ጥቅምት 2023 (እ.አ.አ.) በተካሄደው የሲኖዶስ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት ተሳታፊዎች አብረው ሲጸልዩ ጥቅምት 2023 (እ.አ.አ.) በተካሄደው የሲኖዶስ የመጀመሪያ ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት ተሳታፊዎች አብረው ሲጸልዩ  (ANSA)

የፕሪቶሪያው ሊቀ ጳጳስ ካህናት ለሲኖዶሳዊ ማህበረሰቦች እንደ ብርሃን ሆነው ያገለግላሉ አሉ

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ወደ ሁለተኛው የሲኖዶስ ጠቅላላ ጉባኤ እየተቃረበች ባለችበት በአሁኑ ወቅት፥ የፕሪቶሪያው ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ዳቡላ ፓኮ እንደተናገሩት ካህናት በማህበረሰባቸው ውስጥ ያለውን የሲኖዶሳዊነት አንቀሳቃሽ ሃይል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ሲኖዶስ የሚለው ቃል የእግዚአብሔር ሰዎች አብረው የሚጓዙበትን መንገድ ያመለክታል፥ በተመሳሳይ መልኩ ራሱን እንደ “መንገድ፣ እውነትና ሕይወት” የሚያቀርበውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ያንጸባርቃል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ቤተክርስቲያ ኅብረት እንዲኖራት ባቀረበው ጥሪ በመነሳሳት፥ በህብረት እና በጋራ አብሮ የመጓዝ ሲኖዶሳዊነትን በማስተዋወቅ፥ የበለጠ ሁሉን ያሳተፈች፣ በሲኖዶሳዊነት የምትተባበር ሲኖዶሳዊ ቤተ ክርስቲያን፣ ሁሉም አባላት በቤተክርስቲያኑ ሕይወት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉበት ቤተክርስቲያን እንድትሆን ጥሪ አቅርበዋል።

ሁለተኛው የሲኖዶስ ጉባኤ እየተቃረበ ሲመጣ ግን ‘እንዴት ነው እነዚህን ጥሪዎች የምናሳካው?’ በሀሳብ እና በእውነታው መካከል ያለውን ልዩነት እንዴት ማገናኘት እንችላለን? የሚል አንድ ወሳኝ ጥያቄ ይነሳል ያሉት በደቡብ አፍሪካ የፕሪቶሪያው ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ዳቡላ ፓኮ ከቫቲካን ዜና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “ካህናት ለሲኖዶሱ ማኅበረሰቦች መሸጋገሪያ ድልድይ መሆን አለባቸው” ሲሉ ጠቃሚ አስተያየት ሰጥተዋል።

ከተዋረድ እስከ ትብብር

የፕሪቶሪያ ሜትሮፖሊታን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብጹእ አቡነ ዳቡላ ፓኮ፣ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የ “መሰረታዊ ለውጥ” አስፈላጊነትን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ይህ ለውጥ ካህናትን ማዕከል ካደረገው አካሄድ ወደ ሲኖዶሳዊው አካሄድ መሸጋገርን ይጠይቃል ያሉት ብጹእነታቸው “ካህናት መሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ማህበረሰቦች የጋራ ውሳኔዎችን እንዲቀበሉ አበረታች መሆን አለባቸው” ሲሉ መክረዋል።

ሊቀ ጳጳስ ዳቡላ ፓኮ እንዳሉት፣ ቤተክርስቲያን በሁሉም ደረጃዎች ማለትም በግል፣ በሰበካ፣ በሀገረ ስብከት፣ እና በሁለንተናዊቷ ቤተክርስቲያን ደረጃ ‘‘መንፈሳዊ ለውጥ” ያስፈልጋታል ካሉ በኋላ፥ ይህ ለውጥ የካህናትን አመለካከትና ልማድ መለወጥ እንደሚያስፈልግ ጭምር ገልጸው፥ ይሄን ማድረግ ወሳኝ ነገር ነው ብለዋል።

