የሚሳይል ጦር መሣሪያ ትጥቅ ማስፈታት የሚሳይል ጦር መሣሪያ ትጥቅ ማስፈታት  

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ የኒውክሌር ጦርነት ስጋት ተወግዶ ሰላም እንዲወርድ ጸሎት አቀረቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሑድ መስከረም 29/2015 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከተሰበሰቡት ምዕመናን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ባቀረቡበት ወቅት፣ በዩክሬን ውስጥ እየተባባሰ የመጣው ጦርነት ያስከተለውን የኒውክሌር ጦርነት ስጋት አስታውሰው፣ ይህ እንዳይከሰት ያለፈውን የሰላም መንገድ መከተል እንደሚያስፈልግ በማሳሰብ፣ በዓለማችን የኒውክሌር ጦርነት ስጋት ተወግዶ ሰላም እንዲወርድ በማለት ጸሎታቸውን አቅርበዋል። ከዚህም ጋር በታይላንድ በሚገኝ የመዋለ ሕጻናት ማዕከል የተፈጸመው ጥቃት ሰለባ የሆኑትን በጸሎታቸው አስታውሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ካለፈው በመማር የሰላምን መንገድ መምረጥ አስፈላጊ እንደሆነ የገለጹት ቅዱስነታቸው፣ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ወቅት ማለትም ከስልሳ ዓመታት በፊት የሆነውን በመጥቀስ፣ በኩባ የሚሳይል ቀውስ ወቅት በሰሜን አሜሪካ እና በሶቪዬት ኅብረት መካከል የነበረውን የእርስ በርስ ግጭት አስታውሰዋል። በዚያን ጊዜ መላውን ዓለም ፍርሃት ውስጥ የከተተውን የኒውክሌር ጦርነት አደጋ ልንዘነጋው አንችልም ብለው፣ ከታሪክ መማር የማንችለው ለምን እንደሆነም ጠይቀዋል። በዚያን ጊዜም ግጭቶች እና ከፍተኛ ውጥረቶች የነበሩ ቢሆንም የሰላም መንገድ እንደተመረጠ አስታውሰው፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ፣ በኤር. 6:16 ላይ እግዚአብሔር፥ “በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፣ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፤ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም መድኃኒት ታገኛላችሁ።” ያለውን ጠቅሰዋል። 

ብጽዕት ማርያ ኮስታንዛ እንግዳ ተቀባይ እንድንሆን ትረዳናለች

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ እሑድ መስከረም 29/2015 ዓ. ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ይፋ በሆነው በአቡነ ጆቫኒ ባቲስታ ስካላብሪኒ እና በወንድም አርቴሚድ ዛቲ የቅድስና አዋጅ ሥነ-ሥርዓት ላይ ላይ ለተገኙት ምእመናን በሙሉ ሰላምታቸውን አቅርበው፣ ለኦፊሴላዊ ልዑካን አባላትም ምስጋናቸውን አቅርበውላቸዋል። ቅዱስነታቸው ከዚህ ጋር አያያዘው፣ መስከረም 29/2015 ዓ. ም. ጣሊያን ውስጥ ፋብሪያኖ ከተማ ይፋ የሆነውን የብጽዕና አዋጅ አስታውሰው፣ በአካባቢው በሚገኝ ገዳም ውስጥ እ. አ. አ ከ1917 እስከ 1963 ዓ. ም የኖረች የቅድስት ኪያራ ማኅበር መነኩሴ፣ የማርያ ኮስታንዛ የብጽዕና በዓልን አስታውሰዋል።

ብጽዕት ማርያ ኮስታንዛ የገዳሙን በር የሚያንኳኩትን በሰላም እና በእምነት ተቀብላ ስታስተናግድ መቆየቷን አስታውሰው፣ የደረሰባትን የሕመም መከራዋን ለሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ማቅረቧን አስታውሰው፣ ብጽዕት ማርያ ኮስታንዛ ዘወትር በእግዚአብሔር እንድንታመን፣ ዕርዳታን የሚጠይቁ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን በደስታ ለመቀበል ትረዳን ዘንድ በጸሎታቸው ተማጽነዋል።

በታይላንድ የተፈጸመው የጥቃት ድርጊት

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ በታይላንድ መዲና ባንኮክ በሚገኝ የመዋለ ሕጻናት ማዕከል፣ 24 ህጻናትን ጨምሮ በጠቅላላው በ35 ሰዎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት በማስታወስ፣ በተለይም የሕጻናትን እና ቤተሰቦቻቸው ነፍስ ለእግዚአብሔር በአደራ አቅርበዋል።

10 October 2022, 16:56