ፈልግ

ፀረ-ስደተኛ አመፅን በመቃወም በለንደን የተሰባሰቡ ሰዎች ፀረ-ስደተኛ አመፅን በመቃወም በለንደን የተሰባሰቡ ሰዎች  (CHRIS J RATCLIFFE)

የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ በእንግሊዝ የተነሳው አመጽ እንዲቆም እና ሰላም እንዲሰፍን ጠየቁ

በዩናይትድ ኪንግደም የተነሳው አመፅ ተቀጣጥሎ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት የካንተርቢ ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብጹእ አቡነ ጀስቲን ዌልቢ የብጥብጡ እና የጥቃቱ ሰለባዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው፣ ለግጭቱ መፍትሄ እንዲመጣ ከተፈለገ በሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች ብቻ ጥያቄ ማቅረብ እንደሚገባ በመግለጽ የሰላም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ባለፈው ሳምንት ሃምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም. በሳውዝፖርት ከተማ ሦስት ታዳጊ ሴቶች በቢላ ክፉኛ ተወግተው ከተገደሉ በኋላ ነው በእንግሊዝ እና በሰሜን አየርላንድ ባሉ ከተሞች ውስጥ አመፁ የተነሳው። ይህን አመፅ ተከትሎ በተለይ በማኅበራዊ ሚድያዎች ሐሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ ሲሆን፣ አክራሪ ቀኝ ዘመም እና ፀረ-ስደተኛ ሐሳቦች እየተንፀባረቁ ይገኛሉ።

በብሪታንያ ውስጥ ከተፈፀሙ የቅርብ ጊዜ ክስተቶችን መሃል በየትኛውም ዓመት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እጅግ የከፋ የፀረ-ሴማዊነት ተግባራትን እያስተናገደች በምትገኘው ዩኬ፣ የሃይማኖት መሪዎች በመላ አገሪቱ እየተከሰተ ያለውን ይሄንን የጸረ-ሙስሊም አመፅ ማውገዛቸውን ቀጥለዋል።

ሁሉም የብሪታንያ ዜጋ “የመከበር መብት እና ሌሎችን የማክበር ሃላፊነት አለበት” በማለት ጥላቻን እና ጭካኔን በመቃወም ብጹአን ጳጳሳቱ አንድ ሆነዋል። ከእነዚህም መሃል የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ ጀስቲን ዌልቢ ሲሆኑ፥ ብጹእነታቸው ከሃይማኖት መሪዎቹ ጋር በመሆን ለተጎዱት ማህበረሰቦች በሙሉ የሰላም ተስፋን በማሰራጨት፣ ለቆሰሉት፣ የህዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ በትጋት እየሰሩ ለሚገኙ የፖሊስ አባላት እና ለአምልኮ ቦታዎች እንዲሁም የተለያየ ሃይማኖት ለሚከተሉ እና በጎ ፈቃድ ላላቸው ሰዎች በመጸለይ አብሮነታቸውን አሳይተዋል።

ሊቀ ጳጳስ ዌልቢ ከቢቢሲ ሬድዮ አራት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “በአመፃ የሚካሄድ ማንኛውም ተቃውሞ ሰዎችን ከዓላማቸው ያስታሉ” በማለት የአመጽ አካሄድን በመቃወም አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን፥ “ሰላማዊ የሆኑ ሰልፎች ግን መንስኤው ምንም ይሁን ምን በወንጀል ከሚቀሰቀስ ሁከት ይልቅ በአሥር ሺህ ጊዜ የሚበልጥ ተፅዕኖ ይኖረዋል” በማለት አስረድተዋል።

የጳጳሱ መልዕክት በርካታ የዩናይትድ ኪንግደም ክልሎች ያዳረሰውን የደህንነት ስጋት እንዲሁም የጅምላ ብጥብጥ እና እስራት እያስከተሉ ያሉ፥ በለንደን፣ በርሚንግሃም፣ ዮርክሻየር እና መርሲሳይድ ጎዳናዎች ላይ ያስወጣውን ብሎም እየተስፋፋ እና በርካታ ሰዎችን ወደ ሁከትና ብጥብጥ የመራውን አመጽ ተከትሎ መሆኑም ተነግሯል።

በሊቨርፑል ውስጥ ተወልዶ ያደገው የየመን ዝርያ ያለው ወጣት ተማሪ የሙስሊም ዝርያ ያላቸው የብሪታኒያ ዜጎችን ስሜት ወክሎ እንደተናገረው “አሁን ባለው ሁኔታ እንደራስህ ሃገር አይሰማህም” በማለት ገልጿል።

ሊቀ ጳጳስ ዌልቢ በእንግሊዝ ያሉ የአብያተ ክርስቲያናት ፕሬዚዳንቶች ህብረት ጋር በመሆን፥ በተለይ ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ በሳውዝፖርት ከተማ ለተፈፀመው ጥቃት ፈጣን ምላሽ ለሰጡት በመርሲሳይድ ክልል ውስጥ ላለው የአብያተ ክርስቲያናት ፕረዚዳንቶች ህብረት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የእንግሊዝ እና የዌልስ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ለሀገር ውስጥ ማህበራዊ ተግባር ይፋዊ ኤጀንሲ ቤተክርስቲያኒቷ በአመጽ ወረርሽኙ ሰለባ ለሆኑት የተገለሉ ማህበረሰቦች ተስፋ እና ድጋፍ ለማድረግ ትፈልጋለች በማለት በቅርቡ አጋርነታቸውን ገልፀዋል።
 

12 August 2024, 15:55