የዓለም የወጣቶች ቀን እ.አ.አ 2024 በፖርቱጋል በተከበረበት ወቅት የዓለም የወጣቶች ቀን እ.አ.አ 2024 በፖርቱጋል በተከበረበት ወቅት   (AFP or licensors)

ክርስቶስ ሕያው ነው! ተስፋችን ነው

መለየት

በ “ተደሰቱ ሐሴትም አድርጉ” በተሰኘው ሐዋርያዊ ምክር ውስጥ " ስለ መለየት አጠቃላይ በሆነ መልኩ ተናግሬያለሁ” አሁን ከእነዚያ ውስጥ ጥቂቶቹን በመውስድ በምድር ላይ ጥሪያችንን እንዴት እንደምንለይ መናገር እወዳለሁ” በዚያ እንደገለጽሁት" ሁላችንም ብንሆን" ነገር ግን “በተለይ ወጣት የሕብረተሰብ ክፍሎች በመዋለል ባሕል ውስጥ የተዘፈቁ ናቸው” ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ስክሪኖችን በአንድ ጊዜ ከፍተን ከሁሉም ጋር መግባባት እንቸላለን”።

የመለየት ጥበብ ከሌለን ለመጣው አዲስ ነገር ሁሉ ተጠማጅ እንሆናለን”” በእርግጥም" “አንዳንድ አዳዲስ ነገር ራሱን ወደ ሕይወታችን ሲያመጣ" መለየት በጣም አስፈላጊ ነው” ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የመጣ አዲስ ወይን ነው ወይስ ከዚህ ዓለም መንፈስ አልያም ከዲያቢሎስ መንፈስ ነው ለሚለው መወሰን እንችላለን””።

እንዲህ ያለ መለየት" “ምንም እንኳን ምክንያታዊነትንና ጥንቃቄን የሚያካትት ቢሆንም" ከነዚያም ግን ያልፋል" ምክንያቱም እግዚአብሔር ለእያንዳንዳችን ያለውን የተለየና ምስጢራዊ ዕቅድ በጨረፍታ ማየትን ይሻል ..... በአብ በሚያውቀኝ እና በሚወደኝ ፊት" ተጨባጭ በሆነው የመኖሬን ምክንያት ከእርሱ በተሻለ ማንም የሚያውቀው በሌለ" ከሕይወቴ ትርጉም ጋር ጉዳይ አለው””።

እዚህ ጋ መለየት በጥልቀት እንዲያድግ እና ለእግዚአብሔርም ታማኝ እንዲሆን የሚያደርገውን የኅሊናን መቀረጽ አስፈላጊነት ማየት እንችላለን - “ በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ የነበረውን አሳብ ለማልማት" ለምርጫዎቹ እና ከድርጊቶቹ ጀርባ የነበሩትን አሳቦች ለማሳደግ" ኅሊናችንን መቅረጽ የሕይወት ዘመን ክንዋኔ ነው”” (ፊሊ 2:5)።

በዚህ በኅንጸት ሂደት ውስጥ" “ኅሊናችንን የምንፈትሽበት አንዱ አካል የሆነው መልካም መሥራት ባህርያችን እንዲሆን እያሳደግን ባለንበትም እንኳን ቢሆን" በክርስቶስ እንድንለወጥ እናደርጋለን” ኀጢአትንን ብቻ አይደለም ለይተን የምናውቀው" በሕይወታችን ውስጥ" በግል ታሪካችን ጉዳዮች እና በዙሪያችን ባለው ዓለም" ከእኛ አስቀድመው ያለፉ ወይም ደግሞ በጥበባቸው ከእኛ ጎን በሚቆሙ ሰዎች ምስክርነት" እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ እናውቅበታለን” ይህ ሁኔታ" በመጠንቀቅ ጸጋ እና ስጦታዎቻችንን ውሱንነታችንንም በተመለከተ የተረጋጋ ግንዛቤ እንዲኖረን" አጠቃላይ ለሕይወታችን አቅጣጫ ተጨባጭ የሆኑ ምርጫዎችን በመስጠት እንድናድግ ይረዳናል””።

ጥሪያችሁን መለየት

የመለየት አንዱ ይዘት የራሳችንን ጥሪ የማግኘት ጥረትን ያካትታል” ይህ ጉዳይ ሌሎች ስለ እኛ የማይወስኑት የግል ጉዳይ በመሆኑ" በተወሰነ ደረጃ ለብቻ መሆንንና ጸጥታን የሚጠይቅ ነው” “ጌታ በተለያየ መንገድ ይናገረናል" በሥራ ላይ ሆነን" በሌሎች ሰዎች እንዲሁም በሁሉም ወቅት” ዳሩ ግን የእግዚአብሔርን ቋንቋ ለመረዳት" ተቀብለናል ብለን ያመንነውን ትርጓሜ" ጭንቀታችንን ለማረጋጋት እና በእርሱ ብርሃን ሕልውናችንን እንደገና ለማየት" ረዘም ያለ ጊዜ ወስደን በጸጥታ ካልሆንን ልንሰማ አንችልም””።

