥተዋል።

ሞንሲኞር ባቶኪዮ በአዳራሹ ውስጥ ስለሚደረጉ ውይይቶች “ሥነ-መለኮታዊ ግንዛቤ” የመስጠት ኃላፊነት በሲኖዶሱ ውስጥ ያላቸውን የማይናቅ ሚና በማጉላት፥ ይህ ከ 2015 ዓ.ም. ጋር ሲነፃፀር በዚህ ዓመት በማእከላዊ አቀማመጥ ላይ ብልጫ አሳይቷል ብለዋል።

የሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ
የሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ

ሲስተር ፓሌንሺያ ጎሜዝ፥ “እድገት ለሴቶች!”
ሲስተር ማርያ ዴ ሎስ ጎሜዝ በጉባኤው ውስጥ ስላለው “ታላቅ ነፃነት እና ታላቅ ጉጉት” እንዲሁም ተሳታፊዎቹ እንዴት በጋራ እንደሚራመዱ ገልጸው፥ “የዚህን ዓለም መራር እውነታ ብንገነዘብም እኛ ግን በአባታችን በእግዚአብሔር ዓይን ነው የምንመለከተው” ካሉ በኋላ፥ በተጨባጭ በሲኖዶሳዊነት እና በተልዕኮ ልምድ ማደግ የምንችለው በዚህ መነጽር ብቻ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በቤተክርስቲያን ውስጥ ስላለው የሴቶች ሚና የተጠየቁት ሜክሲካዊ መነኩሴ፥ በተለያዩ አውዶች እና አህጉራት የሴቶች ሚና ከፍተኛ እድገት ማሳየቱን ጠቁመዋል።

በላቲን አሜሪካ ስላጋጠማቸው ተሞክሮ ያነሱት ሲስተር ማርያ “የሴቶች ሚና፣ ተሰጥዖዋቸው እና የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ በሲኖዶሳዊ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታወቀ መጥቷል” ካሉ በኋላ፥ የሴቶችን ሚና ለማጉላት እና ይበልጥ ለመጠቀም አዳዲስ እድሎችም እንዳሉ ጠቁመዋል።

ለሴቶች የድቁና ማእረግ ስለመስጠት ጉዳይም ተነስቷል
ስለ ሴት ዲያቆናትን አስመልክተው፣ ተናጋሪዎቹ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ የብፁዕ ካርዲናል ቪክቶር ማኑኤል ፈርናንዴዝ መግለጫ በመድገም፥ ለዚህ ርዕስ መልስ ለመስጠት ጊዜው ገና እንዳልደረሰ በመግለጽ፣ ነገር ግን በቤተ ክርስቲያኑ የጋራ ጉዞ ውስጥ መፈተሹ እንደማይቀር ጠቁመዋል።

የሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ
የሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ

ብጹእ አቡነ ፍሎሬስ "ጸጥታ የሲኖዶሳዊ ዘይቤ ነው"

ብጹእ አቡነ ፍሎሬስ በሲኖዶሳዊው ሂደት ውስጥ የጸጥታን አስፈላጊነት አንስተው፥ መስከረም 21 እማሆይ ማርያ ኢግናዚያ አንጀሊኒ የመሩትን የማሰላሰል ጊዜ በመጥቀስ፣ ጸጥታ ባዶ ቦታ ሳይሆን በቃላት ትርጉም የተሞላ ቦታ ነው ብለዋል። ይህ የሲኖዶስ ዘይቤ መሠረታዊ አካል ነው ያሉት ጳጳሱ፣ ዓለምን ጥልቅ በሆነ መንፈሳዊነት ለመረዳት እንዴት እንደሚያስችል ጠቁመዋል።

አከባቢያዊ እይታዎችን መመልከት
ብጹእ አቡነ ፍሎሬስ በአካባቢያዊ አመለካከቶች እሴት ላይ ማሰላሰል ‘የእውነት ጠላቶች አይደሉም’ ነገር ግን ቤተክርስቲያኗ በሥርዓት እና በትዕግስት ማዳመጥ እንድትችል ይፈቅዳል። ይህ በበኩሉ የክርስቶስን በዓለም ላይ መገኘት በተመለከተ ሰፋ ያለ አመለካከት እንደሚሰጥ ገልጸዋል። የሲኖዶሱ ተግባር የዛሬዋን የቤተ ክርስቲያኗን ህይወት እና ልምድ የሚገልጽ ወጥ የሆነ ድምጽ ማግኘት ነው ካሉ በኋላ፥ የ “እኛነት” የጋራ አመለካከት በሲኖዶሳዊ ሥራ ውስጥ አስፈላጊ እንደሆነ፣ ይህም ከግለሰባዊ አመለካከቶች የበለጠ ዋጋ እንዳለው አስታውሰዋል።

መስከረም 26 እና 27 የሚከናወነው የቅዱስ አባታችን የሰላም ጥሪ እና ተነሳሽነቶች
ጋዜጣዊ መግለጫው የተጠናቀቀው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ መስከረም 26 እና 27 እንዲደረግ ያሰቡትን የሰላም ውጥኖች ማለትም በእመቤታችን ቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ስለሚደረገው የመቁጠሪያ ጸሎት እና የፆም ጸሎት ቀንን በማስታወስ ነበር።

ሁሉም የሲኖዶስ ተሳታፊዎች በእሁዱ ዝግጅት ላይ እንዲገኙ የተጋበዙ ሲሆን፥ የሰኞው ክፍለ ጊዜ ደግሞ ልዩ በሆነ የጸሎት እና የጥሞና መንፈስ እንደሚታወስ ተገልጿል።

ሲኖዶሳዊ ጉባኤ መክፈቻን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

 


 

04 October 2024, 21:35