የቅድስት ሀገር ተንከባካቢ ካህን አባ ፍራንቸስኮ ፓቶን- የፋይል ፎቶ የቅድስት ሀገር ተንከባካቢ ካህን አባ ፍራንቸስኮ ፓቶን- የፋይል ፎቶ 

አንድ የቅድስት ሀገር ካህን ‘የክርስቶስ ባዶ መቃብር በእኛ ውስጥ ተስፋን ይፈጥራል’ አሉ

በኢየሩሳሌም የሚገኙት የቅድስት ሀገር ተንከባካቢ ካህን የሆኑት አባ ፍራንቺስኮ ፓቶን ለምእመናኖቻቸው ባስተላለፉት የትንሳኤ መልእክት የኢየሱስ ክርስቶስ ባዶ መቃብር “ለክርስቲያኖች ትልቅ ተስፋን እንደሚሰጥ” ካረጋገጡ በኋላ፥ ሁሉም መከራዎች በጌታ ትንሳኤ መጽናናትን እንደሚያገኙ ጠቁመዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

"ትንሳኤ አንድ ሰው ሊገምተው ወደማይችለው 'አዲስና ሙሉ ወደሆነ የሕይወት መንገድ የሚወስደን' ሲሆን፥ ይህንንም የሚያስታውሰን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል ነው" ምንም እንኳን በቅድስት ሀገር ያለው ስቃይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየባሰበት ቢሆንም፣ ይህ በቅድስት ሀገር ያሉት አባታችን አባ ፍራንቺስኮ ፓቶን ለፋሲካ በዓል የላኩልን መልዕክት የመጽናኛ ቃላት ናቸው። 

ካህኑ “ከሞት ጨለማ ባሻገር” በሚል ርዕስ የጻፉት ጽሑፍ፥ የሰው ልጅ በተለይም የሚወዱት ሰው ሞትን በሚጋፈጥበት ጊዜ በአእምሮው እየመጣ ለሚያስጨንቀው ጥያቄ ምን ማድረግ እንዳለበት የሚያግዝ መልስ እንዲያገኝ ይረዳል።

“በእያንዳንዳችን ላይ የሚወርደው እና ወደ “ማይቀለበስ የሞት ምስጢር የሚወስደን” የመከራ፣ የጨለማ እና የተስፋ መቁረጥ ጊዜን” ተከትሎ የሚመጣ የህይወት ልምድ “ከነዚህ ነገሮች በላይ አሻግረን እንድንመለከት” ይረዳናል ይላሉ አባ ፓቶን።

መግደላዊት ማርያም እና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኤማሁስ ሲሸሹ እንደነበረው ሁሉ፣ “የተገለጠው አስደናቂ ነገር” ከሞት ከተነሳው ኢየሱስ ጋር መገናኘት ነው ብለዋል።

ይህ ከጌታ ጋር የመገናኘት ሚስጥር ምንጊዜም የበለጠ ትርጉም ያለው ነገር ነው፥ ይህ ማለት “በአሁኑ ሰዓት በአባቱ ዘንድ ከሚኖረው እና የሰው ልጅነቱ “አሁን ሙሉ በሙሉ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ከተለወጠው፣ እንዲሁም ሞትን ከተለማመደው እና ከሞት ባሻገር ያለውን ነገር ካሳየን ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መገናኘት” ማለት ነው ሲሉ ያጽናኑናል።

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ባዶ መቃብር “ተስፋን ያመጣልናል” ያሉት አባ ፓቶን ሃሳባቸውን ሲያጠቃልሉ፥ “ዛሬ እንኳን ተዘፍቀንበት የምንገኝበትን እጅግ አስከፊ የህይወት እና የሞት ጎዳናዎችን ማብራት የሚችል ነው” ብለዋል።

የቅድስት ሀገር ተንከባካቢ ካህን የሆኑት አባ ፍራንቺስኮ ፓቶን ለመላው ምእመናን መልካም የትንሳኤ በዓል እንዲሆን በመመኘት አጠቃለዋል።
 

02 April 2024, 15:20