ፈልግ

2018.10.08 Asia Bibi 2018.10.08 Asia Bibi 

በፓክስታን ለአሲያ ቢቢ ምሕረት መደረጉ ተነገረ።

አሲያ በበኩልዋ የተሰማት ከፍተኛ ደስታ ገልጻ በጸሎት ለተባበሯት በሙሉ ምስጋናዋን አቅርባላቸዋለች።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የፓክስታን ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የእስምናን ሕይማኖት አጉድፋለች ወይም አሳንሳለች በሚል ወንጀል ክስ ተመስርቶባት በ2002 ዓ. ም. የሞት ፍርድ የተፈረደባትን የክርስትና እምነት ተከታይ አሲያ ቢቢን በነጻ ማሰናበቱ ታውቋል። የፓክስታን ጠቅላይ ፍርድ፣ በአገሩ የሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይ አሲያ ቢቢን ነጻ ማሰናበቱን ገልጿል። በ2001 ዓ. ም. በቁጥጥር ስር በመዋል፣ በ2002 ዓ. ም. የሞት ቅጣት ፍርድ የተበየነባት አሲያ የእስምናን ሕይማኖት አጉድፋለች ወይም አሳንሳለች በሚል ወንጀል በቁጥጥር ስር መዋሏን ገልጾ ከቀረበባት  ክስ በአስቸኳይ ነጻ እንድትሆን ትዕዛዝ ማስተላፉር ይፋ አድርጓል። አሲያ በበኩልዋ የተሰማት ከፍተኛ ደስታ ገልጻ በጸሎት ለተባበሯት በሙሉ ምስጋናዋን አቅርባላቸዋለች። የአሲያን ጉዳይ ከመጀመሪያው ጀምሮ ይከታተል የነበረው አቶ ዮሴፍ ናዲም “vatican insider” ለተባለ መጽሔት በላከው መልዕክት፣ ፍትህ በተግባር ታይቷል፣ አሲያም ነጻ ወጥታለች በማለት የተሰማውን ደስታ ገልጾ “Renaissance Education Foundation” የተባለ ድርጅትን አመስግኗል።

በአገሩ ለሰብዕዊ መብት የቆመ ድርጅትና የክርስቲያን ማሕበረሰብ በጋራ ሆነው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ በደስታ ተቀብለዋል። በሌላ በኩል የሀገሩ የእስልማና ሐይማኖት ተቋማት ከፍተኛ ማስጠንቀቂያ ያስተላለፈ ሲሆን ከሦስት መቶ የጸጥታ አስከባሪ ፖሊሶች የፍርድ ቤቱን አካባቢ ጸጥታን ለማስከበር መሰማራታቸው ታውቋል። በአገሩ ቴሪክ ኤ ላባይክ ፓክስታን የተባለ እስላማዊ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ የሆኑት ካዲም ሁሴን ሪዝቢ ብሔራዊ ተቃዉሞ እያተባበሩ መሆናቸው ታውቋል።

የአሲያ ቢቢ ወላጆች በቫቲካን ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችንሶ ጋር፣

ባለፈው ዓመት የካቲት ወር ላይ የአሲያ ልጅ ኤሻም እና ባሏ አቶ አሺክ እንዲሁም በቦኮ ሐራም ታግታ የቆየች ናይጀሪያዊ ተወላጅ እርብቃ ወደ ሮም መጥተው እንደነበር ታውቋል። በዚህ ወቅት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አሲያ ቢቢን በጸሎታቸው እንደሚያስታውሷት ቃል መግባታቸው ይታወሳል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ለአሲያ ቤተሰቦች ባስተላለፉት መልዕክታቸው በአንድነት ሆነው በጸሎት እንዲበረቱ ማሳሰባቸው ይታወሳል። 

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት ይጫኑ
31 October 2018, 15:30