ፈልግ

እስራኤል በራፋህ የወሰደችውን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በራፋህ የወሰደችውን ጥቃት ተከትሎ 

በጋዛ የእርቅ ውይይቶች ላይ መሻሻሎች እየታዩ እንደእሆነ ዘገባዎች እያሳዩ ነው

አንድ የእስራኤል ባለስልጣን እንደተናገሩት በፈረንሳይ ሲካሄድ የነበረው የእስራኤል - ሃማስ ግጭት የተኩስ አቁም ውይይት ውጤታማ እንደ ነበር ገልጸዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የሞሳድ የስለላ ድርጅት ሃላፊ በሆኑት ዴቪድ ባርኔያ የሚመራው የእስራኤል ልኡካን ቅዳሜ ጧት ወደ እስራኤል ተመልሷል።

የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን እንደዘገቡት በኳታር እና በአሜሪካ ልዑካን አሸማጋይነት በተደረገው ድርድር መሻሻል ታይቷል ብለዋል።

ይሁንና በእስራኤል እና በሃማስ መካከል ያለውን ክፍተት ለማስተካከል ተጨማሪ ስራ እንደሚያስፈልግ የእስራኤል ቲቪ ዘግቧል።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የቅርብ አጋሮች ቅዳሜ በተደረገው ውይይት ውጤት ዙሪያ ሰሞኑን መረጃ ይደርሳቸዋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ታውቋል።

የሟቾች ቁጥር ማሻቀቡን ቀጥሏል

ከቅዳሜ ቀደም ብሎ የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደዘገበው እስራኤል በጋዛ ላይ እየወሰደችው ባለው ጥቃት የሞቱት ፍልስጤማዊያን ቁጥር ወደ 29,606 ከፍ ማለቱን አሳውቋል።

በተጨማሪም በሃማስ የሚተዳደረው የሚዲያ ፅህፈት ቤት በበኩሉ እንዳስታወቀው ባለፈው ዓመት በተጀመረው ግጭት እስከ አሁን 132 የፍልስጤም ጋዜጠኞች በእስራኤል ጦር መገደላቸውን ገልጿል።

ለፍልስጤም መንግስት እውቅና ለመስጠት የተደረጉ ጥሪዎች

ባለፈው አርብ ዕለት የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፥ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን ከጦርነቱ በኋላ የእስራኤልን የፀጥታ ጥበቃ በጋዛ ላይ ማጠንከር እንዳለበት የሚገልፀውን በጋዛ ሰርጥ ላይ ሊተገብሩት ያቀዱትን እቅድ ውድቅ አድርጎታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የፍልስጤም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋሽንግተን እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለፍልስጤም መንግስት እውቅና እንዲሰጡ እና በተመድ ውስጥ ሙሉ አባልነቷን እንድታገኝ ግፊት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
 

26 February 2024, 14:52