ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትት ፍራንቸስኮስ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ ባደረጉበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትት ፍራንቸስኮስ በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ ባደረጉበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በእዚህ አስቸጋሪ ወቅት አንዳችን ለአንዳችን ቅርብ መሆን እንችል ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጠን እንጠይቅ አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጋቢት 09/2020 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የተገለጸ ሲሆን በኮሮና ቫይረስ ለተጠቁ ሰዎች የሕክምና እርዳታ በማደረግ ላይ የነበሩ የሕክምና ባለሙያዎች ራሳቸው በበሽታው ተጠቅተው ሕይወታቸው ማለፉ እጅግ በጣም እንዳሳዘናቸው ቅዱስነታቸው በመስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት የገለጹ ሲሆን “ህይወታቸውን ለታመሙ ሰዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ ያዋሉ” ለእነዚህ የሕክምና ባለሙያ ለነበሩ ሰዎች በመስዋዕተ ቅዳሴው ወቅት ጸሎት ማድረጋቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ሀ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“በቫይረሱ ​​ምክንያት ለሞቱት ሰዎች ዛሬ እንፀልያለን” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የመስዋዕተ ቅዳሴ ሥሥርዓት መጀመራቸው የተገለጸ ሲሆን  በመቀጠልም “ህይወታቸውን ለታመሙ ሰዎች አገልግሎት የሰጡ የጤና ባለሙያዎች” መጸለያችንን ልንቀጥል የገባል ብለዋል።

በእለቱ ከኦሪት ጸዘዐት 4፡5-9 ላይ ተወስዶ በተነበበው የመጀመሪያው ምንባብ ላይ እና እንዲሁም ከማቴዎስ ወንጌል 5፡17-19 ላይ ተወስዶ በተነበበው የእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ትኩረቱን ያደርገ ሲሆን ጭብጡም በሁለቱ ምንባባት ውስጥ የተጠቀሰው በሕግ ዙሪያ ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ ተገልጹዋል።

እግዚአብሔር ህጉን የሰጠበት መንገድ

ሁለቱም ምንባባት በሕጉ ላይ ያተኮሩ ነበሩ፣ በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  “እግዚአብሔር የሰጠንን ህግ ኢየሱስ ወደ ፍፁምነት ሊለውጠው እንደ መጣ” የገለጹ ሲሆን  የሊቀ ጳጳሳቱን ትኩረት የሳበው “እግዚአብሔር ህጉን የሰጠበት መንገድ” እንደ ነበረም ተገልጹዋል።  በእርግጥ ሙሴ እግዚአብሔር ምን ያህል ቅርብ እንደሆነ እና ማንም እሱን በጠራ ቁጥር  አምላካችን እግዚአብሔር ቅርብ መሆኑ ሙሴን ያስደንቀው እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው አስታውሰዋል።

እግዚአብሔር ለሕዝቡ ሕግጋቱን የሚሰጠው ሕዝቡን ቀርቦ ነው። እርሱ ሕግጋቶቻቸውን በሕዝቡ ላይ ጭነው ራሳቸው ከሕዝቡ የሚያርቁ አምባገነን ገዢዎች ዓይነት አይደለም። እናም እርሱ ሕጉን ለሕዝቡ የሚሰጠው ከህዝቡ ጋር አብሮ እንደ ሚሄድ አንድ አባት ሕዝቡን በመቅረብ እንደ ነበረ እናውቃለን። እርሱ ለሕዝቡ ቅርብ የሆነ አምላክ እንደ ሆነም እናውቃለን።

እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ይራመዳል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስብከታቸውን በመቀጠል ሕዝቡ በበረሃ እና በእሳት ዓምድ ውስጥ በሚጓዙበት ወቅት እግዚአብሔር ሕዝቡን ይጠብቅ እንደነበረ ተናግረዋል፣ እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር ይጓዛል ብለዋል ፡፡

ሕግጋቱን በመጸሐፍ ላይ ከትቦ ለሕዝቡ ከሰጠ በኋላ ሕዝቡን ጥሎ የሚሄድ  አምላክ አይደለም። ሕግጋቱን በዐለቱ ላይ በገዛ እጁ ይጽፋል። ከዚያም ለሕዝቡ በሙሴ አማካይነት ይሰጣቸዋል። ሕጉን ለሕዝቡ ሰጥቶ ከእዚያን በኋላ ሕዝቡን ጥሎ የሚሄድ አምላክ ግን አልነበረም።

