የሐምሌ 25/2013 16ኛ እለተ ሰንበት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ የሐምሌ 25/2013 16ኛ እለተ ሰንበት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ 

የሐምሌ 25/2013 16ኛ እለተ ሰንበት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ


የልባችንን ሥነ-ምህዳር ማስፋት አለብን

የእለቱ ንባባት

1.      ኤርሚያስ 23፡1-6

2.    መዝሙር 22

3.    ኤፌሶን 2፡13-18

4.    ማርቆስ 6፡30-34

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል

ሐዋርያትም በኢየሱስ ዙሪያ ተሰብስበው የሠሩትንና ያስተማሩትን ሁሉ ነገሩት። ብዙ ሰዎች ይመጡና ይሄዱ ስለ ነበር ምግብ እንኳ ለመብላት ጊዜ ስላልነበራቸው፣ “እስቲ ብቻችሁን ከእኔ ጋር ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ እንሂድና ጥቂት ዕረፉ” አላቸው።

ስለዚህ ብቻቸውን ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ በጀልባ ሄዱ። እነርሱም ሲሄዱ ብዙ ሰዎች አይተው ዐወቋቸው፤ ከከተሞችም ሁሉ በእግር እየሮጡ ቀድመዋቸው ደረሱ። ኢየሱስ ከጀልባዋ በሚወርድበት ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተሰብስቦ አየ፤ እረኛ እንደሌላቸው በጎች ስለ ነበሩም አዘነላቸው፤ ብዙ ነገርም ያስተምራቸው ጀመር።

 

የእለቱ አስተንትኖ

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው የስርዓተ አምልኮ ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል (ማርቆስ 6: 30-34) ውስጥ የምንመለከተው የኢየሱስ አመለካከት ሁለት አስፈላጊ የሕይወት ገጽታዎችን እንድንገነዘብ ይረዳናል። የመጀመሪያው እረፍት ነው። የሚሶዮናዊ ተልእኮ ሥራ አጠናቀው የተመለሱ ሐዋርያት በደስታ ያደረጉትን ሁሉ መዘርዘር የጀመሩ ሲሆን ኢየሱስ “እስቲ ብቻችሁን ከእኔ ጋር ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ እንሂድና ጥቂት ዕረፉ” በማለት ሐዋርያቱን ይጋብዛቸዋል። የእረፍት ግብዣ ያቀርብላቸዋል።

በዚህም ኢየሱስ ጠቃሚ ትምህርት ይሰጠናል። ምንም እንኳን በስብከታቸው አስደናቂ ነገሮች የተነሳ የደቀ መዛሙርቱን ደስታ በማየቱ ደስ ቢለውም ፣ ለእነሱ ምስጋና ወይም ጥያቄ ለማቅረብ ጊዜ አላጠፋም።ይልቁንም እሱ ስለ አካላዊ እና ውስጣዊ ድካማቸው ያሳስባል። እናም ለምን ይህን ያደርጋል? ምክንያቱም እሱ ለእኛም ቢሆን ሁል ጊዜ እዚያ በድብቅ የሚጠብቀንን አደጋ እንድናውቅ ለማደረግ ስለሚፈልግ ነው ፣ ነገሮችን በማከናወን እብደት ውስጥ ገብተን የመያዝ አደጋ ፣ በጣም አስፈላጊ እና የምናገኛቸው ውጤቶች ባሉበት የእንቅስቃሴ ወጥመድ ውስጥ የመውደቅ አደጋ እና ፍጹም ተዋንያን የመሆን ስሜት ለማስወገድ ፈልጎ ነበር ይህንን ግብዣ ያቀረበላቸው። በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ስንት ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ነገሮች ይከሰታሉ - እኛ ስራ ላይ ነን ፣ እንሮጣለን ፣ ሁሉም ነገር በእኛ ላይ የተመረኮዘ ነው ብለን እናስብና በመጨረሻም ኢየሱስን ችላ የማለት ስጋት ውስጥ እንገባለን፣ ሁሌም እራሳችንን ማዕከል እናደርጋለን። ለዚህም ነው ደቀ መዛሙርቱን እነርሱ ብቻ ትንሽ ከእሱ ጋር እንዲያርፉ የሚጋብዘው። እሱ አካላዊ እረፍት ብቻ ሳይሆን ለልብም እረፍት ነው። እራሳችንን “መንቀል” በቂ አይደለም ፣ በእውነት ማረፍ ያስፈልገናል። እና ይህን እንዴት እናደርጋለን? ይህንን ለማድረግ ወደ ነገሮች ልብ መመለስ አለብን -መቆም፣ ዝም ማለት ፣ ከሥራ ብስጭት ይልቅ ዘና ወደ ሚያደርገን እና ወደ እብደት ላለመሄድ መጸለይ አለብን። ኢየሱስ የሕዝቡን ፍላጎት ችላ አላለም፣ ነገር ግን በየቀኑ ከማንኛውም ነገር በፊት ፣ በጸሎት ፣ በዝምታ ፣ ከአብ ጋር ያለውን ቅርበት ለማጠናከር ገለል ወዳለ ቦታ መሄድ ነበረበት። የእሱ - ትንሽ ጊዜ ማረፍ - የሚለው የእርሱ ግብዣ አብሮን ሊሄድ ይገባል። ወንድሞችና እህቶች ውጤታማ መሆን አለብን ብለን ከምናደርገው ሩጫ እንጠንቀቅ ፣ በአጀንዳዎቻችን የታያዘውን ሽኩቻ እናቁም። እንዴት ማረፍ እንዳለብን ፣ ሞባይላችንን በማጥፋት ፣ ተፈጥሮን ለማሰላሰል ፣ ከእግዚአብሄር ጋር በመነጋገር እራሳችንን ለማደስ እንድንችል እንዴት መማር እንችላለን?

