ፈልግ

የፍልስጤም እና የእስራኤል ጦርነት የፍልስጤም እና የእስራኤል ጦርነት  (AFP or licensors)

በጋዛ ውስጥ ሕጻናት የመኖር ህልውናቸውን ለማረጋገጥ ጥረት እያደረጉ እንደሚገኙ ተገለጸ

በጋዛ ውስጥ ግጭት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናት ለከፋ የሕይወት መጥፋት እና መፈናቀል፣ ለአሰቃቂ ክስተቶች እና ጉዳቶች ተጋርጠዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ሰሜናዊው ጋዛ ከዕድገት ተቆርጧል ማለት ይቻላል። ወደ 300,000 የሚገመት ሕዝቦቿ የመኖር ህልውናቸው ወድቋል። ከደቡብ ጋዛ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች በራፋህ እና አካባቢው ወደሚገኙ ቦታዎች የሸሹት ተፈናቃዮች በተጨናነቀ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ።

ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ13,000 በላይ የጭነት መኪናዎች፣ ከ250,000 ቶን በላይ የሰብዓዊ ዕርዳታ ቁሳቁሶች ወደ ጋዛ ሰርጥ ቢገባም የምግብ፣ የመድሃኒት እና የሌሎች አስፈላጊ ነገሮች አቅርቦት ዝቅተኛ ነው።

በዚህ ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ሕጻናት ቆስለዋል፣ ተገድለዋል። የዕርዳታ ኤጀንሲዎች በእሳት የተቃጠሉ፣ የቆሰሉ እና ሌሎች ከባድ ጉዳቶች የደረሰባቸውን ሕጻናት ወደ ሆስፒታሎች ያመጣሉ። በዚህ ምክንያት ሕጻናት ከዚህ በፊት ሲደረግላቸው ከነበረው ሥነ-ልቦናዊ እና ማኅበራዊ እንክብካቤዎች ተለይተዋል።

በልጆች ላይ የሚከሰቱ ሕመሞች

በተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት “ዩኒሴፍ” በቅርቡ ባወጣው መግለጫ፥ በጨቅላ ሕጻናት ላይ የተከሰተው የተቅማጥ በሽታ ከጊዜ ወደ ጊዜ መስፋፋቱን ገልጾ፥ የቆዳ እና የመተንፈሻ አካላት በሽታዎች በልጆች ላይ እየጨመሩ መምጣታቸውን አስታውቋል።

ጉዳዩን የሚያወሳስበው በጋዛ ሰርጥ በሚገኙ ሕጻናት፣ ነፍሰ ጡር ሴቶች እና በሚያጥቡ ሴቶች ላይ የሚታይ የተመጣጣኝ ምግብ እጥረት በጤናቸው ላይ ከፍተኛ ስጋት መፍጠሩን በግሎባል የሥነ-ምግብ ጥናት መርሃ ግብርን የሚከታተል ድርጅት በጠቅላላ ትንታኔው ላይ አስታውቋል።

በሌላ በኩል የእስራኤል የጦር ካቢኔ በፓሪስ በተካሄደው የተኩስ አቁም ድርድር፥ በጋዛ ጦርነቱ የሚቆምበት እና ታጋቾች የሚለቀቁበትን ጊዜ በተመለከተ ዝርዝር ስምምነት ላይ መደረሱ ተዘግቧል።

 

26 February 2024, 16:49