በኒካራጓ የሚገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን በኒካራጓ የሚገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን   (ANSA)

ኒካራጓ አብያተ ክርስቲያናት ከሚያገኙት መባ እና ምጿት ላይ ግብር ለማስከፈል መዘጋጀቷ ተገለጸ!

የኒካራጓ ፓርላማ የሁሉም ቤተ እምነቶች አብያተ ክርስቲያናት እና የሃይማኖት ድርጅቶች ከምእመናን በተቀበሉት መስዋዕቶች ላይ ግብር እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አዲስ የግብር አዋጅ እርምጃዎችን አጽድቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የኒካራጓ ብሔራዊ ምክር ቤት እ.አ.አ ነሐሴ 20 ቀን የተደረገውን የግብር ማሻሻያ አጽድቋል፥ ይህም ለሃይማኖት ተቋማት ከቀረጥ ነፃ የሚደረጉ ተግባራትን እና ንብረቶች ላይ የገቢ ግብር እንዲከፍሉ የሚጠይቅ ነው።

እንደ ገለልተኛ የኒካራጓ ሚዲያ ዘገባ፣ የሕግ ቁጥር 822 ማሻሻያ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት፣ ቤተ እምነት ምንም ይሁን ምን፣ ከግሉ ኢኮኖሚ ዘርፍ ጋር ተመሳሳይ የሆነ የግብር ሥርዓት እንዲከተሉ ይጠይቃል፣ ሕጋዊ ትርፍ የእንቅስቃሴ ግብ ነው።

ምጽዋት፣ ስጦታዎች እና የምእመናን ልገሳ ላይ ከ10 እስከ 30 በመቶ ባለው ዋጋ የገቢ ግብር ይጣልባቸዋል።

ከቀረጥ ነፃ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ማስቀረት በትምህርት፣ በማህበራዊ እና በእርዳታ ስራዎች ላይ በተሰማሩት የሀይማኖት ማህበረሰቦች የስራ እና የገንዘብ አቅም ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንደሚያሳድር እና በተለይም ለችግር ተጋላጭ በሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ከፍተኛ መዘዝ እንደሚያስከትል ተጠቁሟል።

ተሃድሶው ለካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና ለሌሎች የሃይማኖት እና የሲቪል ድርጅቶች አስቸጋሪ አውድ ውስጥ እንደሚከታቸው ተገልጿል።

የካህናቱ እስራትና መባረር ተከትሎ የኒካራጓ መንግሥት ንብረቶቻቸውን ለመንግሥት በማዛወር ሌሎች 1,500 መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ሕጋዊ እውቅና በቅርቡ ሰርዟል።

ይህን ውሳኔ በተመለከተ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በመግለጫው ላይ የኒካራጓ መንግስት የወሰደው እርምጃ “የእምነት ነፃነትን እና የመሰብሰብ ነፃነትን አደጋ ላይ የሚጥል ነው” በማለት በመግለጫው ላይ የገለጸ ሲሆን “በጥልቅ አሳስቦኛል” ሲል መግለጫው “የግለሰቦች መሠረታዊ ነፃነቶችን ማረጋገጥ እና መጠበቅ አለበት” ሲል ገልጿል።

23 August 2024, 15:37