እግዚአብሄር እኛን ሲቀርበን እኛ እንሸሸጋለን

ቀጥሎም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ ገጾች ላይ የሚታዩትን ዝንባሌዎች የሰው ልጆች እንደ ሚያንጸባርቁ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉ ሲሆን እግዚአብሔር እኛን የበለጠ እየቀረበ በመጣ መጠን እኛ ደግሞ በተቃራኒው ራሳችንን ከእርሱ የማራቅ ዝንባሌ አለን ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን ከእርሱ የመሸሻ የመጀመሪያ መንገድ እራሳችንን መደበቅ ነው ፣ ሁለተኛው መንገድ ደግሞ ቃየን እንዳደረገው ሌሎችን መግደል ነው ብለዋል።

ኃጢያት እርሱን እንድንቀርብ ሳይሆን ከእርሱ እራሳችንን እንድንደበቅ ያደርገናል። ብዙን ጊዜ እርሱ ፈራጅ ዳኛ ነው ብለን እናስባለን። ስለዚህ ይህንን ስለምፈራ እራሴን ደብቄ ኖራለሁ ብለንን እናስባለን። እያንዳንዱን ቅርበት የሚያግዱ ሁለት ዓይነት ግብረመልሶች አሉ። ሰው የእግዚአብሔርን ቅርበት ይክዳል፡፡ የሰው ልጅ ግንኙነቶችን መቆጣጠር ይፈልጋል። ግንኙነቶች ሁል ጊዜ አንድ ዓይነት ተጋላጭነትን ይዘው ይመጣሉ። እግዚአብሄር ራሱን ወደ እኛ የሚያቀርበው ደካም መስሎ ነው። ወደ እኛ እጅግ በጣም እየቀረበ በመጣ ቁጥር እጅግ እየደከመ የመጣ ይመስላል። በመካከላችን ለመኖር ሲመጣ ራሱን እጅግ ደካም በማድረግ እንደ አንድ ሰው ሆኖ ተገልጹዋል። ያንን ድክመት እስከ ሞት ድረስ በጣም ጭካኔ የተሞላው ሞት ድረስ እንዲሄድ አድርጎታል።

ትህትና

“እግዚአብሔር ለእኛ ቅርብ መሆኑ ትህትናውን ያሳያል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ለመሄድ እና እኛን ለመርዳት ራሱን አዋርዱዋል” ብለዋል። ሙሴ እንደተናገረው እርሱ በሰማይ ውስጥ በአንድ ቦታ የሚገኝ አንድ አምላክ አይደለም፣ ይህንንም ኢየሱስ አሳይቶናል፣ ኢየሱስ ከሰዎች ጋር፣ ከደቀመዛሙርቱ ጋር በመጓዝ አስተምሩዋል፣ በፍቅር እርማት ሰጥቱዋቸዋል በማለት ብስከታቸውን የቀተሉት ቅዱስነታቸው አንዳችን ከአንዳችን ከመራቃ ይልቅ በተቃራኒው አንዳችን ለአንዳችን ቅርብ በመሆን በጋራ መጓዝ እንዳለብን ኢየሱስ ይጠይቀናል ብለዋል።

ቅርበትን የምንፈጥርበት መንገዶች

ሰዎችን በተለያዩ መንገዶች ልንቀርባቸው እንችላለን በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ከእነዚህ ሰዎችን መቅረብ ከሚያስችሉን መንገዶች መካከል አሁን “እኛ ባለንበት በእዚህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በዚህ ቀውስ ውስጥ ይህ ቅርበት ይበልጡኑ እንዲገለጥ ይፈለጋል፣ ምናልባት በሽታው እንዳይዛመት በማሰብ ወደ ሰዎች በአካል መቅረብ አንችል ይሆናል፣ ነገር ግን በጸሎት በማገዝ ለሰዎች ቅርብ የመሆን ባሕል ልናዳብር ይገባል፣ እነዚህን የመሳሰሉ ሰዎችን በመንፈስ እንድንቀርብ የሚያደርጉ ብዙ መንገዶች አሉ” ብለዋል።

እግዚአብሔር ቅርብ ነው

አንዳችን ለሌላው ቅርብ የምንሆንበት ምክንያት እግዚአብሔር ራሱን ለእኛ ቅርብ ስላደረገ ነው። “ከጌታ የተቀበልነው ርስት” የጉርብትና ርስት ነው ፣ እኛ ተነጣጥለን የምንኖር ሰዎች አይደለንም በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “አንዳችን ከሌላው ራሳችንን በመደበቅ እንደ ቃየን እጃችንን ለመታጠብ ሳይሆን አንዳችን ለሌላው ቅርብ መሆን እንችል ዘንድ ጸጋውን እንዲሰጠን ጌታን ልንማጸነው ይገባል” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው የእለቱን ስብከት አጠናቀዋል።

ይህንን ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!
18 March 2020, 15:57
ሁሉንም ያንብቡ >