ፈልግ

 እስራኤል ለቀው እንዲወጡ የሰጠችውን ትእዛዝ ተከትሎ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን ወደ ጃባሊያ ሲሻገሩ እስራኤል ለቀው እንዲወጡ የሰጠችውን ትእዛዝ ተከትሎ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን ወደ ጃባሊያ ሲሻገሩ  (AFP or licensors)

ዩናይትድ ስቴትስ በጋዛ የሚደረገው ጦርነት እንዲቆም ጠየቀች

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በጋዛ ሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንዲደርስ የተኩስ አቁም ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በጋዛ እየተካሄደ ያለው ጦርነት እንዲቆም የጠየቁት ሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች እንዲደርስ መሆኑን ገልጸው፥ እስራኤል ያቀደቻቸውን ግቦች ስላሳካች ጦርነቱ አሁን ማብቃት እንዳለበት አክለው ተናግረዋል።

አንቶኒ ብሊንከን ይሄንን ያሉት ዋሽንግተን ወደ ጋዛ ተጨማሪ እርዳታ ለመላክ የሚያስችላት ቀነ ገደብ ቢያልፍም፥ ለእስራኤል የምታደርገውን ወታደራዊ ድጋፍ መላክ እንደምትቀጥል መግለጿን ተከትሎ ነው።

ሆኖም ግን ዓለም አቀፍ የረድኤት ቡድኖች እስራኤል ማንኛውንም የአሜሪካን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ማሟላት ተስኗታል ሲሉ ይገልፃሉ።

በሌላ ዜና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም ስራዎች ዋና ጸሃፊ ዣን ፒየር ላክሮክስ እንደተናገሩት በሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ድርጅቱ ከሁሉም አካላት ጋር ከፍተኛ ጥረት አድርጓል ብለዋል።

የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ባለስልጣኑ ይሄንን ያሉት ማክሰኞ ዕለት ከሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ ነው።

የእስራኤል ጦር ከመስከረም ወር አጋማሽ ጀምሮ በሊባኖስ ላይ የተጠናከረ የአየር ጥቃት እየፈፀመ ሲሆን፥ በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ የእግረኛ ጦር ዘመቻ መጀመሯ ይታወቃል።
 

15 November 2024, 12:45