አብ ልጁን የዓለም አዳኝ አድርጎ እንደላከው
ከእግዚአብሔር የሚመጣ ሁሉ በነፍሰ ወከፍ ደኀንነት ያገኛል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ተናግሮአል በማለት የኢሳይያስን ትንቢት እየጠቀሰ ለአይሁዳውያን የኢየሱስን መምጣት አስታወቃቸው፡፡ ሊያድናቸው ከሰማይ የሚመጣውን መሢሕ በልባቸው አምነው እንዲቀበሉ መከራቸው፡፡ ከዓመት ዓመት፣ ከዘመን ዘመን ቤተክርስቲያን ለእኛም “የእግዚአብሔር መንግሥት መምጫ እቀረበ ነውና ንስሐ ግቡ፣ የእግዚአብሔርን መንገድ አሰናዱ ጥረጉ የሚለውን የመጥምቁ ዮሐንስን አዋጅ በድጋሚ ትነግረናለች፡፡ እንዴት አድርገን ነው የምናዘጋጀው; ቅዱስ ዩሐንስ “ንሰሐ ግቡ$ እንዳለ ንሰሐ ገብተን የእግዚአብሔርን መንገድ እናዘጋጅ (ማቴ. 3፣2)፡፡
ሕፃኑ ኢየሱስ ወደ እኛ የሚመጣበትን መንገድ ልናዘጋጅ እርሱ የሚጠላውን የሚከለክለውን የኃጢአትን መንገድ ትተን የሚወደውንና ተደስቶ ወደ እኛ እንዲመጣ የሚያደርገውን የጽድቅ መንገድ እንድንይዝ ያስፈልገናል፡፡ ወደ እኛ እንዳይመጣ የሚከለክለ የኃጢአት ተራራ ጥል፣ ቅንዓት፣ አምባጓሮ፣ ሁከት፣ ዝሙት፣ ዓመጽ፣ ቂም በንስሐ መደምሰስ አለብን፡፡ በውስጣችን የማገኝ የመንፈስ ቅዝቃዜ የመንፈሳዊነት ጉድለት … በጸሎት በተጋድሎ በበጐ ሥራ በትሕትና በፍቅር በየዋሕነት በምሕረት በትዕግስት በሃይማኖት በእምነት እንድንሞላው ያስፈልገናል፡፡ ጠመዝማዛ አስተሳሰብና አረማመድ እንዲቀና ንግግራችንና ሥራችን የታረመ እንዲሆን ሕይወታችን በሙሉ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር እንዲስማማ አድርገን መዘጋጀት አለብን፡፡
እንደዚህ ያለ መንገድ ከጠረግን ሕፃን ኢየሱስ ተደስቶ ወደ እኛ በመምጣት፡፡ ወደ ልባችን ይገባል፡፡ ይህን መንፈሳዊ ዝግጅት ኢሳይያስ “ከእግዚአብሔር የሚመጣ ደኀንነት የሚለውን ለመቀበል ያብቃን፡፡ መለኮታዊውን ሕፃን በመንፈስ ንፁሃን ሆነን ተዘጋጅተን ካአገኘው በኋላ በመንፈስ እንገደና እንደምንወለድ የልደቱን ጸጋ ያድለናል፡፡
ልደት ለነፍሳችን እንጂ ሥጋችንን እንዲጠቅም የተዘጋጀ ልደት በሥጋ የምንደሰትበት የምንጠጣበት የምንለብስበት በነፍስ ግን ተርበን ተጠምተን በጸጋ ራቁታችን የምንወጣበት የምንውልበትና ነፍሳችን የምትጐዳበት የምታዝንበት ቀን ሊሆን አይገባም፡፡ ልደት የነፍስ በዓል ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ቀን ነፍሳችን በጸጋና በመንፈሳዊ ደስታ መሞላት አለበት፡፡ ይህን እንድናገኝ ደግሞ አስቀድመን በሚገባ ልንዘጋጅ ያስፈልጋል፡፡