ር. ሊ. ጳ. ፍራንቺስኮስ በሊቷዋኒያ ዋና ከተማ በቪልኒዩስ ተገኝተው ለባለስልጣናት ንግግር አደረጉ።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ ግርማቸው ተስፋዬ - ቫቲካን
ዛሬ ማለትም ዕለተ ቅዳሜ መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም. እ.አ.አ. ር.ሊ.ጳ. ፍራንቼስኮስ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸውን ለማድረግ በሊቷዋኒያ ዋና ከተማ በቪልኒዩስ ተገኝተው ለባለስልጣናት፣ ለሲቪል ማህበረሰብ እና የተለያዩ ሃገራትን ለሚወክሉ ኣምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በርዕሰ ብሔሩ ቤተ መንግስት ውስጥ ያደረጉትን የመጀመሪያ ንግግራቸውን ሙሉ ይዘት ትርጉም እንደሚከተለው ቀርቧል።
“የተከበሩ የኣገሪቱ ርዕሰ ብሔር የተከበራችሁ ከፍተኛ የመንግስት ባላሥልጣናት እና የዲፕሎማሲ አካላት አባላት የሲቪል ማህበረሰብ ተወካዮች እንዲሁም ክቡራንና ክቡራት እንግዶች ይህንን ሓዋርያዊ ጉብኝት በባልቲክ ከሚካለሉት ሃገሮች ውስጠ በሊቷአኒኣ መጀመሩ በእርግጥ የደስታ እና የተስፋ ምንጭ ነው። የዛሬ 25 ዓመት ዛሬ በተሰበሰብንበት በዚህ በቪልኒዩስ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በመከረም 4 ቀን 1993 ዓ.ም. እ.አ.አ. እጅግ ጥልቅ የሆነ ዝምተኛው ምሥክርነት ለሃይማኖት ነፃነት ብለው የተናገሩትን ቃል ኣስታውሳለው።
ክቡር ርዕሰ ብሔር ሆይ በእርሶና እና በሕዝቦት ሥም ላደረጋችሁልኝ ሞቅ ያለ አቀባበል እጅግ ኣድርጌ አመሰግናችኋለሁ። ዛሬ በእርሶ መልካም ፈቅድ የሃገሩንና የቤታቸውን በር የከፈቱልኝን ሁሉንም የሊቱዋኒያ ነዋሪዎች ሰላም ለማለት እወዳለሁ ኣንዲሁም ለእያንዳንዳችሁ ፍቅሬ እና ምስጋናዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ።
ይህ ሓዋርያዊ ጉብኝት ሀገሪቱ 100ኛ ዓመት የነጻነት በዓሏን የምታከብርበት ወቅት መሆኑ ይህንን ጉብኝት ታሪካዊ ያደርገዋል ለሊቷአኒኣም ሕዝብ መልካም ኣጋጣሚ ነው።
ለአንድ መቶ ዓመት ወይም ለአንድ ክፍለ ዘመን ብዙ ፈተናዎች እና መከራዎችን እስር ግፍ የተለያዩ ዓይነት ሰማዕትነት ጭምር ኣሳልፋችኃል። መቶኛ ዓመት የነፃነት በዓል ማክበር ማለት ትንሽ አረፍ ብሎ ከዚህ በፊት በሕዝቡ እና በሃገሪቱ ላይ የነበረዉን ኣስከፊና ኣስጨናቂ እንዲሁም ከባድ የነበረውን የሕይወት ልምድ በማስታወስ በኣሁኑ ጊዜ ካለዉ የኑሮና የሕይወት ዉጣ ዉረድ ጋር በማያያዝ ለወደፊት ሁሉንም ሰው በማካተት ለሕዝቦች ነፃነትና እኩልነት በጋር የሚሰራበትን መድረክ ለመፍጠር የሚያስችላችሁን ቁልፍ ባእጃችሁ ማያዝ ማለት ነው።
