ፈልግ

ረቡዕ ጥቅምት 13/2017 ዓ. ም. በተካሄደው 15ኛ የጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ ረቡዕ ጥቅምት 13/2017 ዓ. ም. በተካሄደው 15ኛ የጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ   (Vatican Media)

የብጹዓን ጳጳሳት ጠቅላላ ጉባኤ ለመደበኛ ምክር ቤት አዲስ አባላትን መሰየሙ ተገለጸ

ከመስከረም 22/2017 ዓ. ም. ጀምሮ በሲኖዶሳዊነት ላይ ሲወያዩ የቆዩት የቅዱስ ሲኖዶሱ 16ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች የሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት መደበኛ ጉባኤ አባላትን መርጠዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ረቡዕ ጥቅምት 13/2017 ዓ. ም. በተካሄደው 15ኛ የጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ የተሳተፉት ልዑካን የሲኖዶሱን ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አዲስ አባላት መርጠዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጉባዔውን ተግባር በመምራት ላይ በሚገኝ የአሁኑ መመሪያ ላይ ማሻሻያ ማድረጋቸው የአባላቱን ጠቅላላ ቁጥር ወደ 17 ከፍ እንዳደረገው የሲኖዶሱ ጽሕፈት ቤት በመግለጫው አስታውቋል።

ጥቅምት 13/2017 ዓ. ም. ከሰዓት በኋላ ከተመረጡት ከእነዚህም መካከል አሥራ ሁለቱ የጉባኤው አካል ከሆኑት ሀገረ ስብከቶች መካከል ሲሆኑ፥ ከምሥራቅ ካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት አንድ፣ ከኦሽንያ አኅጉር አንድ እና 2 እያንዳንዳቸው ማለትም ከሰሜን አሜሪካ፣ ከላቲን አሜሪካ፣ ከአውሮፓ፣ ከአፍሪካ እና ከእስያ፥ ከእያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት አባላት ተመርጠዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የወቅቱ የሮማ ኩሪያ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት ኃላፊን ጨምሮ ቀጣዩን ሲኖዶስ ከሚመሩት ጋር አራት አባላትን መርጠው እንደሚያቀርቡ ታውቋል።

"Episcopalis Communio" ወይም "የብጹዓን ጳጳሳት አንድነት” በተሰኘው ሐዋርያዊ ደንብ ቁ. 24/1-3 ላይ፥ የብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ጠቅላይ ጽ/ቤት፥ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን የማዘጋጀት እና የመተግበር ኃላፊነት እንዳለበት ተገልጿል።

የመደበኛ ምክር ቤት አባላት የስልጣን ዘመን የሚጀምረው በመረጣቸው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ መጨረሻ ላይ ሲሆን፥ የሚቀጥለው የመደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት ተልዕኮ የሚያበቃው ጉባኤው ሲፈርስ እንደሆነ ታውቋል። በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራው የምክር ቤቱ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ አስፈላጊ የሲኖዶስ አካል እንደሆነ ይታወቃል።

አዲሱ መደበኛ ጉባኤ ይህን የሲኖዶሳዊነት ሂደት ተግባራዊ ለማድረግ እና ለቀጣዩ ሲኖዶስ ዝግጅት ለማድረግ ቁልፍ ሚና የሚጫወት ሲሆን፥ የብጹዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጠቅላይ ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ማርዮ ግሬሽ ለተመረጡት አባላት መልካም የሥራ ዘመን ተመኝተው አሁን ያለውን የሲኖዶስ ሂደት ከዳር ለማድረስ ላደረጉት ጠቃሚ ትብብር ተሰናባች አባላትን አመስግነዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ የመረጣቸው የመደበኛ ጉባኤ አዲስ አባላት የሚከተሉት ናቸው፥
ከምሥራቅ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያናት፥ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ አብሲ፥ የአንጾኪያ የግሪክ መልቃይት ፓትርያርክ እና የግሪክ መልቃይት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ኃላፊ፣

ከኦሼኒያ፥ አቡነ ቲሞቲ ጆን ኮስቴሎ፥ በአውስትራሊያ የፐርዝ ሊቀ ጳጳስ፣

ከሰሜን አሜሪካ፥ ብጹዕ አቡነ ዳንኤል ኤርነስት ፍሎሬስ፥ በአሜሪካ የብራውንስቪል ጳጳስ እና
አቡነ አላይን ፋውበርት፥ በካናዳ የቫሊፊልድ ጳጳስ፣