ከዚህ ይልቅ ካህናት “ለሲኖዶሱ ማኅበረሰቦች ቀስቃሽ እና አገናኝ ድልድይ” እንዲሆኑ ተጠርተዋል። ይህ አዲስ ሚና በትብብር መንፈስ ካህናት እንደ አስተባባሪዎች እና መሪዎች ሆነው የሚሰሩበት፣ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ የምእመናን እና ገዳማዊያን እህቶችን እና ወንድሞችን ድምጽ የሚያሰሙበት አሰራር መሆን አለበት ብለዋል።

ሲኖዶሳዊ ምግባራትን መቀበል

ይህ አዲስ ሞዴል “የሲኖዶሳዊ ባህሪን ማጎልበትን ይጠይቃል” ያሉት ሊቀ ጳጳስ ፓኮ፥ መሪዎች ብዙውን ጊዜ የተገለሉ ሆነው የሚሰማቸውን ሰዎች ድምጽ በጥሞና ለማዳመጥ እስከ ጥግ ድረስ መሄድ አለባቸው በማለት አብራርተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ለተለያዩ አመለካከቶች ክፍት መሆንን እና ራስን ወደ ተሻለ ነገር ለማሻገር እና አዳዲስ ግንዛቤዎችን በትህትና ለመቀበል ፈቃደኛ መሆንን ይጠይቃል ብለዋል።

ሊቀ ጳጳሱ በአጥቢያ ቤተክርስቲያናት ውስጥ ብቻ ሳይሆን በሀገረ ስብከቶች እና በዓለም አቀፉ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በአንድነት መጓዝ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ብጹእነታቸው ሲኖዶሳዊነት ችግሮችን መፍታት ብቻ ሳይሆን አወቃቀሮች እና ሂደቶች በተፈጥሯቸው የትብብር መንፈስን የሚያንፀባርቁበት በመንፈስ ቅዱስ የተዋሃደች አዳዲስ የቤተ ክርስቲያን አሰራርንም መፍጠር ጭምር ነው ካሉ በኋላ፥
ይህም ማለት ከላይ ወደ ታች ካለው የቤተክርስቲያን መዋቅራዊ ሞዴል ወደ ሁሉምንም ሰው ወዳካተተው፣ ማለትም የካህናት እና የምእመናን ድምፅ ወዳለበት መሸጋገር ማለት ነው ብለዋል። “ይህም የነበሩትን ችግሮችን መፍታት ላይ ያተኮረ ሳይሆን ሙሉ ለሙሉ መለወጥ እንደሚያስፈልግ ነው" ሲሉ አጥብቀው ተናግረዋል።

የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መንፈስን ማደስ፡ የተለወጠች ቤተ ክርስቲያን

“የቤተ ክርስቲያን ዋና መርሕ የሆነው ‘ኅብረት’ እና ‘የእግዚአብሔር ህዝቦች’ ቀደም ሲል በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ተመስርቷል። ይህን መንፈስ ለማደስ ጊዜው አሁን ነው፣ ምክንያቱም ደግሞ ሁሉንም የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን፣ ቁምስናዎችን እና ሀገረ ስብከቶችን ወደ ንቁ ተሳታፊነት በመቀየር ድምፃቸው የሚሰማበት እና የሚከበርበት ማኅበረሰቦች እንዲሆኑ ለማድረግ ነው” ብለዋል ሊቀ ጳጳስ ፓኮ።

ከዚህም ባሻገር ይህ ለውጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለጋራ ውሳኔ ሰጪነት በአዲስ ቁርጠኝነት እንዲሠሩ በማድረግ አሁን ያሉ መዋቅሮችን ያድሳል ባማለትም አክለዋል።

ሊቀ ጳጳስ ፓኮ በመጨረሻም የሁለተኛውን የሲኖዶሱን ጉባኤ በጉጉት በመጠባበቅ ላይ እንዳሉ በመጥቀስ፥ ‘ኢንስትሩመንተስ ላቦሪስ’ በመባል የሚታወቀውን የመሰናዶ ሰነዱ ላይ ቀደም ብለው የተከናወኑ ሰፊ ምክክሮችን እና ሥራዎችን ጠቁመው፥ ይህ ውጤት ተኮር የሆነ አካሄድ ከመጀመሪያው ክፍል ጋር ሲነጻጸር ሁለተኛው ጉባኤ የበለጠ ውጤታማ የሆነ ጉባኤ ይሆናል ብለዋል።
 

28 June 2024, 13:31