በስሪላንካ የእርስ በርስ ጦርነት የፈጠረው ቁስል ሲቃኝ

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

“የኢየሱሳውያን የእርቅ እና የአንድነት እንቅስቃሴ በስሪላንካ” የተሰኘ ፋውንዴሽን ለወጣቶች የተለያዩ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር ጥረት በማድረግ ላይ ሲሆን በተለይ በትምህርቱ ዘርፍ ድጋፍ እያደረገ የሚገኝባቸውን ፕሮጄክቶችን እንመለከታለን።

ስሪላንካ ውስጥ መቆየት ወይም መሰደድ? የሚለው በምጣኔ ሃብት ድቀት እጅግ ለሚሰቃይ እና ጥቂት ተስፋ ብቻ ላለው የሲሪላንካ ተውላጅ ወሳኝ ጥያቄ ነው። የኢየሱሳውያን ማኅበር የጋራ እንቅስቃሴ እና ተግባር ለልማት “MAGIS” የተሰኘ ፋውንዴሽን በገጠራማው አካባቢዎች የሚኖረው ወጣቱ ትውልድ በተለይ በትምህርት የሚገኝ የወደፊት ሕይወት የበለጠ ግንዛቤ እና ችሎታ መምረጥ እንዲችል ዕርዳታ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ማንናር፥ በደቡብ እስያ የመጀመርያው ሰማዕትነት ቦታ

በካንዲ ውስጥ የሚገኘው “የሳቲያዳያ ማኅበራዊ ምርምር እና ግንኙነት ማዕከል” በአገሪቱ እና በመላው ዓለም የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር በነበሩበት ጊዜ ከ 53 ዓመታት በፊት የተመሠረተ ሲሆን፥ ዓላማውም መንፈሱን ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚፈልግ ማንኛውንም ሰው ለተወሰነ ጊዜ የሚያስተናግድ እና የኢየሱሳውያን ተልዕኮዎችን በጥልቀት ለማስተማር ሲሆን የማዕከሉ ፕሬዚደንት አምብሮጂዮ ቦንጆቫኒ፥ ቀድሞ “ሴሎን” በመባል የሚታወቁ እና ድጋፍ ሲደረግላቸው የቆዩ የተግባር መርሃ ግብሮች የትኞቹ እንደሆኑ ያብራራሉ።

በሰሜናዊው የአገሪቱ ክፍል በሚገኝ በማናር ግዛት ያለው ቶታቬሊ የተባለ መንደር እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1544 በነበረው ንጉሥ ካንኪሊ ትእዛዝ ከሂንዱ እምነት ወደ ካቶሊክ እምነት የመጡ ስድስት መቶ ካቶሊክ ምዕመናን የተገደሉበት እና በደቡብ እስያ የመጀመሪያው ሰማዕትነት የታየበት ቦታ ነው።

ዛሬም ቢሆን ቦታው በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛው የክርስቲያን ማኅበረሰብ የሚገኝበት ሲሆን፥ ሁለት የጅምላ መቃብሮች ባሉበት እና እልቂቱ በተፈፀመበት ቦታ ላይ የተገነባው የእመቤታችን ቅድስት ማርያም የሰማዕታት ንግሥት ቤተ መቅድሰስ ተወዳጅ የመንፈሳዊ ንግደት ሥፍራ ሆኗል።

