PANAMA WORLD YOUTH DAY POPE

ክርስቶስ ሕያው ነው! ተስፋችን ነው"! ተስማሚ አካባቢዎች

ብዙዎቹ ወላጅ አልባ የሆኑ ያህል ዓይነት ስሜት እስከተሰማቸው ድረስ" እኛ ማድረግ ያለብን ሁሉም ተቋሞቻችን ወጣቶችን ይበልጥ አቀባበል የሚያደርጉ ይበልጥ የተሟሉ እንዲሆኑ ነው” እዚህ ጋ እየተናገርሁ ያለሁት ስለ ቤተሰብ ችግር ሳይሆን በወንዶችና በሴቶች ልጆች" ወጣቶች" ወላጆችና ሕጻናት ልጆችንም በአንድ ዓይነት ሁኔታ ነው” ለእነዚህ ሁሉ ወላጅ አልባዎች -ምናልባትም እኛንም ጨምሮ - እንደ ቁምሰና ያሉ ወይም ትምህርት ቤት ያሉ ማኅበሮች ግልጽነትን" ፍቅርን" እና እድገት የሚረጋገጥበትን መንገድ ማመቻቸት ይገባቸዋል” አያሌ ወጣቶች በዚህ ዘመን የሚሰማቸው ስሜት ያልተሳኩ የወላጅ" የአያት" ቅድም አያቶቻቸውን ያልተሳኩ ሕልሞች" በኢፍትሃዊነት ምክንያት ያልተሳኩ ሕልሞችን" የሕብረተሰብ ሁከት" ራስ ወዳድነትና ለሌሎች ግድ የለሽነትን እንደወረሱ ነው” በአንድ ቃልም ለማስቀመጥ ያህል ሥራቸው እንደተነቀለ ነው የሚሰማቸው” ወጣቱ የሚያድገው አመድ ውስጥ ባለች ዓለም ከሆነ" ነበልባላቸው የማይጠፋ ታላላቅ ሕልሞችና ፕሮጀክቶችን ማቆየት አዳጋች ይሆንበታል” ወጣቶች የሚያድጉት ከትርጉም ርቀው ከሆነ" ዘር የመዝራት መሻቱን እንዴት ሊያሳድጉ ይችላሉ? ያለመቀጠል ተሞክሮ" ሥር መነቀል" የመሠረታዊ እርግጠኝነት መውደቅ" በአሁን ዘመን የሚዲያ ባሕል ተኮትኩቶ" ሥር የሰደደ የወላጅ አልባነት ስሜት ስለሚፈጥር እኛ ደግሞ ማድረግ ያለብን ሌሎች በምክኒያታዊነት የሚኖሩበት የወንድማማችነት አካባቢና ሁኔታን መፍጠር ነው”።

በአጭር ቃል" 'መኖሪያ' ማደራጀት ማለት 'ቤተሰብ' መፍጠር ማለት ነው” “ጥቅም ያለውና ተግባራዊ ትስስር ከመሆን ባለፈ" ሕይወታችን ትንሽ ከሰብአዊነት ላቅ ያለ እንደሆነ እስኪሰማን ድረስ" ከሌሎች ጋር መተሳሰርን መማር ማለት ነው” መኖሪያ መፍጠር ማለት ትንቢት ሥጋ እንዲለብስ" ሰዐታችንና ቀኖቻችን ቅዝቃዜ ረገብ እንዲል" ልዩነቶቻችን እንዲቀንሱ መፍቀድ ማለት” ሁላችንም ልንሠራ የምንችልበት በቀላልና በሁልጊዜ ክንዋኔ ትስስር መፍጠር ማለት ነው” እያንዳንዱ ሰው ለቤቱ መሥሪያ የሚሆን ድንጋይ እስከሆነ ድረስ" ማንም ምላሽ የማይሰጥ ወይም ተነጥሎ የሚቆም አይሆንም” ይህ ደግሞ ትዕግሥትን እርስ በርስ ይቅር መባባልን" እያንዳንዱን ቀን በአዲስ መጀመርን እንዴት መማር እንደምንችል" ጌታ ጸጋውን እንዲሰጠን መጠየቅን ያካትታል” ምን ያህል ጊዜ ነው ይቅር ብዬ እንደ አዲስ የምጀምረው? ሰባ ጊዜ ሰባት ጊዜ" አስፈላጊውን ያህል ጊዜ” ጠንካራ ትስስር ለመፍጠር አስፈላጊ የሚሆነው ነገር ዕለት ዕለት ትዕግሥ ትንና ይቅርታን በመኮትኮት" በራስ በመተማማን ሌላውን ማመን” እንደዚያ ነው ተዓምራት የሚሆነው : እንደገና የተወለድን" ሁላችንም እንደገና እንደተወለድን ይሰማናል" ምክንያቱም ይበልጥ ሰብአዊ ዓለም እንድናልም" ስለዚህም ይበልጥ መለኮታዊ እንዲሆን" የእግዚአብሔርን እንክብካቤ ስለምንሰማ ነው””።

