ፈልግ

የምግብ ዕርዳታ ስርጭት በቺሊ፤ የምግብ ዕርዳታ ስርጭት በቺሊ፤  

በኮቪድ-19 ምክንያት በዓለማችን 130 ሚሊዮን ሰዎች ለረሃብ ሊጋለጡ ይችላሉ ተባለ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሕዝቦችን እያስጨነቀ የሚገኝ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በዓለማችን ውስጥ 130 ሚሊዮን ሰዎችን ለረሃብ ሊዳርጋቸው እንደሚችል አስጠንቅቋል። ድርጅቱ በሪፖርቱ፣ ወረርሽኙ በሕዝቦች ጤና ላይ ጉዳት ከማስከተሉ በተጨማሪ ለረሃብ አደጋም ሊያጋልጣቸው የሚችል መሆኑን አስታውቋል። የወረርሽኙን መዛመት ለመቀነስ ተብሎ የተወሰዱት አንዳንድ እርምጃዎች፣ ከእነዚህም መካከል በቤት እንዲቆዩ ተብሎ የወጣው ደንብ በምግብ አቅርቦት፣ በማከፋፈል አገልግሎት፣ በገበያ ሥርዓት እና በፍጆታ ላይ እንቅፋት ከመፍጠር ጋር ተያይዞ በርካታ ሰዎችን ለረሃብ ሊያጋልጥ እንደሚችል፣ የተለያዩ ድርጅቶች የዓለማችንን ዓመታዊ የምግብ መጠን እና ዋስትናን አስመልክተው ባወጡት ዓመታዊ ሪፖርታቸው አስታውቀዋል።

የቫቲካን ዜና፤

የረሃብተኛ ቁጥር መጨመር፤

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ድርጅቶች በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሊደርስ የሚችል የምግብ እጥረት አደጋን ከወዲሁ መተንበይ ባይቻልም ቅድመ ጥናቶቹ እንደሚያመላክቱት ከተገመተው 130 ሚሊዮን ተጠቂዎች በተጨማሪ ተጨማሪ 83 ሚሊዮን ሰዎች በአውሮጳዊያኑ 2020 ዓ. ም. የተመጣጣኝ ምግብ እጥረት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል አሳስበዋል። ሪፖርቱ እንዳስታወቀው፣ የምግብ አቅርቦት ማነስ፣ የሰዎች ወርሃዊ ገቢ መቀነስ፣ በወረርሽኙ የሚሞቱ ሰዎች መጨመር፣ ዳያስፖራ የሚላክ የገንዘብ እርዳታ መቋረጥ ብዙዎችን በችግር ውስጥ መጣሉ በተለይም ድሃው ማኅበረሰብ በቂ እና ተመጣጣኝ ምግብ እንዳያገኝ ማድረጉን ዓመታዊ ሪፖርቶች አመልክተዋል።

ለረጅም ጊዜ የዘለቀ የምግብ ማነስ ችግር፤

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዓመታዊ ሪፖርቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አስቀድሞም ቢሆን በዓለማች ውስጥ የነበረውን የምግብ እጥረ ወደ ከፋ ደረጃ ማድረሱን ገልጾ፣ ከጎርጎሮሳዊያኑ 2014 ዓ. ም. ጀምሮ በዓለማችን ውስጥ የምግብ መጠን እየቀነሰ መምጣቱን አስታውቋል። የ2019 ዓ. ም. ሪፖርት እንደሚያሳየው ከዓለማችን ሕዝቦች መካከል 8.9 ከመቶ፣ ይህም ወደ 690 ሚሊዮን የሚጠጉ የዓለማችን ሰዎች በከፍተኛ ረሃብ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን አስታውቆ፣ ከጎርጎሮሳዊያኑ 2014 ዓ. ም. ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የረሃብተኛ ቁጥር በ60 ሚሊዮን የጨመረ መሆኑን አመልክቷል። ዓለማችንን ያጋጠመው የምግብ እጥረት በዚህ መልኩ የሚቀጥል ከሆነ እስከ ጎርጎሮሳዊያኑ 2030 ዓ. ም. ድረስ በቂ እና ተመጣጣኝ ምግብን በማጣት በረሃብ የሚሰቃይ የዓለማችን ሕዝብ ቁጥር ከ840 ሚሊዮን በላይ እንደሚሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።

ከረሃብ ነጻ የሚሆኑበት ጊዜ ገና ነው፤

ከፍተኛ የምግብ እጥረት የሚታይበት የዓለማችን ክፍል የእስያ አህጉር መሆኑን ያስታወቀው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሪፖርት፣ የምግብ እጥረት በአፍሪቃ ውስጥ በፍጥነት እያደገ መሆኑን አስታውቋል። ሪፖርቱ ከዚህ ጋር በማያያዝ በደቡብ እስያ እና ከሰሃራ በታች ባሉት የአፍሪቃ አገሮች 57 ከመቶ የሚሆኑ ሕዝቦች በቂ እና ተመጣጣኝ ምግብ የማያገኙ መሆኑን አስታውቋል። በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ ውስጥ በአንዳንድ አካባቢዎች የምግብ ዋስትና እየቀነሰ መምጣቱን የተባበሩት መንግሥታት አክሎ አስታውቋል። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በጎርጎሮሳዊያኑ 2030 ዓ. ም. ዓለማችንን ከረሃብ ነጻ ለማውጣት የተወጠነው እቅድ ተግባራዊነት ጥርጣሬ ውስጥ መክተቱን ድርጅቱ አስታውቋል።  

15 July 2020, 18:31