የማይደረስ የዘንባባ ዛፎች ሃብት

በስሪላንካ ሰሜናዊ ጫፍ ላይ ያለው የመሬት ገጽታ ቀጣይነት ያለው የዘንባባ ቁጥቋጦዎች እና የሩዝ እርሻዎች የሚገኙበት ነው። በእርሻው ውስጥ ከሚበቅሉ ፍራፍሬዎች መካከል ለሕዝቡ ዋና መተዳደሪያ የሆኑት ጥሩ መጠጦች እና የ “ሽሮፕ” ዓይነቶች የሚሠራባቸው አገር በቀል ዛፎች ይገኙ ነበሩ። ነገር ግን መንግሥት መንደርተኛውን ከዚህ ሥራ በማገድ ድኅነት የበለጠ እንዲያድግ አደረገ። የዘንባባ ዛፍን በመጠቀም አጥርን፣ ጎጆዎችን እና የቤት እቃዎችን መሥራትም በእጅጉ ቀነሰ። የተለያዩ ዓይነት ዕቃዎችን በእጅ ለመሥራት የዘንባባ ቅጠሎችን መጠቀም የሚቻል ቢሆንም ነገር ግን ገበያው አነስተኛ ነው። ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ባዲስ የሥራ ዘርፍ ማለትም በየዕለቱ በመስክ ላይ በመሥራት ለኑሮ የሚያስፈልጉ ጥቂት ነገሮችን ማምረት ነበረባቸው።

ቀደም ሲል “ውዳሴ ላንተ ይሁን!” በሚል ርዕሥ ይፋ የተደረጉ ሐዋርያዊ ምክረ ሃሳቦችን የሚቃረኑ ድርጊቶች መታየት ጀመሩ። ድህነትን እና ማኅበራዊ ኢ-ፍትሃዊነትን የሚያባብስ የሃብት አያያዝ የአካባቢውን ነዋሪ የማይጠቅም ሲሆን፥ ይህ የሆነው ለክቡር ሕይወት በቂ አማራጮችን ሊያስገኝ ባለመቻሉ ነው።

ተንቀሳቃሽ ሱቅ
ተንቀሳቃሽ ሱቅ

በግብርናው ዘርፍ የሚታዩ ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ቅራኔዎች

በተለይ በአገሪቱ ውስጥ ግብርና ወሳኝ ነበር። አርሶ አደሮች በኑሮአቸው ከፍተኛ ስጋት እያጋጠማቸው ይገኛል። “ኡሩማያ” ወይም ሕዳሴ የተባለ የፕሬዝደንቱ ፕሮግራም ከጥር 27/2016 ዓ. ም. ጀምሮ ሙሉ የእርሻ ባለቤትነትን ለገበሬዎች ሰጠ። ነገር ግን ይህ በእውነት ግብርናን ተግባራዊ ለማድረግ ሳይሆን የውጭ ንግድን ለማሳደግ የተደረገ ነበር።

የመሬት እና የግብርና ማሻሻያ ንቅናቄ እንደገለጸው፥ ይህም ገበሬዎች መሬቱን በርካሽ እንዲሸጡ ለማድረግ የተደረገ ሙከራ እንደነበር አስታውቋል። ይህ ማለት የበቆሎ እና የሙዝ ሰብሎች በዋናነት በሺዎች በሚቆጠሩ ሄክታር መሬት ላይ እንዲሰራጭ መፍቀድ አለባቸው። እንዲሁም የፀሐይ ፓነሎች የሚዘረጉበት ሰፊ ሜዳዎች ወይም የድንጋይ ቁፋሮዎች መካሄድ አለባቸው። ከፍተኛ ኢንቨስትመንቶች ያስፈልጉታል። ስለዚህ ከፕሬዝደንቱ የተላለፈው መመሪያ ለገበሬዎች ጥቅም የማያስገኝ ነበር። እንዲያውም ውጥኑ ቀስ በቀስ እንደሚወገድ በአካባቢው ተነግሯል። በአገር አቀፍ ደረጃ ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚሆኑ የገበሬ ቤተሰቦችን እንደሚያካትት የታሰበው ፕሮግራሙ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2024 ሁለት ቢሊዮን ሩፒ ወይም ስድስት ሚሊዮን ዩሮ አካባቢ በጀት ተመድቦለት ነበር።

አካባቢያዊ ተፃፃሪቱ

አንድ ሰው በማናር የሚገኝ የኢስቱመስ ድንበር በተሻገረ ቁጥር፥ ከሕንድ የሚመጡ የአደንዛዥ ዕጽ ጭነቶች ወደ ስሪላንካ እንዳይገቡ ለመከላከል በተመደበ የፖሊስ ኃይል መፈተሽ አለበት። የኢየሱሳውያን ማኅበር በስሪላንካ በ48 መንደሮች ውስጥ ይሠራሉ። ከእነዚህ መካከል 20 የሚያህሉ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የሚደርስባቸው አይደሉም።