ይህ ጸጥታ ግን ራሳችንን እንድንዘጋ አያደርገንም” “በጸሎት መንፈስ የሆነ መለየት ለማድመጥ ልብን ከመክፈት የሚነሣ ነው - ጌታን እና ሌሎችን" በአዳዲስ መንገዶች የሚፈትነን ነባራዊ ሁኔታውን ራሱንም ማድመጥ” ለማድመጥ ዝግጁዎች ከሆንን ብቻ" የራሳችን የሆነውን ጎዶሎ ወይም በቂ ያልሆኑ አሳቦችን ወደ ጎን መተው እንችላለን ..... በዚህ መንገድ" በእውነትም ወደ መልካም ሕይወት የሚመራንን ጥሪ ለመቀበል ልባችንን መክፈት አንችላለን” ሁሉም ነገር የተረጋጋና ሠላማዊ መሆኑ በቂ አይደለም” እግዚአብሔር ምናልባት ከዚያ የበለጠ ነገር ያቀርብልን ይሆናል" ነገር ግን በተመቻቸንበት ያለማስተዋላችን ውስጥ ስለምንሆን" አናውቀውም ወይም ልብ አንለውም””።

የራሳችንን ጥሪ ለመለየት በፍለጋ ውስጥ ሆነን" ልንጠይቅ የሚገቡን አንዳንድ ጥያቄዎች ይኖራሉ” ገንዘብ በደንብ የት እንደምናገኝ" አልያም ከፍ ያለ እውቅናና በሕብረተሰቡ ውስጥ የሚኖረንን ቦታ እንዴት ማሳካት እንደምንችል በማሰብ መጀመር የለብንም” ምን ዓይነት ሥራ ለኛ አስደሳች እንደሚሆንም ከመጠየቅ አንጀምርም” ከመንገድ ፈቀቅ ማለት ከሌለብን" ከእነዚህ የተለየ የመነሻ ነጥብ ያስፈልገናል” መጠየቅ የሚያስፈልገን - ከስሜቶቼና ከምመኛቸው ነገሮች በላይ ራሴን በደንብ አውቃለሁ? ወደ ልቤ ሐዘንን ወይም ደስታን ምን እንደሚያመጣ አውቃለሁ? ጥንካሬዎቼና ድካሞቼ የትኞቹ ናቸው? እነዚህ ጥያቄዎች ወዲያውኑ ሌሎች ጥያቄዎች እንዲከተሉ ያደርጋሉ - ከዚህ በተሻለ እንዴት ነው ሰዎችን ማገልገል እና ቤተ ክርስትያንና ለምድራችን መርዳት እንደምችል የማረጋግጠው? በዚህ ምድር ላይ እውነተኛ ስፍራዬ የቱ ነው? ለሕብረተሰቡ ምን መስጠት እችላለሁ? ይበልጥ ትክክለኛ የሆኑ ጥያቄዎች ከዚያ ይከተላሉ - ይህንን ዓይነት አገልግሎት የመስጠት ችሎታዎቹ አሉኝ? እነዚያን ችሎታዎች ማሳደግ እችላለሁ?

መለየታችን ወይም ማድመጣችን ሕይወታችን ከሌሎች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማየት እንዲመራን" እነዚህ ጥያቄዎች ከእኛ በበለጠ ሌሎችን ያማከለ ሊሆን ይገባዋል” ለዚያም ነው ከሁሉም የሚበልጠውን ጥያቄ የማሳስባችሁ” “አብዛኛውን ጊዜ በሕይወት ውስጥ" ራሳችንን ጥያቄ በመጠየቅ ጊዜያችንን እናጠፋለን - “እኔ ማን ነኝ?” ደጋግማችሁ" “እኔ ማን ነኝ?” እያላችሁ በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ መጠየቅ ትችላላችሁ” ነገር ግን ትክክለኛው ጥያቄ - “እኔ ለማን ነኝ?”159 ነው” እርግጥ ነው" ለእግዚአብሔር ናችሁ” ነገር ግን እርሱ የወሰነው ለሌሎችም እንድትሆኑ ነውና" የተለያዩ ችሎታዎችን" ዝንባሌዎችን"ስጦታዎችን እና ጸጋዎችን ለራሳችሁ ሳይሆን የሰጣችሁ በዙሪያችሁ ካሉ ጋር እንድትካፈሉ ነው”።

ምንጭ፡ ክርስቶስ ሕያው ነው በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለወጣቶች እና ለጠቅላላው የእግዚአብሔር ሕዝብ ከጻፉት ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ምክር ከአንቀጽ 270-286 ላይ የተወሰደ።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ዳንኤል ኃይሌ ሮም።

 

31 May 2024, 13:21