እያንዳንዱ ትውልድ ቀደም ሲል ስላለፈው የኣባቶቹ ትግል እና ስኬቶች በባለቤትነት እንዲይዝና እና በአሁኑ ጊዜ ደግሞ ይህንን የኣባቶቹን መታሰቢያ ለማክበር ተጠርቷል። ነገ ምን እንደሚከሰት ምን እንደሚመጣ ምን እንደሚገጥመን አናውቅም የምናውቀው ነገር ቢኖር እያንዳንዱ ጊዜ በጊዜው ያለዉን የትኛውንም ዓይነት ስቃይና ሥርዐት ኣልበኝነትን ወደ ፍትሓዊነትና መልካም ፍሬ ለማፍራት ወይም ውጤታማነትን ለመጨመር የሚያስችለንን ሕልውናን በሚገባ መንከባከብ ነው።ይህ ሕዝብ በማንኛውንም መልኩ የሚመጡትን ተግዳሮቶች ሁሉ እንዲቋቋምና ገንቢ ሕብረተሰብ እንዲሆን የሚያስችላቸው ጠንካራ ህልውና አለው።
የሃገራችሁ ብሔራዊ መዝሙር ልጆችሽ ኣሁንን ለመመልከትና በወኔ ለመንቀሳቀስ ካለፈው ታሪክ ኃይልን ያገኛሉ ካለፈው ታሪክ ብርታትን ያገኛሉ የሚል ስንኝ ተካቶበታል።
ሊቱዌኒያ ባሳለፈችው የታሪክ ዘመናት በሙሉ የተለያየ ዘር እና ሃይማኖት ያላቸውን ሕዝቦች ተቀብላ ኣስተናግዳለች። ሁሉም በእዚች ሃገር ውስጥ የሚኖሩበትን ቦታ አግኝተዋል የሊቱዋኒያን የታርታር የፖላንድ የሩሲያውያን የቤሎሩስያን የዩክሬን አርመናውያን ጀርመናውያን የመሳሰሉት ሁሉ .... እንዲሁም ካቶሊኮች ኦርቶዶክሶች ፕሮቴስታንቶች ሙስሊሞች አይሁዶች ሁሉ አምባገነናዊ ጽንሰ ሀሳብ መጥቶ ህገወጥነትንና ልዩነቶችን እስካሰፈነበት ጊዜ ድረስ ሁሉም ሕዝቦችና ብሔሮች እንዲሁም ሃይማኖቶች በሠላምና በፍቅር በአንድነት ኖረዋል።
ካለፈ ታሪክ ጥንካሬን መውሰድ ማለት ከዚህ በፊት የተበላሸዉን ወሠረት በማስተካከል ሁል ጊዜ ትክክልና ኣስፈላጊ የሆነውን የእድገትን ኣቅጣጫ በመያዝ እንደ መቻቻል እንደ እንግዳ ተቀባይነት መከባበር እና በአንድነት መኖር የሚሉትን ለአንድ ሃገር ዕድገት የሚበጁትን እሴቶች ማዳበር ማለት ነው። የምንኖርባትን ዓለም ገፅታ በምንመለከትበት ጊዜ የመለያየትና የግጭትን እንዲሁም የጦርነትና ያለመረጋጋትን ድምጽ በየጊዜው የሚዘሩ ወይም ደግሞ የዓለምን ሁኔታ ለማረጋጋትና የዓለምን ድኅንነት ለመጠበቅ እንዲሁም የተለያዩ ባሕሎችንና መልካም እሴቶችን ጠብቆ ለማቆየት ብቸኛው መንገድ የሌላውን ሕዝብ ማንነትና ባሕል ማስወገድ ወይም መሰረዝ ወይም ማጥፋት ነው የሚል ሓሳብ ያላቸው አይጠፉም።
