በሶሪያ የሚገኙ የካቶሊክ መሪዎች በወገኖቻቸው ላይ የበለጠ ስቃይ ይደርሳል ብለው ይሰጋሉ!
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን
ሊቀ ጳጳስ ሳሚር ናሳር በደማስቆ በሚገኘው የኢራን ኤምባሲ ላይ የእስራኤል መንግሥት ገዳይ የሆነ ጥቃት ማድረሱ ከፍተኛ ውጥረት የፈጠረ እና እየጨመረ የሚሄደውን የሶሪያውያንን ሁኔታ ሊያባብሰው እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል።
ከኤሺያ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የሀሌፖ ማሮናዊት ሊቀ ጳጳስ በሶሪያ ያለውን ሁኔታ "ሰዎች ያለማቋረጥ ቁራሽ ዳቦ፣ ነዳጅ፣ ሁሉንም ዓይነት መድሀኒት እየፈለጉ ትንሿን ችግራቸውን እንኳን ለማርካት ሳይቀር እየፈለጉ ነው" ሲሉ ገልፀውታል።
እስራኤል በደማስቆ በሚገኘው የኢራን ቆንስላ ህንጻ ላይ ባደረገችው ጥቃት 7 ኢራናውያን እና 6 የሶሪያ ዜጎችን ጨምሮ 13 ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል። ኢራናዊው ጀነራል መሀመድ ረዛ ዛህዲ የእስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ የቁድስ ልዩ ሃይል አዛዥ እና ምክትላቸው መሀመድ ሃዲ ሃጅሪያሂሚ ላይ ያነጣጠረ ነው ተብሏል። እስራኤል ኢራንን በሊባኖስ ላሉ የሂዝቦላ ሚሊሻዎች የጦር መሳሪያ ታቀርባለች ስትል ትከሳለች።
የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት መባባስ ስጋት
የኢራን ጠቅላይ መሪ እስራኤልን በጥቃቱ ምክንያት "ለመቅጣት" የገቡት ቃል በጋዛ ያለው ጦርነት በአካባቢው ከፍተኛ ግጭት እንዳይፈጠር ስጋት ፈጥሯል።
የማንቂያውን ደውል ከሚያሰሙት መካከል የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ “የሚመለከታቸው ሁሉ ከፍተኛ ቁጥጥር እንዲያደርጉ እና ተጨማሪ መባባስ እንዳይፈጠር” ጠይቀዋል።
በደማስቆ ከሰኞ ድብደባ በፊት ባሉት ሳምንታት ውስጥ፣ “እስራኤል በሶሪያ ሰሜናዊ ክፍል ኢላማዎችን መምታቷ ተዘግቧል፣ የሀሌፖ ሐዋርያዊ ቪካር ለኤሺያኒውስ እንደገለጹት ከሆነ በተባለው ጥቃት 35 ሰዎች መሞታቸውን ዘግቧል።
የሶሪያ 'የተረሳ' ግጭት
እ.ኤ.አ. በሐምሌ 2023 የሀሌፖ ሐዋርያዊ ቪካር ሆነው የተሾሙት ጳጳስ ሃና ጃሎፍ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሶሪያ ያለውን ግጭት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስታወሳቸው “ከ13 ዓመታት በላይ የቆየ እና በአብዛኛው የተረሳ ግጭት” ብለው ጠርተው ስለችግሩ ስፋት በማውሳታቸው አመሰግናለሁ ማለታቸው ተገልጿል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ ባለፈው እሁድ በተከበረው በፋሲካ በዓል እሁድ ላይ ስለ ሶሪያ አጽኖት ሰጥተው እንደተናገሩ ተናግሯል።
"በእርግጥም ከነዚህ ሁሉ አመታት በኋላ አለም ሶሪያን የረሳ ይመስላል ነገር ግን አሁንም ጦርነት አለ እዚህም ላይ በመሬት መንቀጥቀጡ ያስከተለው ውድመት ተጨምሯል [እ.አ.አ የካቲት 6/2023]። ትኩረታቸውን ወደ ኋላ ስለመለሱ ጳጳሱን እናመሰግናለን። ሶርያ ወደ ሰላምና ብልጽግና እንድትመለስ” ልንጸልይ የግባል ሲሉ ጳጳስ ጃሎፍ አክለው ተናግረዋል።
በሶሪያ በሚገኘው በኢራን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ላይ ስለደረሰው ጥቃት አስተያየት ሲሰጡ “አሁን የበለጠ ፍርሃት አለ ምክንያቱም እስራኤል በውጭ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ስትሰነዝር የመጀመሪያ ጊዜ ስለሆነ ፣በአለም አቀፍ ስምምነቶች የተከለለ ክልል ፣ከሁሉም ቀይ መስመሮች በልጦ የወጣ ድርጊት ነው። ይበልጥ አሳሳቢ የሆኑ ምላሾችን እና መዘዞችን በማስከተል እንደሚቀጥል” ያላቸውን ሥጋት ገልጸዋል።