ፈልግ

የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያ ባርተሎሜዎ ቢስካያኖ የሳለው የቅዱስ ቤተሰብ ምስል የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያ ባርተሎሜዎ ቢስካያኖ የሳለው የቅዱስ ቤተሰብ ምስል  

የድነት መንገድ በቤተሰብ ሕይወት በኩል ያልፋል

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ “የኢየሱስ ክርስቶስን መወለድ ክስተት እና የእግዚአብሔር ልጅ የመገለጥ ምስጢርን በቀላል መንገድ በደስታ ከመመስከር ጋር እኩል” መሆኑን አስታወሱ። የኢየሱስ መወለድ ለብዙ መቶ ዘመናት በውበት የሰበኩ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን አነሳስቷል። የቫቲካን ዜና አገልግሎት፥ የገናን ሰሞን በሚገባ ለመኖር እንዲያስችለን ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ንግግሮች ጋር በማድረግ በየሳምንቱ ያቀርባል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በርካታ የቅዱሳት ምስሎች ሞዴሎች ከእምነት ጭብጦች ጋር በተገናኘ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በግል የአምልኮ አውድ ውስጥ የሚሰራጨው በአብዛኛውን ጊዜ በቅርጻ ቅርጽ ሥራዎች አማካይነት ነው። በቫቲካን ሐዋርያዊ ቤተ መጻሕፍት የሕትመት ሥራ ስብስብ ውስጥ በተቀመጡት በ16ኛው እና በ19ኛው ክፍለ ዘመን መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ የተቀረጸው እና ሰውን የፈጠረው የእግዚአብሔር ምስጢር እንድናሰላስል የሚጋብዙ ውድ ጥበባዊ ሥዕሎች ይህንን ያሳያሉ።

ከቅዱስ ቤተሰብ ጋር ያለው ቅርርብ
ከእነዚህም መካከል እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1650 አካባቢ የተሠራው የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት የሚያሳይ መንፈሳዊ ምስል፥ እመቤታችን ማርያም ከዮሴፍ እና ከሚዘምሩ ሁለት መላእክት ጋር መሆናቸውን የሚያሳይ ሲሆን፥ ከበስተጀርባ የሚታዩ ጥንታዊው ፍርስራሾች፥ ከአሮጌው እምነተ አልባው ዓለም ወደ ክርስትና መሸጋገርን ያመለክታሉ።

ሕትመቱ በ1629 እና 1657 መካከል ይኖር የነበረው የ17ኛው ክፍለ ዘመን ጣሊያናዊ ዲዛይነር እና የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያ ባርተሎሜዎ ቢስካይኖ ሥራ ሲሆን፥ የአባቱን የጆቫኒ አንድሪያ ሥዕል ለማጥናት የተነሳሳው ሠዓሊ ባርቶሎሜዮ ለቅጂ ሥራዎቹ ከምንም በላይ አድናቆትን ማግኘቱ ታውቋል።

በክፍለ ዘመኑ አጋማሽ አካባቢ የጄኖኤዝ ባሮክ ሥዕል ዋና ተዋናዮች ከሆኑት መካከል አንዱ በሆነው ቫሌሪዮ ካስቴሎ አውደ ጥናት ላይ በሸራ ላይ ሥዕል መሳል እና መምህሩ የሚሠራውን መጠነ-ሰፊ የፍሬስኮ ማስጌጫን መቅረጽ ይመርጥ እንደ ነበር እና ወደ አርባ የሚጠጉ የተቀረጹ ሳህኖች ከስሙ ጋር ሊገኙ መቻላቸው ታውቋል። በብዙ አጋጣሚዎች ግሬኬቶ ተብሎ ከሚጠራው ከታዋቂው የጄኖቫ የቅርጻ ቅርጽ ባለሞያ ጆቫኒ ቤኔዴቶ ካስቲሊዮን ሥራዎች ተመስጦ የተገኘ ይመስላል።

“አምላክ በልደቱ መላውን የሰው ዘር ወደ መለኮትነት መጠን ያስተዋውቃል፣ ስጦታውን ለመቀበል በእምነት ራሱን ለከፈተ እያንዳንዱ ሰው በመለኮታዊ ሕይወት ተሳትፎን ይሰጣል። እረኞቹ በቤተልሔም ሌሊት ሲናገሩ የሰሙት የመዳን ትርጉም ይህ ነው፡- ‘አዳኝ ተወልዶልሻል’ በማለት ተናግሯል (ሉቃ. 2፡11)። የድነት መንገድ በቤተሰብ ውስጥ ያልፋል፤ በቅድመ-ሰዋዊው የቃሉ አገባብ ብቻ ሳይሆን ከዚህም በላይ ከጌታ መወለድ ጋር በመምጣቱ ምክንያት ነው” (ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ - ታህሳስ 25/1994 እ.አ.አ.)።

 

30 December 2024, 16:31