ከላቲን አሜሪካ፥ ካርዲናል ሉዊስ ሆሴ ሩኤዳ አፓሪሲዮ፥ በኮሎምቢያ የቦጎታ ሊቀ ጳጳስ እና
አቡነ ሆሴ ሉዊስ አዙአጄ አያላ፥ በቬንዙዌላ የማራካይቦ ሊቀ ጳጳስ ናቸው።

ከአውሮፓ፥ ካርዲናል ዣን-ማርክ አቬሊን፥ በፈረንሳይ የማርሴይ ሊቀ ጳጳስ እና
አቡነ ጊንታራስ ግሩሺስ፥ በሊጡዌኒያ የቪልኒየስ ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ፣

ከአፍሪካ፥ ካርዲናል ዲዩዶኔ ንዛፓላኢንጋ፥ በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የባንጊ ሊቀ ጳጳስ እና አቡነ አንድሪው ፉአንያ ንኬ፥ በካሜሩን የባሜንዳ ሊቀ ጳጳስ ናቸው።

ከእስያ፥ ካርዲናል ፊሊፔ ኔሪ አንቶኒዮ ሴባስቲያዎ ዶ ሮዳሪዮ ፌራዎ፥ በሕንድ የጎዋ እና ዳማኦ ሊቀ ጳጳስ
አቡነ ፓብሎ ቪርጂሊዮ፥ በፊሊፒንስ የካሎካን ጳጳስ ናቸው።

በዚህ ዝርዝር ውስጥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የሚመርጧቸው ሌሎች አራት እንዳሉ ተገልጿል።

የአሥራ ስድስተኛው የብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ተልዕኳቸውን የሚያጠናቅቁት ጳጳሳት የሚከተሉት ናቸው፡-
ብጹዕ አቡነ ኢግናስ ዩሲፍ ሳልሳዊ ዮናን፥ በሊባኖስ የሶርያውያን የአንጾኪያ ፓትርያርክ እና የሶርያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ መሪ፣
ካርዲናል ክሪስቶፍ ሼክ ኦንቦርን፥ በኦስትሪያ የቪየና ሊቀ ጳጳስ፣
ካርዲናል ኦስዋልድ ግራሲያስ፣ በሕንድ የቦምቤይ ሊቀ ጳጳስ እና የብጹ ዓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት
ካርዲናል ጄራልድ ሳይፕሪየን ላክሮይስ፥ በካናዳ የኪቤክ ሊቀ ጳጳስ፣
ካርዲናል ቻርለስ ማንግ ቦ፥ በምያንማር የያንጎን ሊቀ ጳጳስ፣
ካርዲናል ዳንኤል ፈርናንዶ ስቱርላ ቢሮየት፥ በኡሩጉዋይ የሞንቴቪዲዮ ሊቀ ጳጳስ፣
ካርዲናል ዲዩዶኔ ንዛፓላይንጋ፥ በመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ የባንጊ ሊቀ ጳጳስ፣
ካርዲናል ሰርጆ ዳ ሮቻ፣ በብራዚል የብራዚሊያ ሊቀ ጳጳስ፣
ካርዲናል ጆሴፍ ዊሊያም ቶቢን፥ በአሜሪካ የኒው ዮርክ ሊቀ ጳጳስ፣
ካርዲናል ሁዋን ሆሴ ኦሜላ፣ በስፔን የባርሴሎና ሊቀ ጳጳስ፣
ካርዲናል ጆሴፍ ኩትስ፥ በፓኪስታን የካራቺ ሊቀ ጳጳስ፣
ካርዲናል ማቴዮ ማርያ ዙፒ በጣሊያን የቦሎኛ ሊቀ ጳጳስ፣
አቡነ ገብርኤል ምቢሊንጂ፥ በአንጎላ የሉባንጎ ሊቀ ጳጳስ፣
አቡነ አንቶኒ ኮሊን ፊሼር፥ በአውስትራሊያ የሲድኒ ሊቀ ጳጳስ፣
አቡነ ጄሜ ካልዴሮን በሜክሲኮ የታፓቹላ ሊቀ ጳጳስ፣
አቡነ አንድሪው ፉአንያ ንኬ በካሜሩን የባሜንዳ ሊቀ ጳጳስ መሆናቸውን የብጹዓን ጳጳሳት ጠቅላላ ጉባኤ አስታውቋል።

 

24 October 2024, 17:30