በጣሊያን ሟች ስደተኞችን የሚዘክር የሙዚቃ ዝግጅት እንደሚካሄድ ተነገረ
አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
ጥቅምት 2006 ዓ.ም. በሜዲትራኒያን ባህር ውስጥ 636 ስደተኞች በሁለት የተለያዩ የጀልባ2 አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፥ ከአሥራ አንድ ዓመታት በኋላ፣ መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም. ይሄንን አሳዛኝ ክስተት የሚያስታውስ የሙዚቃ ዝግጅት በሚላን በሚገኘው የቅዱስ አምብሮጂዮ ባዚሊካ በሜዲ-ትራኒያን ባህር ውስጥ የጠፉትን ስደተኞች በሙሉ ለማስታወስ ተብሎ የሚዘጋጀ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፥ ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ ብቻ በባህር ላይ በሚደረግ አስቸጋሪ የስደት ጉዞ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ30,300 በላይ መድረሱም ተገልጿል።
በዚህ የመታሰቢያ የሙዚቃ ዝግጅት ወቅት ‘ኳርቴት ኦፍ ዘ ሲ’ ወይም (በጣሊያንኛ “ኳርትቴቶ ዴል ማሬ”) ተብሎ የሚጠራው የሙዚቃ ባንድ ሙዚቃውን እንደሚያቀርብ የተነገረ ሲሆን፥ ይህ የሙዚቃ ቡድን ታዋቂው የሙዚቃ ሊቅ የሆነው ሞዛርት ለሙታን መታሰቢያ ብሎ ያቀነባበረውን ሙዚቃ እንደሚጫወቱ ተገልጿል።
የሙዚቃ ባንዱ ከሁለት ቫዮሊን፣ አንድ ቫዮላ እና በአንድ ሴሎ የተዋቀረ እና አቀራረቡ ከሌሎች ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም የሙዚቃ መሳሪያዎቹ አሰራር ከተለመደው በጣም የተለዩ እንደሆነ ይተነገረ ሲሆን፥ ምክንያቱም ደግሞ እነዚህ የሙዚቃ መሳሪያዎች በአንድ ወቅት የተለያዩ ስደተኞችን በባህር ስያጓጉዙ ከነበሩ የጀልባ እንጨቶች በሁለት የጣሊያን እስረኞች ተቀርፀው የተሰሩ እንደሆነ ተጠቅሷል። ኮንሰርቱ ‹ሜታ-ሞርፎሲስ› ተብሎ የተሰየመው ፕሮጀክት አካል ሲሆን፥ ይህ ፕሮጄክት አደጋ የሚያደርሱ መሳሪያዎችን ወደ ውበ እና ማራኪ ወደሆኑ መገልገያ መሳሪያዎች የሚቀይር ፕሮጄክት እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፥ የመታሰቢያ ሙዚቃ ዝግጅቱ የሚከፈተው ስደተኞች እና ታራሚዎች ከአደጋ የመትረፍ፣ የመለወጥ እና የሁለተኛ እድልን የማግኘት ኃይል ልምዳቸውን በሚያካፍሉበት ምስክርነት እንደሆነ ተገልጿል።
ሙዚቃው
የእነዚህ ሙዚቀኞች ባንድ ቅንብር ኤውጂን ጋርጂዮላ እና አግኔስ ታሶ በቫዮሊን፣ ኢቫ ኢምፔ-ሊዜሪ በቫዮላ እና ሚሼል ባላሪኒ በሴሎ በሚጫወቱት ሙዚቃ የተዋቀረ እንደሆነ ተነግሯል። ሬኪዩም የተሰኘው የሞዛርት የሙዚቃ ቅንብር ‘ያላለቀው የሞዛርት ሙዚቃ’ በሚል ርዕስ የቡድኑ አባል በሆነችው ኢቫ የተፃፈ እንደሆነ ተገልጿል። ይህ ርዕስ የዋና አቀናባሪውን የሞዛርትን ያለጊዜ ሞት የሚያስታውስ እና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ አዲስ ህይወትን ለሚፈልጉ ለበርካታ ሰዎች “መካነ መቃብር” መሆኑን ደጋግመው በገለጹት የባህር ላይ ጉዞ ህይወታቸው በአጭር የተቀጨውን ስደተኞች የሚያስታውስ እንደሆነ ተመላክቷል።