እናንተ ሊቷአኒአን ልዩነቶችን ለማስተናገድ መቻቻል የሚል መልካም ኣባባል ኣላችሁ። በግልጽነት በሚደረግ ውይይት በመግባባት እና በመቻቻል በምስራቅ እና በምዕራብ በአውሮፓ መካከል ድልድይ መሆን ይቻላል። ይህ ደግሞ ለዓለም አቀፉ ህብረተሰብ እና በተለይም ለአውሮፓ ህብረት የምታበረክቷቸው የጎለበተና በሳል የሆነ ታሪክ ውጤት ሊሆን ይችላል። እናንተ በተጨባጭ በራሳችሁ ሕይወት ላይ ባላችሁ ተሞክሮ ይህ የጥቂቶች የበላይነት ወይም ጥቅም ከብዙኃኑ ጉዳት ጋር ስለማይነፃፀር ወይም ለጋራ ብልፅግና እንቅፋት ስለሚሆን ከውስጣችሁ ነቅላችሁ ኣውጥታችሁታል።
ይህንንም ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክ 16ኛ ፍቅርና እውነት በሚለው ሓርያዊ መልዕክታቸው ቁጥር 7 ላይ ይህንን ሓሳብ በሚገባ አስቀምጠውታል። እንዲህም ይላሉ ር.ሊ.ጳ. ቤኔዲክ 16ኛ በዚሁ ጽሁፋቸው የጋር ዕድገትና ብልፅግናን መሻት እንዲሁም እሱን ተግባራዊ ለማድረግ አጥብቆ መሥራት ፍትህን ፍቅርንና ሰላምን ለማስፈን ወሳኝ ናቸው። ለጋራ ብልፅግና አጥብቆ በመሥራትና ለተቸገሩ ሁሉ በችግራቸው ፈጥኖ በመድረስ ወንድም እህቶቻችንን ውጤታማ በሆነ መልኩ ማፍቀራችንን ማረጋገጥ ይቻላል።
በየትም ቦታ በሚፈጠሩት ግጭቶች ሁሉ ለሰዎች በተለይም ለደካማው ህዝብ በሚሰጡት ተጨባጭ ትኩረቶች ላይ በመመስረት እና ለሰዎች ሁሉ ጥቅም የሚያመጣውን ታላቅ መልካምነት ለማስፋፋት መጠራታችንን በመረዳት ዘላቂ መፍትሄ ማምጣት ይቻላል። ኢቫንጀሊኡም ጋውዲኡም 235። ከዚህ አንጻር ካለፈው ሕይወት ጥንካሬና ጉለበት መሰነቅ ማለት ለወደፊቶቹ ሳይሆን ለኣሁኑ ወቅት በሃገሪቱ ላይ ላሉ ወጣቶች ልዩ የሆነ ትኩረት ማዋስ ማለት ነው። ለማደግ እና ለመስራት እድል ያገኙ ወጣቶች ያሉበት ኅብረተሰብሰ ይህ ነገር
ወጣቶቹን ይበልጥ ለማህበራዊና ህብረተሰብአዊ ዕድገት የሚያነሳሳ ነገር በመሆኑ በአጠቃላይ ህብረተሰቡ በሙሉ በግንባታው ረገድ ተዋንያን እንዲሆንና ለወደፊት መልካም ተስፋ እንዲሰንቅ ያስችለዋል።
የሊቷኒአን ዜጎች ሃገሪቱ በተለይም በብዙ ረገድ የወጣቶችን ተሳትፎ የሚደግፈዉን ርዕዮተ ዓለም በቋሚነት ትደግፋለች ታበረታታለችም። ይህም ይህ ሕዝብ ሰዎችን ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ እስከሆነ ድረስ ያለምንም ጥርጣሬ እጅግ ተስፋ ሰጪ ጉዳይ ነው። እንግዳን ተቀብሎ ማስተናገድ ወጣቶችን በእንግድነት መቀበል አረጋውያንን በእንግድነት መቀበል ድሆችን በእንግድነት መቀበል በመጨረሻም የወደፊቱን ሁሉ በእንግድነት መቀበል ተስፋን የሚዘራ ጉዳይ ነው።
ክቡር የሃገሪቱ ርእሰ ብሔር ሆይ እንደከዚህ ቀደሙ ኣሁንም ቢሆን የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሊቷኒአ መንግሥት እና ሕዝብ ያቀዱት የተስፋና የኣንድነት ድልድይ ተግባራዊነቱ ኣስከሚረጋገጥ ድረስ ከጎናችሁ ትቆማለች”።