ከመናር ከተማ በጣም ርቀው ከሚገኙት መንደሮች ውስጥ 85 ቤተሰቦችን መጎብኘት ማለት መሠረታዊ መሠረተ ልማት የሌለበትን አካባቢ ማሰስ ማለት ሲሆን፥ ከሰላሳ ዓመታት በፊት የነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት ሁኔታ እስከ ዛሬ ድረስ ቆይቷል። ከቁምስናዎች ዕርዳታን ማግኘት የሚችል ቢሆንም፥ ነገር ግን በአካባቢው የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች በተበላሸ ሁኔታ ላይ የሚገኙ እና ጥቂት የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች የሚገኙባቸው በመሆኑ የንፅህና አጠባበቅ እጦት ይታይባቸዋል።

ከሕንድ ደቡባዊ ክፍል በታች ባለው መሬት ላይ የቆሙ በርካታ ግዙፍ የነፋስ ተርባይኖች በአንድ በኩል ለወደፊት የሚታሰበው ዘላቂ የኃይል ምርት ምልክት ሲሆን በሌላ በኩል አካባቢያዊ ተፃፃሪነቱ ግምት ውስጥ የገባበትን የወደፊት ዕይታ የተነፈገበት ሁኔታ ያመልክታል።

የድርጅቱ ዳይሬክተር አባ ሮበርት
የድርጅቱ ዳይሬክተር አባ ሮበርት

የሕጻናት እና የወጣቶች ሕልም

ብዙውን ጊዜ አራት ልጆች ባሉበት ቤተሰብ ውስጥ አንዱ ብቻ ትምህርቱን መከታተል ይችላል። መምህርነት፣ የባንክ ሥራ አስኪያጅነት ወይም ክኅነት በቀለማት ባሸበረቁ የመማሪያ ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ ሕጻናት የሚገለጹ ሕልሞች ናቸው።

በማዕከሉ ውስጥ ከሚገኙ ከፍ ያሉ ልጆች መካከል አንዲት ልጅ ብዙ መስዋዕትነት የሚከፈለባት አገሯን ለቃ መውጣት እንደምትፈልግ ትናገራለች። በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ ሰላሳ ኪሎ ሜትር ትጓዛለች። ወደ ቤቷ ስትመለስ በመንደሩ 42 ሰዎች ይጠብቋታል። ለእነዚህ ሰዎች የምትሆን አንድ ትንሽ የውሃ ጉድጓድ አለቻቸው። “ምናልባት በኋላ ሳድግ ወደ ስሪላንካ ልመለስ እችል ይሆናል” በማለት ትናገራለች። ነበር ግን ሌላዋ ወጣት የታሚል ባህልን ለማስተዋወቅ ስትል በተወለደችበት አካባቢ እንደምትቆይ ለቤተሰቧ ቃል ገብታለች።

የእርስ በርስ ጦርነት ምልክቶች

“በአምስቱ ዓመታት ውስጥ በማናር የኢየሱሳውያን ገዳም ውስጥ የበላይ አለቃ ሆነው ባገለገሉባቸው አምስት ዓመታት ያዩትን የሚገልጹት አባ ሮበርት፥ የእርስ በርስ ጦርነት ያስከተለው ጉዳት አሁንም በሰዎች መካከል እንደሚታይ ገልጸው፥ ለ25 ዓመታት የተካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት ወደ 100,000 የሚጠጉ ሰዎች ሕይወት የቀጠፈ እንደ ነበር ተናግረዋል።

በሲሪላንካ የተቀሰቀሰው የደም አፋሳሽ ግጭት መነሻው በሀገሪቱ ሰሜናዊ ምሥራቅ ከሚገኘው ትልቁ የታሚል ማኅበረሰብ ጋር የሲንሃሌዝ ማኅበረሰብ እኩል እውቅና ባለማግኘቱ ነበር። እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1976 ዓ. ም. የተመሠረተው የታሚል ኢላም ነፃ አውጪ አማጽያን እስከ መገንጠል ድረስ የትጥቅ ትግል ማካሄድን መረጠ። 