ከዚሁ ጋር" ተቋሞቻችን ወጣቶች በነጻነት የሚመጡበትና የሚሄዱበት" መልካም አቀባበል እንደሚደረግላቸው የሚያዩበትና ሌሎች ወጣቶችን የሚያገኙበት በአስቸጋሪም ሆነ በተስፋ መቁረጥ" በደስታና በበዓልም ጊዜ የራሴ ነው የሚሉት ስፍራዎችን መስጠት ይገባቸዋል” ከእነዚህ አንዳንዶቹ ቀደም ሲል ጀምሮ በአንዳንድ የወጣት ማዕከላት እየተደረጉ ነው" በአብዛኛውም ወዳጅነቶች የሚጠናከሩበት ዘና ያሉ ሁኔታዎችን የሚያስተናግዱ" ወጣት ወንድና ሴቶች የሚገናኙበት" ሙዚቃ" ግጥሚያዎች" ስፖርቶች" እንዲሁም ደግሞ ስለ እግዚአብሔር ቃል የሚነጋገሩበትና የሚጸልዩበትም ሁኔታ አለ”።

እንዲህ ባሉ ስፍራዎች" ያለ ብዙ ወጭና የገንዘብ ምንጭ ፍለጋ" ብዙ ነገር ማቅረብ ይቻላል” እንደገናም ያን ጊዜ" በማናቸውም ዓይነት ሐዋርያዊ ምንጭ ወይም ስልት ሊተካ የማይችለው" መልእክቱን ለማስተላለፍ ወሳኝ የሆነው የሰው ለሰው ግንኙነት እውን ይሆናል”

“ወዳጅነትና መወያየት" አብዛኛውን ጊዜ ይብዛም ይነስም የተዋቀረ ቡድን" አንዱ በሌላው የማይመረመርበት አልያም የማይፈረድበት የማኅበራዊና የግንኙነት ክህሎትን ለማጠናከር ዕድልን ይፈጥራል” የቡድን ተሞክሮ ከዚህም በተጨማሪ እምነትን ለመጋራት እና ለመመስከር የጋራ መረዳዳት እንዲኖር ትልቅ ግብአት ነው” ወጣቶች ሌሎች ወጣቶችን መምራትና እና በጓደኞቻቸው መኻከል እውነተኛ የሆነ ሐዋርያ መሆን ይችላሉ””።

ይህ ማለት ራሳቸውን አግልለው ከቁምስናቸው ጋር ያላቸውን ማናቸውንም ግንኙነት" እንቅስቃሴ" ማቋረጥ ማለት አይደለም” ነገር ግን በተሻለ ሁኔታ ለሌሎች ራሳቸውን ክፍት ከሚያደርጉ" እምነታቸውን ከሚኖሩት" ክርስቶስን ከሚያንጸባርቁ" ደስተኞች" ነጻ የሆኑ" ወንድማማቾች እና በትጋት ከሚሠሩ ጋር ይበልጥ ይጣመራሉ” እነዚህ ማኅበራት ውድ የሆኑ ግንኙነቶችን የማሳደጊያ አካባቢዎች ናቸው”።

ምንጭ፡ ክርስቶስ ሕያው ነው በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለወጣቶች እና ለጠቅላላው የእግዚአብሔር ሕዝብ ከጻፉት ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ምክር ከአንቀጽ 216-220 ላይ የተወሰደ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ዳንኤል ኃይሌ ሮም።

26 January 2024, 13:44