PORTUGAL-VATICAN-POPE-RELIGION-WYD

ክርስቶስ ሕያው ነው! ተስፋችን ነው" ሁልጊዜም ሚሽነሪዎች

እዚህ ስፍራ ላይ ማለት የምፈልገው ወጣቶችን ሚሸነሪ ለማድረግ ብዙም እንደማያስቸግር ነው” ደካሞች የሆኑትን እንኳን ሳይቀር" ውሱንነት ያለባቸው እና የሚቸገሩ በራሳቸው መንገድ ሚሺነሪዎች መሆን ይችላሉ" ምክንያቱም መልካምነት ከብዙ ውሱንነት ጎን ቢሆንም አንኳን" ሁልጊዜ ሊጋሩት የሚቻል ነገር ነው” መንፈሣዊ ጉዞ የሚያደርግ ወጣት እመቤታቸንን እርዳታ መጠየቅ" አብሮ የሚጓዝ ሰው መጋበዝ" በዚያች ትንሽ ምልክት መልካም ሚሽነሪነት ይታያል” “ከታዋቂነት” የወጣትነት አገልግሎት ባልተለየ ሁኔታ “ታዋቂ” ሚሽነሪ" ባሕላዊ የሆኑ ሞዴሎችና አስተሳሰቦችን የሚሰብር ክንዋኔ አለ” እናግዝ እና እናበረታታው" ነገር ግን መቆጣጠር መጀመር የለብንም” መንፈሱ ምን እያለን አንደሆነ መስማት ከቻልን" የወጣት አገልግሎት ሁልጊዜም ሚሽነሪ መሆኑን እንገነዘባለን” ወጣት ልጆች ቁጥብናቸውን ትተው ቤቶችን መጎብኘት ቢገዳቸው" በዚህ መንገድ የሌሎችን ሰዎች ሕይወት መንካት ስለሚችሉ በጣም ያድጋሉ” ከቤተሰብና ከጓደኞቻቸው ባለፈ መመልከት ይችላሉ" እንዲሁም የሕይወትን ሰፋ ያለ እይታ ያገኛሉ” በዚያውም ልክ" እምነታቸውና የቤተ ክርስትያን አካል የመሆናቸው ስሜት ይበልጥ ይጠነክራል” የወጣት ሚሺኖች" በተለይም ከዝግጅት በኋላ ትምህርት ቤቶች በሚዘጉበት ወቅት ሲደረጉ" ወደ ታደሠ የእምነት ተሞክሮ እንዲያውም ስለ ጥሪ ጠንከር ብሎ ወደማሰብም ይመራሉ” ።

በጣም በተለያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ወጣት ልጆች ለሚሽን አዳዲስ መስኮች ማግኘት ይችላሉ” ለምሳሌ ያህል" የማኅበራዊ ኔትወርኮች እውቀት ስላላቸው" በእግዚአብሔር" በወንድማማችነት እና በመሰጠት እንዲሞሏቸው ማበረታታት”።

የአዋቂዎች አብሮነት

ወጣት ልጆች ነጻነታቸው እንዲከበርላቸው ያስፈልጋል" ሆኖም ደግሞ አብረዋቸው ሊሆኑም ያስፈልጋቸዋል” ቤተሰብ በአብሮነቱ የመጀመሪያውን ስፍራ መያዝ አለበት” የወጣት አገልግሎት በዐለት ላይ እንደሚመሠረተው ቤት ሂደት(ማቴ 7:24-25) በክርስቶስ ያለውን ሕይወት ማሳየት ይችላል” ለብዙ ወጣት ልጆች" ያ ቤት" ሕይወታቸው" በትዳርና በትዳር ፍቅር ላይ ይመሠረታል” ለዚያም ነው የሐዋርያዊ እንክብካቤ ቤተሰብ" ቀጣይና አመቺ በጥሪው ሂደት እንዲኖር መተባበርና መቀናጀት ያለባቸው”።

ማኅበረሰቡ ወጣት ልጆች ጋር አብሮ የመሆን ዋነኛ ሚና መጫወት አለበት - የመቀበል" የማነቃቃት" የማበረታታት" እና የመቀስቀስ የሕብረት ኀላፊነት እንዳለበት ሊሰማው ይገባል” ሁሉም ሰው ወጣት ልጆችን በመረዳት" በማድነቅ" በመውደድ" እና አዘውትሮ መፈረጅን በማስወገድ አልያም ከዕድሜያቸው በላይ የሆነ ፍጽምናን ከእነርሱ ባለመጠበቅ ሊመለከታቸው ይገባል”።

በሲኖዱ ወቅት" “ብዙዎቹ እንዳመለከቱት አብሮ በመሆን የሚያግዙ ብቁ የሆኑ ሰዎች እጥረት አለ” የሥነ መለኮትና የማድመጥ ሐዋርያዊ እሴት ደግሞ የክህነትን አገልግሎት በትክክል መተግበሩንና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ቅድሚያ ተሰጥቷቸው እንደሆነ መመልከትን" ማሰብን እና ማደስን ያካትታል” ሲኖዱ በተጨማሪም ወጣቶች ጋር አብረው እንዲሆኑ የተቀደሱ ሰዎችን" ምዕመናን" ወንዶችንና ሴቶችን የማሠልጠን አስፈላጊነትን ተገንዝቧል” መንፈስ ቅዱስ በማኅበራት ውስጥ ወደፊት ሲጠራ የማድመጥ ስጦታ ምናልባትም እንደ ቤተክርስትያን አገልግሎት ተቋማዊ እውቅናንም ሊያገኝ ይችል ይሆናል””።

