ከመላው ታይላንድ ለሦስት ቀን ስብሰባ የተሰበሰቡ ወጣቶች ከመላው ታይላንድ ለሦስት ቀን ስብሰባ የተሰበሰቡ ወጣቶች  (Photo by MISSION POSSIBLE / LiCAS)

የታይላንድ ወጣቶች ሲኖዶሳዊነትን በ 3 ቀን ማህበራዊ 'hackathon' ወደ ህይወት ያመጣሉ!

የታይላንድ የካቶሊክ ትምህርት ምክር ቤት (ሲኢሲቲ) እና ሊሲኤኤስ በባንኮክ በሚገኘው ማተር ዴይ ትምህርት ቤት ለሦስት ቀናት የፈጀ የወጣቶች ማህበራዊ ‘ሃካቶን’ ለማድረግ በመላው ታይላንድ ከሚገኙ 12 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን ሰብስበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በእንግሊዘኛው “hackathon” (ሀካቶን በመባል የሚታወቀውና ከተለያዩ የአይቲ ሴክተሮች የተውጣጡ ባለሙያዎች በተለያየ አቅም የሚሳተፉበት፡ የሶፍትዌር ገንቢዎች፣ ፕሮግራመሮች እና ግራፊክ ዲዛይነሮች የሚሳተፉበት ክስተት ነው፣ ይህ ስብሰባ በአጠቃላይ ከአንድ ቀን እስከ አንድ ሳምንት መካከል የሚካሄድ ስብሰባ ነው፣ የተለያዩ ስራዎች፣ ትምህርታዊ እና ማህበራዊ ዓላማዎች ሊኖሩት ይችላል)።

እ.ኤ.አ ከሐምሌ 12 እስከ 14 ቀን 2024 ዓ.ም የተካሄደው ዝግጅቱ በሲኖዶስ ላይ በሲኖዶስ መነፅር የህብረተሰቡን አንገብጋቢ ፈተናዎች ለመፍታት የወጣቶችን አእምሮ ለማሳተፍ ያለመ ነው።

የሊሲኤኤስ ዋና ዳይሬክተር ፒተር ሞንትሄንቪቺንቻይ የዝግጅቱ አላማ “በወጣቶች መካከል ከሲኖዶስ ጋር ያለውን ግንዛቤ እና ግንኙነት ማሳደግ ነው” ብለዋል።

"ከሁሉም በላይ ደግሞ ሁላችንም ሲኖዶሳዊነትን የምንለማመድበት በተለይም አዋቂዎች እነዚህን ወጣቶች የምንሰማቸው እና የምናዳምጣቸው መሆናችንን የምናሳይበት አጋጣሚ ነው" ብሏል።

የእስያ ሲኖዶስ አህጉራዊ መድረክ ላይ ከተለዩት ዘጠኝ አበይት ጉዳዮች መካከል እድሜያቸው 13 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተሳታፊዎች እንዲወያዩ ተጋብዘዋል።

እህት ኒና በመጨረሻው የስብሰባው ቀን ለታዳጊ ወጣቶች ባደረጉት ንግግር “ከሃካቶን የእውነት የማዳመጥን አስፈላጊነት እንደተረዱት ተስፋ አደርጋለሁ” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን አክለውም "ማዳመጥ የሂደቱ አካል ብቻ ሳይሆን የመፍትሄውም አካል ሊሆን ይችላል። ሁላችሁም ልዩ ተልእኮ፣ በዚህ ዓለም አገልግሎት አላችሁ፣ እናም ተልእኮአችሁ ይቻላል” ሲሉ አክለው ተናግረዋል።

የሀካቶን መርሃ ግብሩ በተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ አማካሪዎች የአመራር ስልት አሰልጣኝ እና የአገሬው ተወላጅ የማህበረሰብ መሪን ጨምሮ እውቀታቸውን እና ልምዳቸውን ያካፈሉበት ተከታታይ አውደ ጥናቶች ተጀምሯል።

በዝግጅቱ ላይ አማካሪ የሆኑት ዶክተር ሳንቲ ላፕቤንጃኩል የተሳታፊዎችን አቅም አውስተዋል። “የልጆቹ ጥያቄዎች በጣም አስደነቀኝ… አልኳቸው፣ ሚኒስቴር ስትሆኑ ከአምስት እስከ ስድስት ዓመታት በኋላ እንደገና ወደ እኔ ኑ፣ በእርግጠኝነት እንደገና እንነጋገራለን” ብያቸው ነበር ሲሉ አውስተዋል።

የመጀመሪያው ቀን ተማሪዎችን በማነሳሳት እና ሃሳባቸውን ወደ እውነታ ለመቀየር አስፈላጊ መሳሪያዎችን በማስታጠቅ ላይ ያተኮረ ነበር።

17 July 2024, 15:50