የአንታርኪቲካ አከባቢ ሙቀት መጨመር የአየር ንብረት ለውጥን ሊያፋጥን ይችላል መባሉ ተገለጸ!
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
የአየር ንብረት ለውጥ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩን እንደቀጠለ ነው፣ የአታርኪቲካ ክልሎችም እኛ በምናሳየው ችልተኝነት በጸጥታ እየተበላሹ ይገኛሉ። የአንታርኪቲካ ባህር የበረዶ መጠን ባለፉት አስር አመት ውስጥ ብቻ በ13 በመቶ እየቀነሰ ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታ የበረዶ መጠን እየቀነሰ ይገኛል። በዚህም ምክንያት የአርክቲክ ባህር ደረጃዎች በአስጨናቂ ሁኔታ መጠኑ እየጨመረ ነው፣ አሁን በዓለም አቀፍ ደረጃ በውቅያኖስ ደረጃ መጨመር 35% ይሸፍናል። ይህ በአርክቲክ የዱር አራዊት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል፣ በቀጥታ በበረዶ ላይ ጥገኛ የሆኑ ዝርያዎችን ሕልውና አስፈሪ ያደርገዋል፣ ነገር ግን በተዘዋዋሪ ከበረዶ-ነጻ የሆኑ ፍጥረታትንም አደጋ ላይ ይጥላቸዋል።
በሜሲና (ጣሊያን) ክፍል ውስጥ የዋልታ ሳይንስ ተቋም ኃላፊ የሆኑት ማውሪዚዮ አዛሮ “ይህ እየሆነ ያለው የአንታርኪቲካ ውቅያኖስ ከዓለማችን በአራት እጥፍ ገደማ ስለሚሞቅ ነው” ብለዋል። ክስተቱ የአንታርኪቲካ በርዶ መቅለጥ መስፋፋት (Arctic Amplification) በመባል የሚታወቀው ሲሆን፣ ሁኔታው አሁን በጥሩ ሁኔታ የተመዘገበ እና በሳይንስ ማህበረሰብ ዘንድ እውቅና ያገኘ ነው።
“የአርክቲክ መስፋፋት እየተከሰተ ያለው አንዱ ምክንያት አርክቲክ ከፍተኛ መጠን ያለው በረዶ እና ልም በረዶ ስላለው በጣም ነጭ በመሆኑ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ያንን ነጭ ስፋት ሲያቀልጥ፣ ጠቆር ያለ ገጽ ይመረታል እና ይጋለጣል፣ እናም ጠቆር ያሉ ቦታዎች የፀሐይ ብርሃንን ይቀበላሉ” ከእዚያም የሙቀት መጠን እንዲጨምር በማድረግ በረዶ እንዲቀልጥ ምክንያት ይሆናሉ ሲሉ አዛሮ ገልጿል። "ይህ (ice-albedo) የበረዶ-ፅብርቅ ግብረመልስ በመባል ይታወቃል"።
"ሌሎች አሉታዊ ግብረመልሶች የአርክቲክ በረዶ መቅለጥ መስፋፋት በማባባስ የደመና ግብረመልስ እና የውቅያኖስ ግብረመልስን ጨምሮ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ" ሲል አዛሮ አክሎ ገልጸዋል።
የአርክቲክ የበረዶ መቅለጥ መስፋፋት ወይም የበረዶ መቅለጥ ምክንያት በተቀረው ዓለም ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ የሙቀት መጨመር ለውጦች በአርክቲክ ክልሎች ከሶስት እስከ አራት እጥፍ በፍጥነት ይከሰታሉ። ጥልቅ ጭንቀትን በመግለጽ "አርክቲክ እንደምናውቀው በጣም በፍጥነት እየጠፋ ነው" ሲሉ አቶ አዛሮ ተናግረዋል።
በግሪንላንድ ውስጥ በበረዶ ግግር የተሞላ አለታማ በሆኑ ተራሮች እና ኮረብቶች ላይ ያሉ የዱር አበቦች የአርክቲክ መስፋፋት ባስከተለው መዘዝ በአለም አቀፍ ሙቀት ላይ ያለው ተጽእኖ በመጨመሩ የተነሳ ለከፍተኛ አደጋ እየተጋለጡ ይገኛሉ።
ይሁን እንጂ የአርክቲክ አከባቢ መስፋፋት ተጽእኖ በአርክቲክ ክልሎች ብቻ ተወስኖ የሚቀር ላይሆን ይችላል። የለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ተመራማሪዎች ባደረጉት አዲስ ጥናት አርክቲክ በረዶ መቅለጥ መስፋፋት የፓሪስ ስምምነትን 2 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በመጣስ ከስምንት ዓመታት በፊት አካባቢው በአማካይ በአለም አቀፍ ደረጃ እየሞቀ ከነበረው ይልቅ የባሰ እንዲሆን በማድረግ ረገድ የአርክቲክት በረዶ መቅለጥ መስፋፋት የአንበሳውን ሚና ይጫወታል።
