ክርስቶስ ሕያው ነው! ተስፋችን ነው
ወጣት ልጆች የፍቅርን ጥሪ በደንብ ይሰሙታል; ቤተሰብ መሥርተው በጋራ ሕይወትን ለመምራት የሚችሉበትን ትክክለኛ ሰው ለማግኘት ያልማሉ” ያለ ምንም ጥርጥር" ይህ እግዚአብሔር ራሱ በስሜታቸው" በመሻታቸው እና በሕልማቸው አማካኝነት እንዲያውቁት የሚያደርገው ጥሪ ነው” ይህንን ጭብጥ በሙላት የቤተ ሰብ ፍቅር ሐዋርያዊ ምክር ውስጥ አብራርቻለሁ” ሁሉም የወጣት ሕብረተሰብ ክፍል እንዲያነብበው በተለይም ዐራተኛውንና አምስተኛውን ምዕራፍ እንዲያተኩርበት አበረታታለሁ”።
“ሁለት ለመጋባት ያሰቡ ክርሰትያኖች በራሳቸው የፍቅር ታሪክ ውስጥ የጌታን ጥሪ " ከሁለቱ" ወንድና ሴት" አንድ ሥጋና አንድ ሕይወት እንዲኖራቸው የሚለውን ጥሪ ተገንዝበዋል” የቅዱስ ጋብቻ ምስጢር ይህንን በእግዚአብሔር ጸጋ ውስጥ ያለ ፍቅር ይጠቀልላል; በእራሱ በእግዚአብሔር ውስጥ ሥሩን ያደርጋል” በዚህ ስጦታ" በዚህ ጥሪ እርግጠኛነት" በመተማመን ወደፊት መራመድ ትችላላችሁ" ምንም ሥጋት አይኖርባችሁም" ሁሉንም በጋራ ትወጡታላችሁ!”” ብዬ ማሰብ እወዳለሁ”።
እዚህ ጋ ልናስታውስ የሚያስፈልገን ነገር እግዚአብሔር ሲፈጥረን ሁላችንም ለጾታዊ ግንኙነት ስሜት ያለን ሰዎች አድርጎ እንደፈጠረን ነው” “ለሰዎች ድንቅ ስጦታን ለመስጠት ሲል ስሜቱንም የፈጠረው እርሱ ራሱ ነው””። በጋብቻ ጥሪ ውስጥ “የጾታዊ ግንኙነትን ስሜት" ግንኙነቱንም የእግዚአብሔር ስጦታ ስለ መሆኑ እውቅና ልንሰጥ እና ልናደንቅ ይገባናል” ነውር አይደለም” የእግዚአብሔር ስጦታ ነው" ጌታ የሰጠን ነው” ሁለት ዓላማዎችም አሉት - ለማፍቀርና አዲስ ሕይወት እንዲቀጥል ማድረግ” የሚያስደስት ነው" የሚያስደስት ፍቅር” እውነተኛ ፍቅር አስደሳች ነው” በወንድና በሴት መኻከል ያለ ፍቅር" አስደሳች ከሆነ ሁልጊዜም ቢሆን ሕይወት ወደመስጠት ያመራል” ሁልጊዜም” በነፍስና በሥጋ ሕይወት መስጠት””።
ሲኖዱ አጥብቆ እንደተናገረው" “ለወጣቱ ሕብረተሰብ" ቤተሰብ ዋነኛ የማጠቃሻ ነጥብ መሆኑ ይቀጥላል” ሕጻናት የወላጆቻቸውን ፍቅርና እንክብካቤ ያደንቃሉ" ስለ ቤተሰብ ትስስር ቦታ ይሰጣሉ" የእነርሱ ጊዜም በደረሰ ጊዜ ቤተሰብ መመሥረት እንደሚሳካላቸው ተስፋ ያደርጋሉ” ያለ ምንም ጥርጥር" የጥንዶች መለያየት" መፋታት" ሁለተኛ ጋበቻ እና ልጆችን ለብቻ የማሳደግ ሁኔታ ትልቅ ሥቃይና የማንነት ቀውስን በልጆች ላይ ይፈጥራል” አንዳንድ ጊዜ ለዕድሜያቸው የማይመጥን ኀላፊነትን ሊሸከሙ ስለሚገደዱ ያለ ጊዜያቸው ጎልማሶች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል” አብዛኛውን ጊዜ" አያቶች የግድ የፍቅርና የሃይማኖት ትምህርት እገዛ ያደርጋሉ - ከጥበባቸው ጋር በትውልድ መኻከል ዋነኛ አያያዥ ናቸው”።
