ካርል አንደርሰን በፖላንድ በሉብሊን ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ሲቀበሉ ካርል አንደርሰን በፖላንድ በሉብሊን ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ሲቀበሉ 

ፕ/ር ካርል አንደርሰን በሉብሊን የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተሰጣቸው

በፖላንድ የሚገኘው የጆን ፖል 2ኛ የሉብሊን ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ለቀድሞው የ ‘ናይት ኦፍ ኮሎምበስ’ (ናይትስ ኦፍ ኮሎምቦስ ዓለም አቀፋዊ የካቶሊክ ወንድማማችነት አገልግሎት ሲሆን፥ እ.አ.አ. መጋቢት 29 ቀን 1882 በአባ ሚካኤል ማጊቪኒ የተመሰረተ ነው) የተባለው የካቶሊክ የወንድማማችነት ተቋም ከፍተኛ አመራር ለነበሩት ፕሮፌሰር ካርል አንደርሰን የክብር ዶክትሬት አበርክቶላቸዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በሉብሊን ከተማ በተካሄደው አስደሳች ሥነ ሥርዓት ፕሮፌሰር ካርል አንደርሰን የዶክትሬት የክብር ሽልማት ተሸልመዋል።

ፕሮፌሰር አንደርሰን ከቫቲካን ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “በኋላ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ካሮል ዎጅቲላ ካስተማሩበት ዩኒቨርሲቲ የዶክትሬት ዲግሪ መቀበል ትልቅ ክብር ነው። ይህ ዩኒቨርሲቲ የወደፊት መሪዎችን ማብቃት የሚችል ልዩ ቦታ ነው” ብለዋል።

ተነሳሽነት

የክብር ዶክትሬት ዲግሪውን ለፕ/ር አንደርሰን የሰጠው የሉብሊን የካቶሊክ ዩኒቨርስቲ ሴኔት ያወጣው የውሳኔ ሃሳብ ‘ዩኒቨርስቲው ለፕሮፌሰር ካርል አልበርት አንደርሰን እንቅስቃሴ በተለይም በኮሎምበስ ናይትስ ውስጥ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በማጎልበት፣ የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛን አስተምሮት እና ትሩፋት በማስተዋወቅ እንዲሁም የህይወት ስልጣኔን በማስተዋወቅ ረገድ ለሰሩት ሥራ ያለውን ክብር እና አድናቆት ለመግለጽ እንደሚፈልግ’ ይገልጻል።

በሥነ ሥርዓቱ መክፈቻ ላይ የሉብሊን ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ሃላፊ የሆኑት አባ ፕሮፌሰር ሚሮዝላው ካሊኖውስኪ እንደገለፁት፥ ፕ/ር ካርል አንደርሰን በጣም እምነት የሚጣልባቸውን እና በተለያዩ የቫቲካን ተቋማት ውስጥ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ መሆኑን በመገንዘብ የሰውን ልጅ ህይወት በመጠበቅ እና በቤተሰብ ውስጥ ክርስቲያናዊ እሴቶችን በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ቦታ ላይ እንደነበሩ ተናግረዋል።

“በወንጌል ምሳሌ ላይ እንደተገለጸው ድንቅ ሰዎች ችሎታቸውን አውቀው፣ በተግባር ሊያሳዩአቸው እና የድካማቸውን ፍሬ ማካፈል ይችላሉ። በእኔ አስተያየት፥ ልክ እንደሳቸው ያለ ሰው፣ በፈጣሪ በተሰጣቸው ልግስና አስፈላጊ ለሆኑ ሥራዎች የተጠሩት ለብዙ ዓመታት የናይትስ ኦፍ ኮሎምበስ ከፍተኛ መሪ የነበሩት ካርል አንደርሰን ናቸው” በማለት የቶሩን ጳጳስ ዊስላው ስሚጌል ስለ ተሸላሚው ተናግረዋል።

የፍቅር ሥነ-መለኮት

ፕሮፌሰር ካርል አንደርሰን “ዮሃንስ ጳውሎስ 2ኛ በ21ኛው ክፍለ ዘመን” በሚል ርዕስ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም ውስጥ የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ክንዋኔዎች ከቅዱስ አውግስጢኖስ ጋር በታሪካዊ ግምገማዎች ሊነፃፀሩ እንደሚችሉ ሀሳብ አቅርበዋል። ይህም ለወደፊቷ ቤተ ክርስቲያን ራዕይ ያለው መንገድ ለማቅረብ ባላቸው ችሎታ እና አዲስ ዘመን ከመፈጠሩ በፊት የነበረውን ውድቀት ለመቋቋም ባደረጉት ጥረት ምክንያት ነው ብለዋል። በተጨማሪም “የዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የፍቅር ሥነ-መለኮት የትምህርት ልምምድ ሳይሆን የአንድ ካቶሊክ ሕይወት ዋና ክፍል እንደሆነ እንዲሁም በአማኙ ልብ ውስጥ ‘ለክርስቶስ በራችሁን ክፈቱ’ የሚለውን ጥሪ ልብ ነው” በማለት ገልፀዋል።
 

11 December 2023, 15:09