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2002 ዓ. ም. መንግሥት እና የታሚል ኢላም ነፃ አውጪ አማፂያን በኖርዌይ ሸምጋይነት የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈራረሙ። ይሁን እንጂ በቀጣዩ ዓመት ጦርነቱ እንደገና ተጀምሮ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ እስከ 2009 ዓ. ም. ድረስ ብዙ ደም ከፈሰሰ በኋላ የታሚል ኢላም ነፃ አውጪ ቢሸነፍም ጥያቄው በሙሉ ተመልሶለት መፍትሄ ተገኘ።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2012 ዓ. ም. የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ስሪላንካ ከታሚል ኢላም ነፃ አውጪ አማጽያን ጋር በነበረው ግጭት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ተፈጽሟል የተባለውን የጦር ወንጀል እንድትመረምር አሳሰበ። ነገር ግን ኮሎምቦ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2016 ዓ. ም. ወደ 65,000 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ አመነ።

እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ 2021 እና 2022 ዓ. ም. መካከል የምጣኔ ሃብት ቀውሱ ተባብሶ ወደ አጠቃላይ ውድቀት በመድረስ የጎዳና ላይ አመጾችን አስከተለ። የቀድሞ የጦር አርበኛ በሕዝብ ተቃውሞ ከሀገር እንዲወጣ ተደረገ።

ወጣቶች በሎዮላ የመማሪያ ማዕከል ውስጥ
ወጣቶች በሎዮላ የመማሪያ ማዕከል ውስጥ

የኢየሱሳውያን የእርቅ እና የአንድነት እንቅስቃሴ በስሪላንካ ያከናወነው ተግባር

የኢየሱሳውያን የእርቅ እና የአንድነት እንቅስቃሴ በስሪላንካ “MAGIS” የሚል ድርጅት ዳይሬክተር ኢየሱሳዊ ካህን አባ ሮበርት በዋናነት ለታሚል ሕዝብ የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት የሚሰጥ ማዕከል እንቅስቃሴን በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ብዙ ወጣቶች ወደ ማዕከሉ ገብተው ለመማር ጥያቄ ቢያቀርቡም ማዕከሉ እስከ መቶ ተማሪ ብቻ መቀበል እንደሚችል እና ከቅድመ-ኮሌጅ ጀምሮ አንዳንድ የኮምፒዩተር ሳይንስ እና ግራፊክስ ትምህርቶችን እንደሚሰጥ አስረድተዋል። በመጀመሪያ ተቋሙ በኢየሱሳውያን የዕርዳት ማስተባበሪያ አገልግሎት ባለቤትነት የተያዘ ሲሆን ይህም ለታሚል ስደተኞች መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎችን ያሰራጭ እንደ ነበር እና አሁን በተወሰነ መልኩ ለአዲስ ተግባር መዋሉን አስረድተዋል።

የማዕከሉ መምህራን እና እናቶች ያደረጉት አስደናቂ ዕርዳታ ለማዕከሉ ዕድገት አስተውጽዖ ማድረጉን የገለጹት አባ ሮበርት፥ የቁምስናው መሪ ካኅን ወጣቶችን በብልሃት መያዝ መቻሉ እና የአካባቢው ካቶሊክ ማኅበረሰብ አጋዥ ኃይል እንደሆነ ገልጸው፥ ይህም በአምልኮ ሥነ-ሥርዓቶች እና በስብሰባ ወቅቶች የሚያሳዩት የባለቤትነት ስሜት እና ለሕይወት፣ ለማኅበራዊ መታደግ እና የግል መብቶችን ለማወቅ አስፈልጊ እንደሆነ በማስረዳት፥ ሕጻናቱ ለተወደዱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መዝሙር እንዲዘምሩላቸው እያስተባበሩ፥ ይህን የደስታ ዝማሬያቸውን ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መላክ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።

ሕጻናቱ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዘመሩት የደስታ መዝሙር

 

14 March 2024, 15:13