የዓለም አቀፉ የበላይ ተቆጣጣሪዎች ህብረት በዓለም ዙሪያ የሃይማኖታዊ ሕይወት ምስረታን ያጠናክራል ተባለ
አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
ቤተክርስቲያን እና ዓለም በ21ኛው ክፍለ ዘመን ውስጥ ያለው የሃይማኖት ምስረታ ሁሉን አቀፍ አቀራረብ ያስፈልጋቸዋል ሲል የካቶሊክ ገዳማዊያት መሪዎች እናት ድርጅት የሆነው የዓለም አቀፉ የበላይ ተቆጣጣሪዎች ህብረት አስታውቋል።
በዓለም አቀፉ የበላይ ተቆጣጣሪዎች ህብረት (USIG) ገዳማዊያት እህቶችን ለምስረታ አገልግሎት የማዘጋጀት አስፈላጊነት ላይ ጠንክሮ መስራት ከጀመረ 6 ዓመታትን አስቆጥሯል።
የተቋሙ የምስረታ ፕሮግራም አስተባባሪ ሲስተር ሻሊኒ ሙላክካል ከቫቲካን ዜና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የምስረታ ስልጠና መርሃ ግብሩ በእንግሊዘኛ የቀረበ ሲሆን አሁን ያለውን ሃይማኖታዊ ሕይወት የሚዳስስም ነው ብለዋል።
ትምህርቱ በመጀመሪያ ደረጃ ምስረታ ላይ ሴቶችን አብሮ በመሆን ለማገዝ ሃላፊነት ለሚወስዱ እህቶች የተዘጋጀ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
መርሃ ግብሩ የምስረታ አገልግሎትን መሰረታዊ ነገሮች፣ የተቀደሰ ህይወት አውድ፣ መሃላዎችን ከተለያየ አቅጣጫ ማየት፣ በተለያዩ ባህሎች መካከል መኖር እና አገልግሎት፣ ራስን ማወቅ፣ ማስተዋል እና አመራርን ለማዳበር የፈጠራ ቅርጾች እና ሂደቶችን፣ ተልዕኮ እና ዓለም አቀፍ ስጋቶች የሚሉትን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን ይዳስሳል።
ሲስተር ሻሊኒ ከዚህም በተጨማሪ የምስረታ መርሃ ግብሩ እያንዳንዷ ገዳማዊ እህት ውስጣዊ ለውጥ እንድታገኝ ለማስቻል ተግቶ እንደሚሰራ ገልጸው፣ “በነዚህ ጊዜያት ውስጥ የሚማሩት ነገር ሁሉ በአደራ ለተሰጣቸው ሰዎች ጥሩ አጋር እንዲሆኑ እና በገንቢ ጉዟቸው አብረው እንዲሄዱ ይረዳቸዋል” ሲሉ ተናግረዋል።
ሲስተሯ አክለውም ተሳታፊዎች ፕሮግራሙን የሚያንጽ እና የሚያነቃቃ ብሎም የቡድን ስራን፣ መስተጋብርን፣ የግል እይታን እና ምክክርን የሚያበረታታ ነው ሲሉ ይገልፃሉ ብለዋል።
ፕሮግራሙ በመጨረሻም “ከተከበሩ ወዳጆቻችን ጋር በአመስጋኝነት ወደፊት አብረን እንጓዛለን” በሚል መሪ ቃል በሚዘጋጅ ስነስርዓት ይጠናቀቃል።
የጋራ ልምዶች እና ግንዛቤዎች
‘የቤተክርስትያን ሴት ልጆች’ ከሚል ማህበር ከህንድ የመጡት ሲስተር ቤና ፒተር የተባሉ አንድ ተሳታፊ እንደተናገሩት፥ ገዳማዊያን እህቶቹ እርስ በርስ በተለዋወጡት ልምድ ጥንካሬን ማግኘታቸውን ገልጸው፥ “ከተለያዩ ባህሎች እና ብሄረሰቦች ውስጥ መጥተን በ21ኛው ክፍለ ዘመን ህብረትን፣ ለውጥን እና አዲስ የምስረታ መንፈስን በጽኑ እንደሚፈልግ ገዳማዊያት አንድ ላይ መሰብሰብ አዳዲስ ትስስሮች እንዲፈጠሩ እና እንዲጠናከሩ የሚያስችል እድል ነው” በማለት ገልጸዋል።
ከቴክሳስ ግዛት፣ ሂዩስተን ከተማ ከሚገኘው ‘ሲስተርስ ኦፍ ቻሪቲ’ ማህበር የመጡት ሲስተር ጃዎ-ሁንግ ሲምፎኒ ንጎ፣ ፕሮግራሙ ከሌሎች የዓለም ክፍሎች ካሉ እህቶች ጋር እርስ በርስ መደጋገፍ፣ የባህል ትስስር፣ እና ጥልቅ ግንኙነት እንዲኖር አስችሏል” ብለዋል።
ሲስተር ጃዮ ሁንግ አክለውም በመርሃ ግብሩ ወቅት በተሰጡት በተለያዩ ኮርሶች በኩል ባደረጉት ጉዟቸው እጩዎችን ለማገዝ ባገኙት አዳዲስ ልምዶች እና ክህሎቶች ስለ አጠቃላይ ሃይማኖታዊ አደረጃጀት ሰፋ ያለ ግንዛቤ አግኝተናል ብለዋል።
እ.አ.አ. ከ2019 ዓ.ም. ጀምሮ ከ50 የሚበልጡ ጉባኤዎችና ሃገራት የተውጣጡ ከ250 የሚበልጡ ገዳማዊያት እህቶች በዚህ ፕሮግራም ተሳትፈዋል።