ፈልግ

አንድነትን እና ኃላፊነትን የሚገልጹ እጆች አንድነትን እና ኃላፊነትን የሚገልጹ እጆች 

ከሰላሳ በላይ የሚሆኑ ምርጥ የፈጠራ ሥራዎች ለሽልማት መመረጣቸው ተገለጸ

በሮም የንግድ ምክር ቤት ውስጥ ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎች ብሔራዊ ማህበር፥ እንደ ጎርጎሮሳዊው በ2023 ዓ. ም. ያዘጋጀውን ሽልማት ለአሸናፊዎች መስጠቱ ተገለጸ። በንግዱ ዓለም እና በጅምር ላይ ለሚገኙ ምርጥ የፈጠራ ሥራዎች ከተሰጣቸው ከሰላሳ በላይ ሽልማቶች መካከል አንዱ፥ ወጣቶችን በመደገፍ፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂን በማሳደግ እና አካታችነትን በማስተዋወቅ ላይ የሚገኝ የቅድስት መንበር የመገናኛ ጽሕፈት ቤት እንደሆነ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎች ብሔራዊ ማህበር እና የሮም ንግድ ምክር ቤት በጋራ ያዘጋጁት ስድስተኛ ዙር የ 2023 ዓ. ም. የሽልማት ሥነ-ሥርዓት መካሄዱ ታውቋል። በጀማሪ የቢዝነስ ዓለም ውስጥ የሚገኙትን ምርጥ የሥራ ዕቅዶችን ለመሸለም እና በአንዳንድ የሲቪል ማኅበረሰብ ውስጥ የሚገኙትን፣ በዋና ተዋናይነት እና በአስፈላጊ ሙያዊ ሥራቸው ራሳቸውን ለገለጹት ከ30 በላይ የፈጠራ ባለሙያዎች ሽልማት ተሰጥቷል።

በሽልማት አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የጣሊያን እና የአውሮፓ ተቋማት ተወካዮች የተገኙ ሲሆን፥ በይዘቱ የመጀመሪያ ስኬት የታየበት እንደ ነበር ተመልክቷል። ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎች ብሔራዊ ማኅበር ፕሬዝደንት አቶ ገብሪኤሌ ፌሪዬሪ በሽልማቱ ወቅት በሰጡት አስተያየት፥ “ወጣቱን ትውልድ መደገፍ እና የጣሊያንን የላቀ ብቃት እና ተሰጥኦን ማሳደግ፥ ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎች ብሔራዊ ማኅበር ተልዕኮ መሠረታዊ ምርጫ ነው” በማለት አስረድተዋል። “ፈጠራን፣ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እና ዘላቂ ልማትን በአጀንዳው በማካተት የአገራችንን ሥነ-ምህዳር እንደገና ለማስጀመር ይበልጥ ኢንቨስት ማድረግ አለብን” ብለዋል የማኅበር ፕሬዝደንት አቶ ገብሪኤሌ ፌሪዬሪ።

ከተሸላሚዎቹ መካከል አንዱ የሆኑት እና በቅድስት መንበር የኮሚዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ዶ/ር ፓውሎ ሩፊኒ በዕለቱ ባሰሙት ንግግር፥ ወጣቶችን በመደገፍ ዘላቂነትን የብልጽግና እና የደኅንነት መርሆች ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸው፥ ፈጠራን እንደ አካታችነት በመመልከት ማኅበረሰብን ለመደገፍ የሚደረግ አንድነት እንደሆነ አስረድተዋል።

 

12 December 2023, 16:11