ሆኖም ቅዱስ ወንጌል ኢየሱስ እና ደቀ መዛሙርቱ እነርሱ እንደወደዱት ማረፍ እንደማይችሉ ይነግረናል። ህዝቡ እነሱን ለማግኘት ከሁሉም አቅጣጫ ወደ እነሱ ይጎርፋል። በየትኛውም ጊዜ ቢሆን እርሱ በርህራሄ ይነዳል። ርህራሄ የሚለው ቃል ሁለተኛው ገጽታ ነው፣ እሱም የእግዚአብሔር ዘይቤ ነው። የእግዚአብሔር ዘይቤ መቅረብ ፣ ርህራሄ እና ምሕረት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “እርሱ ራራላቸው” የሚለውን ይህንን ሐረግ በወንጌሉ ውስጥ ስንት ጊዜ እናገኛለን? ኢየሱስ ራሱን ለሰዎች ወስኖ እንደገና ማስተማር ይጀምራል (ማርቆስ 6፡ 33-34)። ይህ እርስ በእርሱ የሚቃረን ይመስላል ፣ ነገር ግን በእውነቱ የሚቃረን ነገር አይደለም። በእውነቱ በችኮላ እንዲወሰድ የማይፈቅድ ልብ ብቻ ነው የመንቀሳቀስ ችሎታ ያለው፣ ማለትም በራሱ እና በሚከናወኑ ነገሮች እንዲጠመድ ባለመፍቀድ እና ስለ ሌሎች ሰዎች ቁስሎች እና ፍላጎቶቻቸው ያውቃል። ርህራሄ ከማሰላሰል የተወለደ ነው። በእውነት ማረፍ የምንማር ከሆነ የእውነተኛ ርህራሄ ችሎታ እናዳብራለን። የማሰላሰል አስተሳሰብን ካዳበርን ሁሉንም ነገር ለመያዝ እና ለመበላት የሚፈልጉ እነዚያ ርኩስ አመለካከት የሌላቸውን ተግባራትን እናከናውናለን፣ ከጌታ ጋር ከተገናኘን እና የራሳችንን ጥልቅ የሆነ ክፍል ካላደነቅን ማድረግ ያለብን ነገሮች እንዳናከናውን የሚያደርጉን ነገሮች ኃይል አይኖራቸውም። እኛ እረፍ ማደረግ ያስፈልገናል፣ በማረፍ፣ በማሰላሰል እና በርህራሄ የተዋቀረ “የልብ ሥነ-ምህዳር” ያስፈልገናል። ለዚህም የበጋውን ጊዜ እንጠቀምበት! ትንሽ ሊረዳን ይችል ይሆናል።

እናም አሁን ዝምታን ፣ ጸሎትን እና ማሰላሰልን ለእኛ ያስተማረች፣ እኛ ልጆቿ ለሆንን ሰዎች ሁልጊዜ በርኅራኄ ቅርብ ወደ ሆነችው እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንጸልይ።

 

31 July 2021, 08:58