ፈልግ

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቫቲካን የካርዲናሎች ጉባኤን ሲመሩ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቫቲካን የካርዲናሎች ጉባኤን ሲመሩ  (ANSA)

የካርዲናሎች ጉባሄ የሚያተኩረው በሕብረት፣ በሴቶች ሚና፣ በአለም ቀውሶች ላይ ነው።

በታህሳስ 22 እና 23/2017 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኛው በቅድስት ማርታ ቤት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በተገኙበት በተካሄደው የብፁዕን ካርዲናሎች በታኅሣሥ ወር የተካሄደው ጉባኤ፣ ቤተ ክርስቲያንና ዓለምን የሚመለከቱ በርካታ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ እና በቅርቡ በተካሄደው ሲኖዶስ ላይም ውይይት ተደርጎበታል። ስብሰባዎቹ በካርዲናሎች የተወከሉትን የተለያዩ ሀገራት ሁኔታ ላይ ለማሰላሰል እድል ሰጥተዋል "ስለ ግጭት እና ቀውስ ቀጣይ እውነታ ስጋቶችን እና ተስፋዎችን ለመጋራት" የተጠራ የካርዲናሎች ጉባኤ ነበር።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የአንድነት አገልግሎት፣ የሴቶች ሚና፣ በቅርቡ የተካሄደው ሲኖዶስ፣ በላቲን ቋንቋ "Praedicate Evangelium" (ወንጌልን መስበክ) በተሰኘው የሐዋርያዊ ሕገጋት በሀገረ ስብከቱ ኩርያ ውስጥ ያለው አፈጻጸም ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ሚና ፣ በቀውሶች እና ግጭቶች ውስጥ ለዓለማቀፉ እውነታ አሳሳቢነት እና በተስፋዎች በታኅሣሥ ወር የተነሱት የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ነበሩ። ርዕሰ ሊቀ ጳጳሳት ፍራንችስኮስን የሚረዱ እና የሚያማክሩ ዘጠኝ ካርዲናሎች ያሉት የሥራ ቡድን፣ C9 በመባል የሚታወቀው የካርዲናሎች ምክር ቤት ስብሰባ ነበር የተካሄደው።

በቤተክርስቲያን ውስጥ የሕበረት አስፈላጊነት

ስብሰባው ባለፈው ሰኞ ኅዳት 23 እና 24/2017 ዓ.ም የተካሄደ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት የምክር ቤቱ ካርዲናሎች የቅድስት መንበር የዜና ማተሚያ ክፍል እንደዘገበው፣ “በጉባኤው ላይ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ተብራርተዋል” በማለት ብፁዕ ካርዲናል ማርሴሎ ሰመራሮ የምክር ቤቱ ዋና ጸኃፍ አብራርተዋል፣ “በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስላለው ኅብረት በተለይም በልዩ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ስላለው ግንኙነት፣ ቤተ ክህነት፣ በቅርቡ በተጠናቀቀው ሲኖዶስ ላይ የጋራ ውይይት ተደርጓል" ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

የሴቶች ሚና

በተጨማሪም፣ በስብሰባዎቹ ወቅት፣ “ባለፉት አራት የካርዲናሎች ምክር ቤት ስብሰባዎች ላይ የተነሱትን ጉዳዮች ውህድ በመፈለግ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሴቶች ሚና ተዳሷል። በመጨረሻም - መግለጫው ይቀጥላል - የሐዋርያዊ ሕገጋቶችን በማንሳት መርሆች እና መመዘኛዎችን በማጥናትና በሥራ ላይ ለማዋል ተወስኗል፣ በላቲን ቋንቋ "Praedicate Evangelium" (ወንጌልን መስበክ) በተሰኘው የሐዋርያዊ ሕገጋት  በሀገረ ስብከቶች ደረጃ የሚተገበርበትን ሁኔታ፣  'የጳጳስ ተወካዮች ሚና በሲኖዶሳዊ ሚስዮናዊ እይታ' በሚል ርዕስ ከብፁዕ ካርዲናል ኦስዋልድ ግራሲያስ ጋር በተደረገ ውይይት የቦምቤይ ሊቀ ጳጳስ፣ የሚመለከተው የጥናት ቡድን ፕሬዝዳንት እንዲሆኑም ተወስኗል።

በቤተክርስቲያን እና በአለም ላይ ነጸብራቅ

የቫቲካን ፕሬስ ጽ/ቤት እንደዘገበው፣ “ጉባኤው በካርዲናሎች በተወከሉ የተለያዩ አካባቢዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን እና የዓለምን እውነታ በተመለከተ አጠቃላይ የማሰላሰል እድልን በማሳየት ቀጣይነት ባለው የግጭት ሁኔታዎች ላይ ስጋቶችን እና ተስፋዎችን ለመካፈል እድል ሰጥቷል" ሲል ገልጿል። ቀጣዩ የካርዲናሎች ምክር ቤት ስብሰባ እ.አ.አ በሚቀጥለው በመጋቢት ወር 2025 ዓ.ም ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዟል።

05 December 2024, 15:50