ፈልግ

ከመስከረም 22 እስከ ጥቅምት 17/2017 ዓ.ም በሲኖዶሳዊነት ላይ ሲካሄድ የነበረው የ16ኛው መደበኛ ሲኖዶስ ሁለተኛ ክፍል ከመስከረም 22 እስከ ጥቅምት 17/2017 ዓ.ም በሲኖዶሳዊነት ላይ ሲካሄድ የነበረው የ16ኛው መደበኛ ሲኖዶስ ሁለተኛ ክፍል   (Vatican Media)

ሥር መሠረቱን በጠበቀ መልኩ ወንጌልን ለማወጅ የሚደረግ መንፈሳዊ ንግደት!

ከመስከረም 22 እስከ ጥቅምት 17/2017 ዓ.ም በሲኖዶሳዊነት ላይ ሲካሄድ የነበረው የ16ኛው መደበኛ ሲኖዶስ ሁለተኛ ክፍል የተጠናቀቀ ሲሆን የሲኖዶሱ የመጨረሻ ሰነድ ሁለተኛውን የቫቲካን ጉባኤ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ተጨባጭ እርምጃ የወሰደ ነው ሲሉ የቫቲካን ዜና የአርትኾት ሥራ አላፊ የሆኑት አርታይ አንድሪያ ቶርኔል ሐሳባቸውን ለቫቲካን ዜና አጋርተዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ከጥቂት ቀናት በፊት በሲኖዶሱ የጸደቀው ሰነድ ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የጀመረው ጉዞ ቀጣይነት ያለው እና በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በየደረጃው በተጨባጭ መኖር ያለበት መድረክ ነው። ሲኖዶሳዊነት የመኖር እና የኅብረት ምስክርነት መንገድ መሆኑን እውቅና መስጠት ነው። ቤተክርስቲያኗ ኩባንያ ወይም ፓርቲ አይደለችም፥ ኤጲስ ቆጶሳት የሮም 'አስተዳዳሪዎች' አይደሉም፣ ምእመናን የካህናት ውሳኔዎችን እና መመሪያዎችን ብቻ የምያስፈጽሙ አካላት አይደሉም። ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ሕዝብ በአንድነት የሚመላለሱባት መንገድ  ወይም ማደሪያ ናት፡ የመኖሯ ምክንያት በመዋቅሮች፣ በቢሮክራሲዎች ወይም በሥልጣን አስተዳደር ውስጥ ብቻ አይደለም። በአለም ላይ የራሷን ቦታ ለማሸነፍ እና ለመከላከል አላማ የላትም። የመኖሯ ብቸኛው ምክንያት የዘመናችን ሴቶች እና ወንዶች በሚኖሩበት፣ በሚሰሩበት፣ በሚደሰቱበት፣ በሚሰቃዩበት ቦታ ሁሉ ከክርስቶስ ጋር መገናኘትን ዛሬ ማድረግ ነው።

ስለዚህ፣ ፍፁም የተለየ እና ወንጌላዊ የሆነ የኑሮ ግንኙነት እና ትስስር አለ። ኢየሱስ እንዳስተማረው በአገልግሎት ላይ ያማከለ መንገድ ያስፈልጋታል። በተለይ እንደኛ ባለ ዘመን መለያየት፣ጥላቻ፣አመጽ፣ልዩነት የታየበት፣የውሳኔ፣የማቀድ፣የመተግበር ተጨባጭ መንገድ አለ።

ሲኖዶሳዊነትን መኖር ማለት የሁለተኛውን የቫቲካን ጉባሄ ሙሉ ትግበራ አንድ እርምጃ መውሰድ ማለት ነው። ይህም ማለት መነሻውን በቁም ነገር መውሰድ ማለት ነው - ከመነሻው - ከመጀመሪያው- ቤተ ክርስቲያን መሆን: ለሁሉም ሰው የሚሆን ቦታ ያለው እና ሁሉም ሰው ዋጋ ያለው ማህበረሰብ፣ የእግዚአብሔርን ፍቅር የሚለማመዱ እና መግባባት የሚፈልጉ ኃጢአተኞች ይቅር የተባሉ ማኅበረሰቦች የሚኖሩባት፣ ለሁሉም ክፍት የሆነች ቤተክርስቲያን መሆን መቻል ማለት ነው።

በሲኖዶሳዊነት ላይ የተደርገው ሲኖዶስ የተለያዩ አመለካከቶች ያሉት ሁሉም ሰው ብዙ ጥያቄ እንዲያነሳ የምያደርግ ሲኖዶስ ነበር ማለት ይቻላል። የአስተሳሰብ ለውጥ ይጠይቃል። ሲኖዶሳዊነትን እንደ ቢሮክራሲያዊ ተግባር እንዳንቆጥረው ይጠይቀናል፣ በአባትነት መንፈስ የሚተገበር እንጂ፣ በጥቂት ጥቃቅን የመዋቢያ ማሻሻያዎች የሚስተካከል ብቻ አይደለም። ይህ የሚያስከትላቸው መዘዞችን ሁሉ በቀላሉ ከመታገስ ይልቅ አብሮ የመሄድ ፍላጎት እንደገና እንድናገኝ ይጠይቃል። ቤተክርስቲያኗን በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የሚመራው ጌታ መሆኑን በእርግጠኝነት በመተማመን መንጋውን እንድናስቀጥል እና እንድንደፍር ይጠይቀናል። የቅዱስ ጴጥሮስን ተተኪ ጨምሮ የስልጣን አገልግሎት እንደገና እንዲታሰብበት ይጠይቃል። ለምእመናን እና በተለይም ለሴቶች የላቀ ኃላፊነት እንዲኖራቸው እና እንዲሰጣቸው ይጠይቃል።

አባላቱ ሥር የሰደዱ - በቦታ ፣ በታሪክ ፣ በማህበረሰብ ፣ በዐውደ-ጽሑፍ - እና በተመሳሳይ ጊዜ ምዕመናን ፣ ማለትም በእንቅስቃሴ ላይ ፣ ፍለጋ ላይ ያሉ ፣ ሚስዮናውያን የሆኑ የቤተ ክርስቲያን ምስል ናቸው። የቤተክርስቲያን አወቃቀሮች፣ በዚህ አዲስ አተያይ፣ ከአሁን በኋላ ምእመናን መሸፈን ያለባቸውን ቦታ አይወክሉም፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝቦች በዓለም ውስጥ ለሚያደርጉት አገልግሎት ድጋፍ ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በላቲን ቋንቋ "ኢቫንጄሊ ጋውዲውም" (የወንጌል ደስታ) በሚል አርዕስት ለመላው ቤተ ክርስቲያን በአፋጣኝ ያደረሱት ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ የጽሁፉ አድማስ ተልእኮ በተዘጋጀው ረቂቅ መሠረት፣ “ቤተ ክርስቲያን የምትወጣ” እንጂ እንደ መፈክር በአንድ ቦታ ተገትራ የምትቆም ሳይሆን በሁሉም መልካም አስተዋጾ ወደ ፊት የምትጓዝ መሆን ይኖርባታል።

28 October 2024, 14:16