አዛውንቱ ስምዖን ኢየሱስን በቤተ መቅደስ ተቀበል አዛውንቱ ስምዖን ኢየሱስን በቤተ መቅደስ ተቀበል 

ሰባቱ የማርያም ሐዘኖች

1. የስምሆን ትንቢት (ሉቃስ 2፡32-35)

"ወትቀውም ንግሥት በየማንክ በአልባስ ወርቅ ዑጽፍት ወኀብርት" (በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፍና ነግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች" (መዝ 45፡10) ይላል ነቢዩ ዳዊት።

እግዚአብሔር ያቺ ከሁሉም የበለጠች ፍጥረቱን እንደ ሁሉም ሰው በኃጢአት ቆሻሻ እንድትነካ ባይፈቅድም በምድር ለሚኖሩ ለሰው ልጅ ሁሉ ከሚደርሰበት ሐዘንና ስቃይ ነጻ እንድትሆን ግን አልፈቀደም። እንደ ማንኛውም ሰው እንድትሰቃይ ተዋት። እመቤታችን ማርያም ከሌሎች የበለጠ ሐዘን መከራና ስቃይ ተቀበለች። በስቃይ በኩል ከኢየሱስ ሌላ የሚበልጣት የለም። የቅዱሳን ሰማዕታት የከፋ መከራ እንኳ ከእመቤታችን ማርያም ጋር ሊወዳደር አይችልም። እርስዋ ከልጇ ከኢየሱስ ጋር በመሆን «እናንተ መንገድ የምታልፉ ሁሉ በእኔ ላይ እንደ ተደረገው የሚመስል መከራ እንዳለ ተመልከቱ» (ሰቆ. ኤር. 1፣12) እያለች ታሳስበናለች።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ሰለዚህ ቅዱሳን «ሰማዕተ ሰማዕታት፣ ንግሥተ ነግሥታት» እያሉ ይጠሯታል። የማርያም ሰማዕትነት ከሌሎች ሰማዕታት የሚበልጠው በሥጋዊ ስቃይ ሳይሆን በመንፈሳዊ በኩል እንደሆነም ይናገራሉ። ይህም ስቃይ እንደ አንድ የተሳለ ሰይፍ ልቧን ይሰንጥቀው እንደነበር ቅዱሳኖቹ ያውቃሉ። ቅዱስ በርናርዶስ «የማርያም ሰማዕትትነት ከብረት የጠነከረ ነው» ይላል። ኢየሱስ እንደ ተወለደ የእርሱ ስቃይ ወዲያው ጀመረ። የእርስዋም ስቃይ በዚያው ጀመረ። የልጇን ስቃይና ውርደት በማሰብ በመሰቃየት ልቧ በሐዘን ይወጋ ነበር። ቅዱስ አልበርቶ «የጽዮን ልጅ ድንግል ሆይ የሐዘንሽን ጥልቀትና ስፋት እንደ ባሕር ነው” (ሰቆ. ኤር. 2፣12) የሚለውን የሰቆቃው ኤርምያስን ጥቅስ ለእመቤታችን ማርያም ይደግመዋል። እመቤታችን ማርያም ይህ ሁሉ ሐዘን የደረሰባት በእርስዋ ላይ በተፈጸመው ስቃይ ሳይሆን በኋላ በልጇ ላይ ስለሚደርሰው መከራ በማሰብ ነበር።

እንግዲህ ሐዘኗን ብቻ ከሚያስተነትኑ አፍቃሪዎች ጋር በመሆን እነዚህን ሰባት ነጥቦች ቀስ ብለን እናስብ፣

1.    የስምሆን ትንቢት (ሉቃስ 2፡32-35)

በዚያን ጊዜ ጻድቅና ትጉህ የሆነ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው በኢየሩሳሌም ይኖር ነበር፤ እርሱም የእስራኤልን መጽናናት የሚጠባበቅና መንፈስ ቅዱስ በላዩ ያደረ ሰው ነበር። ደግሞም የጌታን መሲሕ ሳያይ እንደማይሞት በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ነበር፤ እርሱም በዚህ ጊዜ በመንፈስ ተመርቶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ የልጁም ወላጆች በሕጉ ልማድ መሠረት ተገቢውን ሊፈጽሙለት ሕፃኑን ኢየሱስን ይዘው በገቡ ጊዜ፣ ስምዖን ተቀብሎ አቀፈው፤ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እንዲህ አለ፤ “ጌታ ሆይ፤ ቃል በገባኸው መሠረት፣ አሁን ባሪያህን በሰላም አሰናብተው፤

ዐይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን፣ ማዳንህን አይተዋልና። ይህም ለአሕዛብ መገለጥን የሚሰጥ ብርሃን፣

ለሕዝብህ ለእስራኤልም ክብር ነው።” አባቱና እናቱም ስለ እርሱ በተነገረው ነገር ተገረሙ። ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፤ “ይህ ሕፃን በእስራኤል ለብዙዎች መነሣትና መውደቅ ምክንያት እንዲሆን፣ ደግሞም ክፉ ለሚያስወሩበት ምልክት እንዲሆን ተወስኗል፤ የብዙዎችም የልብ ሐሳብ የተገለጠ እንዲሆን፣ የአንቺም ነፍስ ደግሞ በሰይፍ ይወጋል።”

አስተንትኖ

ዮሴፍ እና ማርያም ኢየሱስን ወደ ቤተመቅደስ ሲወስዱ፣ ስምዖን የሚባል አንድ እንግዳ ሰው ልጃቸውን ወሰደ፣ እግዚአብሔርን ስለ እርሱ አመሰገነ፣ እና አሁን ለመሞት መዘጋጀቱን አስታውቋል፣ ምክንያቱም በመጨረሻ እሱ አዳኝ የሚሆነውን መሲህ ስላየ ነው። አይሁዶችና አህዛብም እንዲሁ። ዮሴፍና ማርያም ይህ ሰው በተናገረው ነገር “ተደነቁ” (በእንዲህ ያለ እንግዳ ገጠመኝ የማይደነቅ ማን ነው?) ስምዖን ባረካቸው።

እስካሁን ድረስ ግንኙነቱ ያልተለመደ ነው ፣ ግን ምናልባት በጣም አስደሳች ነው። ነገር ግን ስምዖን በተለይ ትኩረቱን ወደ ማርያም አዞረና ....

·      ልጅዋ “በእስራኤል ለብዙዎች ውድቀትና መነሣት” የግጭት ምልክት እንደሚሆን

·      እሷ ራሷ ሰይፍ ሲወጋት ነፍሷ እንዴት እንደሚሰቃይ ነግሮታል። ይህ ምናልባት ማርያም በሕማማት ውስጥ የምትጫወተው ሚና በጣም ግልፅ ምሳሌ ነው፡ ትንቢቱ ከክርስቶስ ጎን እንደምትሠቃይ፣ መከራዋ ግን መንፈሳዊ እንደሚሆን ነው። ሰውነቱ በጦር ሲወጋ ነፍሷም እንዲሁ። እናም የስምዖን ትንቢት እራሱ የማርያም ሀዘን የመጀመሪያው ነው - ይህ እንግዳ እና አስፈሪ የሆነው ነገር ለወጣት እናት ፣ በልጇ ላይ አንድ አስከፊ ነገር ሊደርስበት ነው እያለች እንድትሰጋ አድርጓታል።

ሁለተኛው የማርያም ሐዘን ይቀጥላል ...

 

08 August 2024, 09:15