ሥልጠናና አስፈላጊውን ብቃት እንዲቀበሉ" የመሪነት ክሂል የሚያሳዩ ወጣት ወንድና ሴቶችን አብሮ ሆኖ መደገፍ ልዩ ፍላጎት አለ” ከሲኖዱ በፊት የተገናኙ ወጣት ልጆች" “ለወጣት መሪዎች የሚሆን የማነጽና ቀጣይነት ያለው እድገት መርሃ ግብሮች እንዲኖሩ” ጥሪ አድርገዋል” አንዳንድ ሴት ወጣቶች" በቤተ ክርስትያን ውስጥ የመሪነትን ሚና የሚጫወቱ አርአያ የሚሆኑ ሴቶች እጥረት እንዳለ ነው የሚሰማቸው" ያላቸውንም ሙያዊ እና የእውቀት ስጦታ ለቤተ ክርስትያን ሊሰጡ ይመኛሉ” ሴሚናሪያኖችና ገዳማውያን ለሌሎች ወጣት መሪዎች አጋር የመሆን የበለጠ ችሎታ እንዳላቸው እናምናለን””።

እነዚሁ ወጣት ልጆች በመካሪዎች ውስጥ ምን ዓይነት ጥራት ማግኘት እንደሚፈልጉ ገልጸውልን" ይህንንም ያስረዱት እጅግ በጣም ግልጽ በሆነ መንገድ ነው” “እንደዚህ ያሉ መካሪዎች የሚያካትቱት - በቤተ ክርስትያን እና በዓለም ገብቶ የሚሰራ ታማኝ ክርስትያን" አዘውትሮ ቅድስናን የሚፈልግ" በሌላው የማይፈርድና በራሱ የሚተማመን” በተመሳሳይም" የወጣቶችን ፍላጎት የሚያደምጥና ምላሽ የሚሰጥ; አፍቃሪና የራስ ግንዛቤ ያለው; ውሱንነቱን የሚያውቅ እና የመንፈሣዊውን ጉዞ ሐዘንና ደስታ የሚያውቅ” በመካሪዎች ውስጥ ሊኖር የሚገባ ዋነኛ ልዩ ነገር ራሳቸው ስብዕና እውቅና መስጠት ነው - ስህተት የሚፈጽሙ ሰብአዊ ፍጡራን የመሆናቸውን እውነታ; ፍጹማን ሰዎች ሳይሆኑ ምህረት የተቀበሉ ኀጢአተኞች” አንዳንድ ጊዜ መካሪዎች መድረክ ላይ እንዲሆኑ ይደረጋሉ" ሲወድቁ" በቤተ ክርስትያን ውስጥ መሳተፍን ለመቀጠል" በወጣት ልጆች ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ የከፋ ይሆናል” መካሪዎች ሲመሩ ወጣት ልጆች ምላሽ የማይሰጡ ተከታዮች እንዲሆኑ አድርገው መምራት ሳይሆን" ከጎናቸው አብሮ መጓዝ" በጉዞው ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ ይገባቸዋል” ከማድመጥ ሂደት ጋር የሚመጣውን ነጻነታቸውን ማክበር እና በደንብ እንዲተገብሩ በአስፈላጊ መሣርያዎች ማስታጠቅ” መካሪ" በሙሉ ልቡ ወጣት ልጆች በቤተ ክርስትያን ሕይወት ውስጥ የመሳተፍ ችሎታ እንዳላቸው ማመን አለበት” ስለዚህ መካሪ" የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች የሆኑትን ወዲያውኑ ለማየት ባለመቸኮል" በወጣት ልጆች ውስጥ የተዘራውን የእምነት ፍሬ መኮትኮት ይገባዋል” ይህ ሚና ለካህናትና ለተቀደሱ ሰዎች ሕይወት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን ምዕመኑም ይህንን ሚና ለመጫወት አቅሙን ማጎልበት አለበት” እንዲህ ያሉ ሁሉም መካሪዎች በደንብ መቀረጽና" ቀጣይነት ባለው መቀረጽ ውስጥም መስራት አለባቸው””።

የቤተ ክርስትያን ትምህርታዊ ተቋማት ያለ ምንም ጥርጥር ለመተጋገዝ የጋራ መድረኮች ናቸው; “በተለይም ለሁሉም ወጣት ልጆች" የሃይማኖት ምርጫቸው ምንም ቢሆን ምን" ከየትኛውም ባሕል ቢመጡ"የግልም ሆነ የቤተሰብ ወይም ማኅበራዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ያለ ምንም ልዩነት አቀባበል ማድረግ ሲፈልጉ" ለብዙ ወጣት ልጆች ምሪት መስጠት ይችላሉ” በዚህ መልኩ" ቤተ ክርስትያን መሠረታዊ አስተዋጽኦ በተለያየ ዓለም የሚኖሩ ወጣት ልጆችን ጥምረት በትምህርት መፍጠር ይቻላል”” ተማሪዎች እንዲገቡና በዚያው እንዲቆዩ ድርቅ ያለ መመዘኛ የሚያስቀምጡ ከሆነ" ብዙ ወጣት ልጆችን ሕይወታቸውን ሊያበለጽግ ከሚችል እገዛ እያሳጧቸው ስለሚሆን ይህንን ሚና ይገድበዋል”።

ምንጭ፡ ክርስቶስ ሕያው ነው በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለወጣቶች እና ለጠቅላላው የእግዚአብሔር ሕዝብ ከጻፉት ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ምክር ከአንቀጽ 239-247 ላይ የተወሰደ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ዳንኤል ኃይሌ ሮም።

 

16 February 2024, 16:17