‘ሪክዌም ማስስ’ (Requiem Masses) ተብሎ የተሰየመው የሙዚቃ ዝግጅቱ ለሙታን የሚደረጉ የመታሰቢያ መስዋዕተ ቅዳሴዎችን የሚያመላክት ሲሆን፥ አቀናባሪዋ ኢቫ በሞዛርት ሞት ምክንያት ያላለቀውን ቅንብር ‘ላክሪሞሳ’ ወይንም (በላቲንኛ ‘አሳዛኝ’ ማለት ነው) በሚል ርዕስ ለመጨረስ እንደመረጠች፣ ይሄም የሞዛርትን በአጭር የቀረ የህይውት ጉዞ ከማመላከቱም ባሻገር፣ በጉዞ ላይ ሳሉ ሰምጠው የቀሩ ስደተኞችን አሳዛኝ ህይወት የሚያመላክት እንደሆነ ተገልጿል።
ኢቫ የሞዛርት ተማሪ የነበረው ሱስ-ማይር የሞዛርትን ያላለቀ ስራ እንዴት እንዳጠናቀቀው እና የሰው ልጅ የስደተኞችን፣ የእስረኞችን እና የተገለሉትን ሁሉ ያልተጠናቀቁ ታሪኮች ሸክም መሸከሙን እንዴት እንደሚቀጥል በማመሳሰል ገልጻለች።
ዝግጅቱ እንዲሁም ከጀርባው ያሉት ድርጅቶች እና ሰዎች ሁሉም በባህር ላይ ለሚጓዙ ስደተኞች ህይወት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ የሚከራከሩትን የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ አስተምህሮ ይከተላሉ የተባለ ሲሆን፥ ብጹእነታቸው በቅርቡ እንደተናገሩት “ስደተኞች በእነዚያ ገዳይ ባህር ውስጥ መቅረት የለባቸውም” ማለታቸው ይታወሳል። ይህ የሙዚቃ ኮንሰርት ዝግጅት ብቻ ሳይሆን በመካከላችን ያሉ በጣም ለተጎዱት እንኳን ሳይቀር መጨው ጊዜ ፍቅር የሚሰፍንበት ዘመን እንዲሆን የምንጸልይበት ወቅት እንደሆነም ተነግሯል።
የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስኮን አስተምህሮ የሚከተለው ፕሮጄክት
የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስስኮን አስተምህሮ የሚከተለው የሜታሞርፎሲስ ፕሮጀክት ለዚህ የሙዚቃ ዝግጅት አብሪ ኮከብ እንደሆነው ያመላከተችው አቀናባሪዋ፥ ባንዱ የተመሰረተው በካሳ ዴሎ ስፒሪቶ ፋውንዴሽን እንደሆነ፣ የሙዚቃ መሳሪያዎቹን ከጀልባ እንጨቶች የሰሩትን የኦፔራ እና ሴኮንዲ-ግሊያኖ እስር ቤት ታራሚዎችን እንደሚያካትት ገልፃለች።
ይህ ተነሳሽነት እስረኞቹ አዳዲስ ክህሎቶችን እና ዓላማዎችን እንዲያነገቡ ለውጥን እና መቤዠትን ለማሳየት ያለመ ነው ተብሏል። እ.አ.አ. በ 2012 ዓ.ም. በአርኖ-ልዶ ሞስካ እና ማሪሳ ባልዶኒ የተመሰረተው ፋውንዴሽኑ ሁለተኛ እድሎችን በማቅረብ ላይ የሚያተኩር ሲሆን፥ በጣሊያን እና በዓለም ዙሪያ ያሉ በተለያዩ ፕሮጀክቶች በኩል ለአደጋ ተጋላጭ ከሆኑ ግለሰቦች ጋር እንደሚሰራ እና ፕሮጀክቱ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በሚረዳው ሪል-ሞንቴ ኢ. ቲ. ኤስ በተባለው ማህበር እንደሚደገፍም ተገልጿል።