ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ ከመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት በኋላ ያስተላለፉት መልእክት

ከመልኣከ እግዚኣብሔር ጸሎት በኋላ
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥቅምት 18/2011 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበስቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች በእለቱ በተጠናቀቀው 15ኛ አጠቅላይ መደበኛ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የብጹዕን ጳጳሳት ሲኖዶስ መጠናቀቁን በማስመልከት ካስተላለፉት መልእክት በመቀጠል እንደ ተለመደው ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 17/2011 ዓ.ም በአሜሪካ ፒቴስቡርግ ተብሎ በሚጠረው ሥፍራ በነበረው የአይሁዶች የመሰብሰቢያ ማዕከል በአንድ ታጣቂ በደረሰው የመሳሪያ ጥቃት ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች ማዘናቸውን መግለጻቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ሁሉን የሚችል እግዚኣብሔር የሟቾችን ነፍስ በሰላም እንዲያስርፍ፣ በአደጋው የተጎዱ ሰዎችን ቶሎ እንዲያገግሙ፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ ሰዎች ሁሉ መጽናናትን መመኘታቸውን ከስፍራው ከደረሰን ዜን ኣለመረዳት ተችሉዋል።
 

28 October 2018, 17:27