ፈልግ

በቅርቡ በኢንዶኔዢያ ተከስቶ የነበረው ከፍተኛ ጎርፍ በቅርቡ በኢንዶኔዢያ ተከስቶ የነበረው ከፍተኛ ጎርፍ  

በግጭቶች እና በተፈጥሮ አደጋዎች በዐስር ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን መፈናቀላቸው ተገለጸ።

በቅርቡ የተቋቋመው በአንድ አገር ውስጥ የሚከሰቱትን ውስጣዊ መፈናቀሎችን የሚከታተለው ተቋም (IDMC) በአወጣው አመታዊ ሪፖርት እንደ ገለጸው እ.አ.አ በ2020 ዓ.ም በጭቶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች በሕዝብ ላይ የሚያስከትለውን አስከፊ ውጤት የያዘ ሪፖርት ይፋ ማደረጉ የተገለጸ ሲሆን ግኝቶቹ እንዳመላከቱት እስከ ባለፈው ዓመት መጨረሻ ድረስ 55 ሚሊዮን ሰዎች በአገራቸው ውስጥ መፈናቀላቸውን ገልጿል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የተፈጥሮ አደጋዎች እና ግጭቶች ባለፈው ዓመት ሚሊዮኖች በአገራቸው ውስጥ እንዲፈናቀሉ ያስገደዱ ሲሆን አንዳንድ ጊዜ በዓለም ዙሪያ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ተቋሙ እንደ ገለጸው እጅግ አስደንጋጭ በሆነ መልኩ በቁጥር እያሻቀበ መምጣቱን እና በሚልዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለከፋ ስቃይ እየዳርገ መሆኑን ሪፖርቱ አክሎ ገልጸዋል።

በሀገር ውስጥ የተፈናቃዮች ቁጥጥር ማዕከል ባለፈው ሳምንት ሐሙስ እለት ባወጣው የቅርብ ጊዜ ሪፖርት እ.አ.አ በ 2020 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ቢያንስ 55 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች በአገር ውስጥ የተፈናቀሉ እንደ ነበሩ ገልጿል።

አሁን በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ሀገሮች በቤት ውስጥ የመቆየት አስገዳጅ ገደቦች ቢኖሩም ፣ በአገር ውስጥ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ድንበር ተሻግረው ከሚሰደዱ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ይበልጣል።

መፈናቀልን የሚያስገድዱ ሁከት እና አደጋዎች

በሪፖርቱ መሠረት እ.አ.አ በ2020 ዓ.ም 48 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በአመፅ እና በግጭት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን የተቀሩት 7 ሚሊዮኖች ደግሞ በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ተፈናቅለዋል።

ከዚህ ቁጥር ውስጥ ወደ 20 ሚሊዮን የሚሆኑት ተፈናቃዮች ከአስራ አምስት አመት በታች የሆኑ እና ከ 2.6 ሚሊዮን በላይ ደግሞ ከ 65 በላይ እድሜ ያላቸው ሰዎች ናቸው። 10.5 ሚሊዮን የሚሆኑት ከ 15 እስከ 24 ዓመት ባለው የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ ከፍተኛው ቁጥር ያላቸው ተፈናቃዮች ቁጥር ያለው የዕድሜ ክልል ደግሞ ከ 25 እስከ 64 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ሲሆኑ በቁጥር ወደ 22 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ሰዎች እንደ ሆነ ሪፖርቱ አክሎ ገልጿል።

በገዛ አገራቸው ውስጥ የተፈናቀሉትን ሰዎች በተመለከተ ተቋሙ ባለፈው ሐሙስ ባወጣው ሪፖርት ይፋ የተደረገው ዘገባ ባለፈው ዓመት እንደ ኢትዮጵያ ፣ ሞዛምቢክ እና ቡርኪናፋሶ ባሉ አገራት ካሉ ጽንፈኛ ቡድኖች የሚመጡ ጥቃቶች እየተባባሱ መምጣታቸውን አመልክቷል።

በተመሳሳይ ጊዜ እንደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፣ ሶሪያ እና አፍጋኒስታን ባሉ ስፍራዎች ለረጅም ጊዜ የቆዩ ግጭቶች ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል።

በቅርቡ የተቋቋመው በአንድ አገር ውስጥ የሚከሰቱትን ውስጣዊ መፈናቀሎችን የሚከታተለው ተቋም ግኝቶች እንደ ሚያመለክቱት የደቡብ እስያ ክልል እ.ኤ.አ. በ 2020 ዓ.ም በዓለም ላይ ከተከሰተው ውስጣዊ መፈናቀል አዲስ የአስቸኳይ አደጋ ምደባ አንድ ሦስተኛ ያህል ድርሻ እንደነበረው አመልክቷል ምክንያቱም አንፋን በመባል የሚታወቀው አውሎ ነፋስ በግንቦት ወር በባንግላዴሽ ፣ በቡታን ፣ በሕንድ እና በማያንማር ወደ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ማፈናቀሉ ይታወቃል። በተጨማሪም ባለፈው አመት ሰኔ ወር በአከባቢው የዘነበው ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ እና የጎርፍ መጥለቅለቅ ከሰኔ ወር ጀምሮ በተለይም ባንግላዴሽ ላይ መላውን ክልል በመጎዳቱ የተነሳ ብዙ ሰዎች ለመፈናቀል ተገደው ነበር።

በተጨማሪም በቅርቡ የተቋቋመው በአንድ አገር ውስጥ የሚከሰቱትን ውስጣዊ መፈናቀሎችን የሚከታተለው ተቋም ያወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው ግጭቶች እና የተፈጥሮ አደጋዎች በተከሰቱባቸው የዓለማችን አከባቢዎች ብዙ ሰዎች አከባቢያቸውን ጥለው እንዲሸሹ በማድረግ ባለፈው ዓመት ለ 40.5 ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀል አስተዋጽኦ አድርገዋል - ይህ ከአስር ዓመት በኋላ በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት የደረሰው ከፍተኛ መፈናቀል ነው።

በተፈጥሮ አደጋ ​​ምክንያት ከፍተኛ የሆነ ውስጣዊ መፈናቀል የደረሰባቸው አገራት በቅደም ተከተል ሲቀመጥ አፍጋኒስታን (1.1 ሚሊዮን) ፣ ህንድ (929,000) እና ፓኪስታን (806,000) ሲሆኑ በግጭት ምክንያት ከፍተኛ ተፈናቃዮች ያሉት ደግሞ ሶሪያን (6.6 ሚሊዮን) ፣ ኮንጎ (5.3 ሚሊዮን) ፣ እና ኮሎምቢያ (4.9 ሚሊዮን) እንደ ሆነም ተዘግቧል።

በአጠቃላይ ባለፈው ዓመት በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ከፍተኛ በአገር ውስጥ የተፈናቃዮች ቁጥር ያላት ሀገር ቻይና ስትሆን በአጠቃላይ ከአምስት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፣ ከቻይና በመቀጠል ደግሞ ፊሊፒንስ ፣ ባንግላዴሽ እና ህንድ እንደ ሚከተሉ በቅርቡ የተቋቋመው በአንድ አገር ውስጥ የሚከሰቱትን ውስጣዊ መፈናቀሎችን የሚከታተለው ተቋም ባለፈው ሐሙስ ባወጣው ሪፖርት ገልጿል።

27 May 2021, 16:20