2024.04.16 Camerun, Ebolowa. Un momento dei funerali di suor Maria José

"በመንፈስ መሪነት የሚካሄዱ ውይይቶች" ሴቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲያጠናክሩ ይረዳል!

የዓለም የካቶሊክ ሴቶች ማኅበራት (WUCWO) ፕሬዚደንት ሞኒካ ሳንታማሪና ከቫቲካን ዜና ጋር ስለ ሲኖዶስ ሁለተኛ ክፍል ዝግጅት በተመለከተ በበይነ መረብ የተደርገ ቃለ ምልልስ ማድረጋቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ሲኖዶሳዊውን ዘዴ ይተግብሩ እና በተልእኮ ላይ የሴቶች ተሳትፎ በሲኖዳላዊ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማዕከል ያድርጉ፣ ይህ እ.አ.አ በመጪው ማክሰኞ ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም በበይነ መረብ ዙም የሚካሄደው እና በአለም ዓቀፋዊው ሕበረት የሚዘጋጅ ስብሰባ ሲሆን “በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የሚካሄድ ውይይት” እንደ ሚሆን ይጠበቃል። በሲኖዶሳዊ መንገድ ማዕቀፍ ውስጥ የካቶሊክ የሴቶች ድርጅቶች (UMOFC) ከፍተኛ የሆነ አስተዋጾ እንደሚኖረው ይጠበቃል።

ሲኖዶሳዊ ትምህርት ቤት

የድርጅቱ ሊቀ መንበር ሞኒካ ሳንታማሪና ለቫቲካን ዜና እንዳስረዱት ሐሳቡ የሲኖዶሳዊ ትምህርት ቤት አካል እንደሆነና በዚህ መርሐ ግብር በርካታ ሴቶች በአምስቱ አህጉራት ሥልጠና እየወሰዱ እንደ ሆነ የገለሱ ሲሆን ትንንሽ ቡድኖችን ያማክራሉ እና ንግግሮቹ በተቀመጠው ተለዋዋጭነት መሰረት እንዲዳብሩ ያደርጋሉ። ከመላው አለም እስከ 1,400 ሰዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ሲሉ ለቫቲካን ዜና ተናግረዋል።

ስብሰባው ትንንሽ ቡድኖችን መፍጠር እና በተለያዩ ቋንቋዎች (እንግሊዝኛ፣ ስፓኒሽ እና ፈረንሳይኛ) እያንዳንዱ ተሳታፊ ሃሳቡን እንዲያካፍል እና ሌሎች ልምዶችን እና አመለካከቶችን እንዲያዳምጥ ያስችላል ያሉት ዋና ጸኃፊዋ እያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ ለአንድ ሰዓት ተኩል የሚቆይ ሲሆን ፍላጎት ያላቸውም ሰዎች ከወዲሁ መመዝገብ እንደሚችሉ ገልጸዋል። ቦታው የተገደበ ነው እና ምዝገባው በሚያዝያ 10/2016 ዓ.ም እንደሚያበቃ የገለጹት ዋና ኃላፊዋ እንደ አስፈላጊነቱ ታይቶ የምዘገባው ቀን ሊራዘም እንደሚችል ተገልጿል።

ከዚህ ቦታ በተጨማሪ የጳጳሳት ሲኖዶስ 16ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ 2ኛ ዙር ጉባኤ ለመዘጋጀት የዓለም የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሴቶች ሕብረት ድርጅት የተሳተፉትን ሴቶች ምስክርነት ለማካፈል ተከታታይ የቪዲዮ ዝግጅቶችን ለመክፈት አቅዷል።

የሴቶችን ፀጋዎችን እና አቅም በሚገባ መጠቀም

ሳንታማሪና የመክፈቻ መንገዶችን አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥታ ገልጸዋል፣ የሴቶችን ውዴታ እና እምቅ አቅም በተሻለ መንገድ መጠቀም፣ "ምክንያቱም ሁልጊዜ እንደዚህ አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል። እንደዚሁም የእነዚህን ውይይቶች ውጤት ለሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽህፈት ቤት እና ለሰፊው ሕዝብ ማሳወቅ ይፈልጋሉ። በተራው፣ ብዙ ሴቶችን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች እና ሚናዎች ውስጥ ማካተት ስለሚቻልባቸው መንገዶች፣ እንዲሁም ስለሚያስፈልጉት ለውጦች እና ለምን እንደሆነ ግንዛቤን ያጠናክራሉ።

የዓለም የካቶሊክ ሴቶች ሕብረት ማኅበራት (WUCWO) ፕሬዚደንት ሞኒካ ሳንታማሪና ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለድርጅቱ ሥራ ያደረጉትን ድጋፍ በተመለከተ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል። እንዲያውም ቅዱስ አባታችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በጣም ተጋላጭ የሆኑትን ለመድረስ መሥራታቸውን ለመቀጠል እና የዚህ ታዛቢ ሀሳብ በትክክል ፣ በሆነ መንገድ ፣ የማይታየውን እንዲታይ ለማድረግ ነው ሲሉ የዓለም የካቶሊክ ሴቶች ሕብረት ማኅበራት (WUCWO) ፕሬዚደንት ሞኒካ ሳንታማሪና መናገራቸው ተዘግቧል።

 

17 April 2024, 21:32