በራሳቸው ቤተሰብ ውስጥ ያጋጠሟቸው ችገሮች ብዙዎችን ወጣቶች" 'ትዳር መመሥረት" ታማኝ መሆን" ለጋሥ መሆን ይገባል ወይ?' የሚሉ ጥያቄዎችን እንዲያነሡ ማድረጉ እውን ነው” ቤተሰብ ላይ ለመሥራት ሁሉንም ጥረታችሁን ብታፈስሱ የሚገባ ነገር ነው" በዚያ ለመብሰል የሚረዷቸሁ እጅግ በጣም የተሻሉ ማበረታቻዎች እና የምትጋሩት ደስታ አለ” ታላቅ ፍቅርን አትዘረፉ” ሊቆጣጠሩት በማይችሉ የግለኝነትን ሕይወት ሐሳብ በሚያቀርቡ ሰዎች ውትወታ ከመንገድ አትውጡ ምክንያቱም በመጨረሻው ይህ አስተሳሰብ ወደ ራስን የማግለልና አስከፊ ብቸኝነት የሚመራ ነው” ።
ዛሬ" 'ለጊዜው' የሚል ባሕል የበላይ የሆነበት ነው" ነገር ግን ቅዠት ነው” ምንም ነገር ፍጹም መሆን አይችልም ብሎ መናገር ሐሰት ነው” “ዛሬ" ጋብቻ ጊዜ ያለፈበት ነገር ነው የሚሉ ሰዎች አሉ" ብዙዎች የአሁኑን የጊዜውን ብቻ መደሰት ነው እያሉ ይሰብካሉ” የሕይወት ዘመን ቃል መግባት የሚገባው ነገር አይደለም ይላሉ” እኔ ግን እንደዚያ ከሚሆን ለውጥ ፈላጊዎች ሁኑ እላችኋለሁ" ከወዠቡ በተቃራኒው አቅጣጫ ዋኙ" አዎን" ነገሮችን ሁሉ ጊዜያዊ አድርጎ የሚያይን በመጨረሻም እናንተ ኀላፊነትን መውሰድ የማትችሉ" እውነተኛ ፍቅርን ማፍቀር እንደማትችሉ በሚያሳምናችሁ በዚህ ባሕል ላይ አምጹ እያልኳችሁ ነው”” በእናንተ ላይ ትልቅ መተማመን አለኝ" በዚህም ምክንያት" ጋብቻን እንድትመርጡ እላችኋለሁ” ።
ጋብቻ ዝግጅት ይጠይቃል" ይህ ደግሞ ራስን በማወቅ ማደግን" የሚበልጡ መልካምነቶችን ማሳደግን" በተለይም ደግሞ ፍቅር" ትዕግሥት" ለንግግር ክፍት መሆንን" እና ሌሎችን መርዳትን ያካትታል” ሌላውን ወገን መጠቀሚያ ከማድረግ ይልቅ የራስን የጾታዊ ግንኙነት ስሜት ማሳደግ ራስን ሙሉ ለሙሉ ለሌላው በአግባቡ መስጠትንም ይጨምራል”።
የኮሎምቢያ ጳጳሳት እንዳስተማሩት" “ክርስቶስ" የትዳር አጋሮች ፍጹም እንዳልሆኑ" ፍቅራቸው እንዲያድግና እንዲቻቻሉ" ድካሞቻቸውንና ታማኝነትን ማጉደላቸውን ማሸነፍ እንደሚኖርባቸው ያውቃል” በዚህም ምክንያት"እንደ እግዚአብሔር እቅድ የሆነውን ትክክለኛ የሆነው ትዳር እንዲይዙ የሚያደርግ ብርሃንና ጥንካሬ" ለትዳር አጋሮች ጸጋውን ይሰጣል””።
ለትዳር ወይም ለቅድስና ሕይወት ላልተጠሩ ሰዎች" ሁልጊዜም ቢሆን ሊታወስ የሚገባው ዋነኛና አስፈላጊ የሆነው ጥሪ በጥምቀት የተጠራነው ጥሪ መሆኑን ነው” ያላገቡ" በራሳቸውም ምርጫ እንኳን ባይሆን እንኳን ያላገቡት" ለዚያ ጥሪ ራሳቸው ያደጉበትን መንገድ መመሰከር ይችላሉ” ።
ምንጭ፡ ክርስቶስ ሕያው ነው በሚል አርእስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለወጣቶች እና ለጠቅላላው የእግዚአብሔር ሕዝብ ከጻፉት ድኅረ ሲኖዶሳዊ ሐዋርያዊ ምክር ከአንቀጽ 260-268 ላይ የተወሰደ።
የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ዳንኤል ኃይሌ