"ለበርካታ ሰዎች የፓሪስ ስምምነት የሙቀት ደረጃዎች የአየር ንብረት ለውጥን የመረዳት እና የመለካት ዋና መንገዶች ናቸው" ሲሉ የለንደን የሳይንስ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ ክፍል እጩ ዶክተር እና የጥናቱ መሪ ጸኃፊ አሊስቴር ዱፌይ ተናግረዋል ። "የእኛ ጥናት አላማ የአርክቲክ የአየር ንብረት ለውጥ ለሰዎች በሚታወቅ መልኩ ለመተርጎም እና ለማስረዳት ያለመ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ጥናቱን ለማካሄድ ተመራማሪዎቹ የወደፊቱን የአየር ንብረት ለውጥ ትንበያ ከአርክቲክ በረዶ መቅለጥ መስፋፋት ጋር እና ያለአርክቲክ ክልል መስፋፋትን አወዳድረዋል። "ይህ የአርክቲክ በረዶ መቅለጥ መስፋፋት ቀጥተኛ ተጽእኖን ለመለካት ያስችለናል" ሲል እጩ ዶክተር አሊስተር ዱፌይ ገልጿል።
እንደ ሳይንቲስቶች ገለጻ ከሆነ በአርክቲክ ውስጥ ያለው ተጨማሪ ሙቀት አምሳያዎቹ ወደ 1.5 ° ሴ እና 2 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ደረጃዎች ሲደርሱ ወደ አምስት እና ስምንት አመታት ልዩነት ይተረጉማል። "በዘዴዎች መሰረት፣ አርክቲክ በረዶ መቅለጥ መስፋፋት አለም የፓሪስን ስምምነት የሚጥስበትን ጊዜ ይጎትታል" ሲል እጩ ዶክተር አሊስተር ዱፌይ ገልጿል።
የአርክቲክ በረዶ መቅለጥ መስፋፋት ሌሎች አሉታዊ ውጤቶችም አሉት። "የአርክቲክን የበረዶ ግግር በሚቀልጥበት ጊዜ በሰሜናዊው የአለም ንፍቀ ክበብ፣ ፐርማፍሮስት በመባል የሚታወቀውን በቋሚነት የቀዘቀዘውን የመሬት ክፍል ያቀልጣቸዋል" ሲሉ ዱፌይ ተናግሯል። "ይህ ደግሞ ሚቴን እና የካርቦን ዳይኦክሳይድ ልቀቶችን በመጨመር የግሪንሀውስ ጋዞችን በአለም ሙቀት ላይ መጨመር ይችላል" ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ አዛሮ በበኩላቸው ጉዳዩን በተመለከተ ሲናገሩ "የፐርማፍሮስት መቅለጥ በእንቅልፍ ላይ ያሉ ጥንታዊ ቫይረሶች እና ባክቴሪያዎች እንዲቀሰቀሱ እንዲሁም የመሬት መንሸራተትን እና ሌሎች የስነ-ምድር አደጋዎችን ሊያመጣ ይችላል" ሲሉ አቶ አዛሮ ገልጿል። "በሕይወት እና በአካባቢ ላይ የሚያስከትለው መዘዝ አስከፊ ሊሆን ይችላል" ሲሉ ስጋታቸውን አክለው ገልጸዋል።
የበረዶ ግግር መቅለጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ንፁህ ውሃ መጨመር የውቅያኖስ ዝውውርን ሊያስተጓጉል ስለሚችል የባህር ውስጥ ፍጥረታትን በቀጥታ እንደሚጎዳ ጥናቶች ይጠቁማሉ።
"በተጨማሪም በአርክቲክ ውስጥ ያለው ተጨማሪ ሙቀት እና የባህር በረዶ መጥፋት በሰሜናዊው የምድር ንፍቀ ክበብ ካለው ከፍተኛ የአየር ሁኔታ ጋር በቀጥታ የተገናኘ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ አለ" ሲል አቶ አዛሮ አክለው ገልጸዋል።
ተስፋዎች
"የአርክቲክ ሙቀት መጨመር በአየር ንብረት ትንበያዎች ላይ እርግጠኛ አለመሆንን ይጨምራል" ሲሉ እጩ ዶክተር አሊስተር ዱፌይ ተናግሯል። "ይህ የሆነበት ምክንያት በሳይንሳዊ ማህበረሰቡ ውስጥ የአርክቲክ ሙቀት መጨመር እና መስፋፋት መጠኖች አንዳንድ ልዩነቶች ስላሉ ይህም ወደፊት የተለያዩ የአየር ሁኔታ ትንበያዎችን ስለሚነካ ነው" ብለዋል።
"የአርክቲክ አከባቢ ሙቀት መጨመር እና ሁሉንም መንስኤዎቹን የበለጠ ለመረዳት ተጨማሪ ጥናቶች ያስፈልጋሉ። ይህ የወደፊቱን የአየር ንብረት ዘዴዎችን ሊያሻሽል ይችላል” ሲሉ እጩ ዶክተር አሊስተር ዱፌይ ገልጸዋል።
አቶ አዛሮ በበኩላቸው "የዓለም ሙቀት መጨመር በአሁኑ ጊዜ የረጅም ጊዜ፣ ተፈጥሯዊ ልዩነቶች እርስ በርስ የሚጋጩበት እና በሰው-ተኮር ለውጦች የሚፈጠሩበት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣ የመሬት ገጽታ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።